May 16, 2020
5 mins read

የውስጥ ጠላቱን ያላሸነፈ የውጭ ጠላቱን መቼም አያሸንፍም – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አንድ ጓደኛየ በከፍተኛ ብስጭት “መጀመሪያ መምታት ለግብጽም ሆነ ለሌሎች የውስጥም ሆኑ የውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች በገንዘብ ራሳቸውን ሸጠው እርስ በርስ የሚያበጣብጡንን እንትናን፣ እንትናንና እንትናን ነው!…” እያለ እንደሽሮ በንዴት ሲንተከተክ ከአፉ ቀለብ አድርጌ ይህችን አጭር ማስታወሻ ጻፍኩ፡፡ እርሱ የሰዎቹን ስም እየጠራ ነበር የሚንፈቀፈቀው፡፡ እኔ ግን “ጃፋር፣ ገርቡና ልቀቱ” እያልኩ እንደሱ ስም በመጥራት በስም ማጥፋት ወይም በግድያ ዛቻ መከሰስ ስለማልፈልግ  ስማቸውን በሆድ ይፍጀው ተውኩት፡፡

እርግጥ ነው፡፡ ማንም ወገን የውስጥ ጠላቱን ለይቶ ካላስወገደ ምንም ዓይነት ውጊያ አያሸንፍም፤ በልማትም ሆነ በሥልጣኔ ስንዝርም ብትሆን ሊጓዝ አይችልም፡፡ ማስወገድ ሲባል ለኢትዮጵያዊ ቀድሞ የሚታየው መግደል ሊሆን ይችላል፤ ይህም የሚሆነው የብዙዎቻችን አስተዳደግ ከግድያና ከጠበንጃ ጋር ብዙ ቁርኝት ስላለው ይሆናል፤ በጨዋነት ተነጋግሮ በሃሳብ ልዩነት መሸናነፍ ብርቃችን በመሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡ በሰለጠነ ዓለም ግን ግድያ ምርጫ ውስጥ ሊገባ የማይገባው ምናልባትም ከገባ በመጨረሻ የሚመጣ ነው፡፡

ስለሆነም ጓደኛየ የጠቀሳቸውን የመሰሉ የሀገራችን ጠላቶች ዋናው መለየታቸው እንጂ የአወጋገዳቸው ጉዳይ ብዙም ከባድ አይሆንም፡፡ እነሱን መምከር፣ መገሰጽ፣ ማስመከርና በዚህ አልመለስ ካሉ ህግን ተከትሎ በሀገር ክህደት ወንጀል በመክሰስ የሚገባቸውን ቅጣት በትክክለኛ የፍርድ ሂደት ማስበየን ነው፡፡ እፍኝ የማይሞሉ ሰዎች ሆድ እምብርት ባጣ ቁጥር፣ የጥቂት አጋሰሶች ቁሣዊ ፍላጎት ለከት ባጣ ቁጥር ሀገር ልክ እንዳሁኑ በቁሟ እንጦርጦስ መውረድ የለባትም፡፡ እነሱን ሁልጊዜ እያባበሉና እሹሩሩ እያሉ የፈለጉትን እንዲያደርጉ መፍቀድ ደግሞ ከነሱ እንደ አንዱ መሆን አለዚያም በአንድ ወይ በሌላ መንገድ እነሱንና በጠማማ መንገድ ተጉዘው ያገኙትን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ  መፍራት ነው፡፡  ከነሱ እንደ አንዱ ሆነን ወይም ፈርተን ደግሞ እንዲሁ በማስመሰል ብቻ  ይህችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ማጥ ማውጣት አንችልም – በጭራሽ፡፡ ድካማችን ሁሉ በዜሮ እየተባዛ ከንቱ እንቀራለን እንጅ ሰላም፣ ዕድገትና ብልጽግና ዕንቁልልጭ ናቸው፡፡ የምንችለው ሀገራችንን ይበልጥ ቅርቃር ውስጥ መክተትና የነፃነቷን ቀን ማራቅ ነው፤ ሁለት ተሸናፊዎች ደግሞ አንድ የሁሉም ሊሆን የሚችልና የሚገባው ድል ሊያስመዝግቡ አይችሉም (መንግሥትና ከሃዲዎች እየተፈራሩ ቢጓዙ ሁሉም ተሸናፊ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡) ጠላትህን እጉያህ ወትፈህ፣ ከዚያም ባለፈ በዘረኝነት አረንቋ ገብተህም ይሁን የድንቁርና ሰለባ ሆነህ  ለጠላትህ የሽፋን ተኩስ እየሰጠህ፣ “አገር፣አገር” ብትል “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ዓይነት ራስን የማታለል ቂልነት ነው፡፡ በቃ፡፡

እግዚአብሔርን የምለምነው ነገር አለኝ፡፡ እርሱም “ምንም የሚሣንህ ነገር የሌለህ አምላኬ ሆይ! ሀገራቸውንና ወገናቸውን ሸጠው በሚያገኙት ገንዘብ የተንደላቀቀ ሰይጣናዊ ኑሮ የሚኖሩ ብኩን ዜጎች በደም የተገዛ ኑሯቸው ኅሊናቸውን እየኮሰኮሰ የአእምሮ ዕረፍት ሲነሣቸው፣ በሀገር ሸያጭ ገንዘብ የሚበሉት ወፍራም እንጀራ ደም ደም እያለ ወይም እየመረረ አልዋጥ ሲላቸውና ከሆዳቸው ወደ ሕዝባቸው ሲመለሱ በዕድሜ ዘመኔ እንድታሳየኝ እማጸንሃለሁ፡፡

አሜን፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop