ዘ-ሐበሻ

እውን የወልቃይትና የራያ ጉዳይ የህግ መንግሥት ተብየው  ጉዳይ ነው?

የትግሬ አዲስ አጀንዳ…

May 12, 2024

ጠገናው ጎሹ

በሁለቱ የኢህአዴግ እኩያን አንጃዎች (በፈጣሪው ህወሃት እና የእርሱ ፍጡርና ፍፁም አሽከር በነበረው ኦህዴድ/ብልፅግና)  መካከል በተፈጠረ የበላይነቱ (የጠርናፊነቱ) ሥልጣነ ዙፋን   “የይገባኛልና የአይገባህም”  ውዝግብ ምክንያት እጅግ አስከፊ የሆነ አገራዊ ጉዳት ካደረሱ በኋላ አንዱ ሌላውን አሽንፎ ሊቀጥል እንደማይችል ሲገነዘቡ  እና የዓለም ማህበረሰብን ተፅዕኖ  በቀላሉ  ማለፍ እንደማይቻላቸው ሲረዱ በሦስተኛ ወገን አቀራራቢነትና ጫና ፈጣሪነት “የፕሪቶሪያና የናይሮቢ የሰላም ስምምነት” እየተባለ በሚጠራው የስምምነት   ሰነድ ላይ ተፈራርመዋል።

በመሠረተ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን ለአገር (ለህዝብ) ካላቸውና ሊኖራቸው ከሚችለው ጠቀሜታ አንፃር እንዲህ አይነት እጅግ አስከፊ የሆኑ ፖለቲካ ወለድ ጦርነቶች ሲሆን እንዳይጀመሩ የማድረግን ፣ ካልሆነም ቢያንስ ብዙ ውድመት ሳያስከትሉ እንዲቆሙ የማድረግን እና ይህ ካልሆነ ደግሞ ከመሪር ተሞክሮ በኋላም ቢሆን ትርጉም በሚሰጥ ፀፀት፣ ቁርጠኝነት፣ የህዝብ አሳታፊነት  እና አስተማማኝ ዘላቂነት ባለው የድርድርና የስምምነት አግባብ የማስቆምን  አስፈላጊነት የማይረዳና የማይፈልግ እውነተኛ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መከባበር፣  ሰላምና የጋራ እድገት ፈላጊ የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም።

ገዥዎቻችንም ሲሆን ይህንን እውን ለማስደረግ የሚያስችል ፖለቲካዊና ሞራላዊ ተፈጥሮ፣ ባህሪና ተሞክሮ ያላቸው ቢሆኑ ኖሮ እና እኛም ዘመን ጠገቡንና አስከፊውን ፖለቲካ ወለድ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማራቸውን አስወግደን መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ እውን ከማድረግ ይልቅ በባዶ የቃላት ዲስኩር በተቃኘውና በተለወሰው የሸፍጥ፣ የሴራና የጭካኔ ፕሮፓጋንዳቸው ተሽመድምደን ባንወድቅ ኖሮ ምንኛ በታደልን ነበር።ግን አልሆነም።

ለዚህም ነው  ሁለቱ አንጃዎች (የአራት ኪሎውና የመቀሌው) አያሌ ሚሊዮኖችን ከገደሉና ካገዳደሉ፣ እጅግ አያሌ ሚሊዮኖችን መግለፅ ለሚያስቸግር የቁም ፍዳ (ሰቆቃ) ከዳረጉ እና በአጠቃላይ አገርን ምድረ ሲኦል ካደረጉ በኋላ ቢያንስ ለሆነው ሁሉ እናዝናለን የሚል መሠረታዊ የሰብአዊነት ድምፅ እንኳ ሳያሰሙ የፕሪቶሪያና የናይሮቢ ስምምነት ተፈራርመው በመተቃቀፍና  የችርስ ብርጭቆ እያጋጩ ከደሙ ንፁህ እንደሆኑ አድርገው የተሳለቁብን።

የዚህ የሸፍጥና የሴራ ስምምነታቸው ሰለባ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ነው። ጥያቄው ለምን? በማን? ለማን? እንዴት? ከየት ወደ የት? የሚል እንጅ  የድርድርንና  የስምምነትን መሠረታዊ ጠቀሜታ የመካድ ወይም የማጣጣል ጉዳይ  አይደለም።  እንኳንስ ከአጎራባች ትግራይ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በመሄድ ሠርቶና ተከባብሮ ይኖርባቸው የነበሩትንና ለረጅም ዘመናት በአማራ ሥር ሲስተዳደሩ   የነበሩትን ወልቃይትንና ራያን   በጉልበት ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ህገ መንግሥትነት በተለወጠ ርካሽና አደገኛ የፖለቲካ ፕሮግራማቸው” ከዛሬ ጀምሮ ምእራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ ሆነዋልና ይህንን የማይቀበል ወይም የሚቃወም ወዮሎት” በሚል ንፁሃንን ለግፍ አሟሟትና ለቁም ሰቆቃ መዳረግ ፈፅሞ ይቅርታ የሌለው ትውልዳዊ ወንጀል መሆኑን ለመረዳት ብዙና ጥልቅ የሆነ ጥናትን አይጠይቅም። ይህ ደግሞ ከትግራይ የተገኙና እድሜ ጠገብ የሆኑ እውነተኛ ኢትዮጵያዊያንን ምስክርነትንም ይጨምራል።

እርግጥ ነው የሃሰት ትርክት እየፈበረኩ አማራንና የአማራ የሆነውን ሁሉ እጅግ አደገኛ በሆነ የሸውራራነት አመለካከት መርዝ እየበከሉ ያሳደጉትን የእነርሱ ዘመን ወጣት ትውልድ ወደ እውነተኛው የጋራ መግባባትና የእድገት ጉዞ መስመር ማምጣት ቀላል አይሆንም። በእኩያን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ መሃንዲሶችና ጠርናፊዎች ሥርዓት ከርሰ መቃብር ላይ እውነተኛ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መተሳሰብ፣ ፍቅር፣ ሰላምና የጋራ እድገት የሚረጋገጥባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ካለብን ይህ ትውልድ እኩያን ገዥ ቡድኖች ካስለከፉት የጎሰኝነት፣ የመንደርተኝነት ፣ የደምና የአጥንት ስሌት ፖለቲካ ማንነት ይላቀቅ ዘንድ እልህ አስጭራሽ ጥረትና ትግል የግድ ነው።

ማንም ነፃ አውጭ ነኝ ባይ ጊዜና ሁኔታውን  እየተጠቀመ መሬትን ብቻ ሳይሆን መሠረታዊውን የማንነት መብት በጉልበት እየደፈጠጠ እና ሽፍትነቱንና ዘራፊነቱን በህጋዊ ሰነድ ስም ህጋዊ እያስመሰለ የሚኖርበት አገር የአናርኪስቶችና የአደገኛ ቀማርተኞች ምድር እንጅ  ትክክለኛ የአገር ምንነትና እንዴትነት ትርጉም አይኖረውም። በተጠና የፖለቲካ ስትራቴጂ  ጨቋኝ፣ ነፍጠኛና ትምክህተኛ የሚል  እጅግ አስቀያሚና አደገኛ የፖለቲ ትርክት ዒላማቸው ያደረጉትን የአማራን ማህበረሰብ  ከገዛ ርስቱና ቀየው  ከማፈናቀልና ለከፋ ስቃይና መከራ ከመዳረግ አልፈው በመግደል/በመጨፍጨፍ የተቆጣጠሩትን መሬት  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቀድሞው የምእራብ ትግራይና የደቡብ ትግራይ ይዞታ (status qua ante) ካልተመለሰ በሚል ያዙንና ልቀቁን ሲሉ መታዘብ ባይገርምም ለዚህ አይነት ቅዠታቸው ግን ተገቢ ምላሽ የግድ ነው።

ከህገ መንግሥት ተብያቸው በፊት ጊዜና ሁኔታውን ተጠቅመው  ሸፍጥን፧ ሴራንና ጉልበትን ባቀናጀ ሁኔታ ወደ ትግራይ የጠቀለሉት የአማራ መሬትና ማንነት አራት ኪሎ በገቡ በ4ኛው ዓመት አገዛዛቸው (1987 ዓም) በሴራና በሸፍጥ ወደ ህገ መንግሥትነት በለወጡት የፖለቲካ ፕሮግራማቸው የሚዳኝበት ወይም ትክክለኛ መፍትሄ የሚያገኝበት አንዳችም አሳማኝ ምክንያት ባለመኖሩ  ነገሮች ቀድሞ ወደ ነበሩበት ይመለሱ( status qua ante) የሚለው ፈፅሞ ተቀባይነት አይኖረውም።  በማንነቱ ምክንያት በገዛ ባድማው ላይ እንዳይኖር መደረግ ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህአዴግ የግፍ ግድያና የቁም ሰቆቃ ሰለባ በመሆን አያሌ ዓመታት ባስቆጠረው ማህበረሰብ ላይም መሳለቅ ነው የሚሆነው።

በረጅሙ የነፃ አውጭነትና በአራት ኪሎው አገዛዛቸው  ወቅት በዚያ መከረኛ ማህበረሰብ (ወልቃይትና ራያ) እና በአጠቃላይ በአገር ላይ በፈፀሙት ፖለቲካ ወለድ ወንጀል የጨቀየው ህሊናቸውና ፖለቲካዊ ማንነታቸው  በእንዲህ አይነት እጅግ አስከፊና አደገኛ ፖለቲካዊ ስላቅ እንዲቀጥል ሊፈቀድለት አይገባም።

በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን ለተፈፀመው ዘመን ጠገብና በእጅጉ አስከፊና ሁለንተናዊ ለሆነ  መከራና ውርደት ዋነኛው ምክንያት ሥርዓተ ፖለቲካው ነው። አግባብነት ባለው የሽግግር ፍትህ አማካኝነት ዲሞክራሲያዊ የሽግግር መንግሥት እውን ለማድረግ እስካልቻልን ድረስ የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ትክክለኛ መፍትሄ ያገኛል ብሎ እንኳንስ ማመን ማሰብም ፈፅሞ አይቻልም ። “በህገ መንግሥቱ መሠረት” የሚባለውና እኛም ልማድ ሆኖብን እንደ በቀቀን መልሰን የምናስተጋባው የፖለቲካ መነባንብ በሥርዓቱ አስከፊ አዙሪት ውስጥ እየጓጎጥን ተአምር እንፈጥራለን የሚል አይነት እጅግ አሳፋሪና አስፈሪ የፖለቲካ አስተሳሰብ ነው። ከዚህ አይነት አስቀያሚ ወለፈንዲነት ካልተላቀቅን በስተቀር የምንፈታው ችግርና እውን የምናደርገው ፍኖተ ዴሞክራሲ አይኖርም። የወልቃይትና የወራያ  ጉዳይም እንዲሁ።  በዘመናት ፖለቲካ ወለድ ወንጀል ህሊናወቻቸውና እጆቻቸው የበሰበሱና የከረፉ እኩያን ገዥዎች በሚያስቀምጡት ቅድመ ሁኔታና  በሚዘውሩት አውድ (መድረክ) ሥር ሆኖ እንኳንስ ውስብስብነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮች እንደ ወልቃይትና ራያ የመሰሉ ግልፅና ግልፅ የመሬትና የማንነት ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ ፍፅሞ አይቻለንም።

እናም በአማራ ፋኖዎችና በሌሎች ነፃነትና ፍትህ ወዳድ ወገኖች ተባባሪነት በመካሄድ ላይ ያለው በመሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለሁሉም ዜጎቿ የምትመች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ተጋድሎ ዓላማውን፣ መርሁን፣ አቅጣጫውን፣ ዒላማውንና ግቡን ጠብቆ ለድል እንዲበቃ ገንቢነት ባለው ሂሳዊ ድጋፍ ማጎልበት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆን ያለበት። በሽተኛ ሥርዓት በጤነኛ ሥርዓት ሲተካ የወልቃይትና የራያ ጉዳይም በወንድማማቾችና እህትማማቾች ምክክርና ድርድር አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኝ ይሆናል።

 

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት ያልተቀደሰ ጋብቻ

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት ያልተቀደሰ ጋብቻ

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት ያልተቀደሰ ጋብቻ

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት     ያልተቀደሰ ጋብቻ።

 

“የማይዘልቁ ፍቅረኞች በየወንዙ ይማማላሉ” እንዲሉ እነ ኦነግ ብልፅግና እና ህወሃት እንጣመር እና አጋር ፓርቲ እንሁን በሚል የጫጉላ ሽር-ሽር ላይ እንደ ሆኑ እየሰማን ነበር። እንግዲህ ያዝልቅላችሁ ከማለት ውጭ ምን ማለት ይቻላል።

 

የሚያሳዝነው ግን የአንድ ሚልዮን የትግራይ ወጣት ነፍስ “የደም ካሳ” ሳይከፈል በህውሃት አዛውንት ባለስልጣኖች የስልጣን ጥም መመንዘሩ ነው። የትግራይም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ይህን አካሄድ ካልተቃወመ ከባድ ችግር በሕዝቡ የመንፈስ እና የሰውነት ማንነት ላይ እንዳለ የሚያሳይ ይሆናል ።

 

በተለይ የትግራይ ዲያስፖራዎች እና እንደ ኤርምያስ ለገሰ ያሉ ተቀጣሪዎቻቸው ሰሞኑን እየለፈለፉት ያለው ከእውነት የራቀ ዲስኩር የትግራይን ሕዝብ በእውነት የሚጠቅም ከሆነ የምናየው ከመሆኑ ባሻገር መላው የትግራይ ሕዝብ ፣ በዲያስፖራ ያሉ ትግራዊ የሰብሃዊ እና የማህበራዊ አንቂዎች ትክክለኛውን የታሪክ ፣ የቱፊት እና የማንነት  ጠርዝ ይዘው እንዲጓዙ እንመክራለን። ነግሮቹ “ ከድጡ ወደ ማጡ” እንዳይሆንባቸው ከወዲሁ እኛ አማሮች ምክራችንን ጀባ እንላለን።

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከዚህ የቁጩ ስምምነት ጀርባ አጂሪት ህወሃት “ትላንት ብልፅግና ወይም አጋር ፓርቲ የሚባል ጉዳይ አታንሱብኝ ብላ ወደ ደደቢት ካመራች ፣ ጦር ከመዘዘች ፣ የትግራይን ሕዝብ እና መሪዎቿን ካስበላች በኋላ ምን ፈልጋ ይሆን ከብልፅግና ጋር የአጋር ፖርቲ ስምምነት የማድረግ ዳርዳርታ ያሰበችው?” የሚለውን ጥያቄ በጊዜ ሂደት ጉንጉን ሴራውን እና ዓላማውን የምናየው ይሆናል።

 

እንደሚታወቀው የኦሮሞ ብልፅግና እና የህወሃት ቡድኖች በዘር ፣ በነገድ ፣ በታሪክ ፣ በጆግራፊያዊ አቀማመጥ ፣ በባህል ፣በቋንቋ ፣ በቱፉት ፣ በማንነት ወ.ዘ.ተ. የሚገናኙ ሕዝቦች አይደሉም።

 

እነዚህ ብሔሮች ላለፉት 30 ዓመታት በረቀቀ እና በሴራ ኢትዮጵያን ፣ የኦርቶዶክስ እና የእስልምናን ሃይማኖት መርሆዎችን (Pillars) በመፈነቃቅል ፣ በማሽመድመድ ፣ በመበጣጠስ  ፣ ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጩ ፣ ቤተ-ክርስቲያናትን እና የእስልምና ተቋማትን እያቃጠሉ ፣ ካህናትን እና የእስልምና አባቶችን እያሳደዱ ፣ እያፈኑና እየገደሉ ዘልቀዋል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የጋራ የስልጣን ጥማቸውን ለማመቻቸት ፣ ለማስቀጠል እና ሃገረ ኢትዮጵያን በጋራ ለመዝረፍ ነው።

 

እነዚህን ቡድኖች በቅርብ ለሚያውቃቸው፣ ምርምር ላካሄደ እና የሴራቸውን ውስጠ ወይራ ቀመራቸውን ለተረዳ ይህን ለምን ለማድረግ ተነሳሱ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ በጣም ቀላል ነው።

 

አንደኛው እና ዋነኛው በ1885 እና በ1935 ኢትዮጵያ የጣሊያንን ፋሽሽታዊ ወራሪ ኃይል አዋርዳ እና አፈርድሜ አብልታ ስትመልስ ጣሊያኖች የትግራይን እና ከፊል የኤርትራ ባንዳዎችን ፀረ ኢትዮጵያዊ አቋም እንዲያራምድ ሲያደርጉ ፣ ጀርመኖች እና ምዕራባውያን ደግሞ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ነፃነት መጎናፀፍ ምክንያት ስለሆነች ይህ ኩነት ዳግም እንዳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የጥላቻ መንፈስ ያሳድር ዘንድ የእውሸት የትርክት መፅሃፎችን በመፃፍ እና “ኦነግ” የሚባል ፀረ ኢትዮጵያ ድርጅት በማቋቋም አገረ ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ ነበር የጅማሮ እቅዳቸው።

 

ምዕራባውያን ተፃፃሪ ቡድኖችን በማቋቋም  ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያደረጉት እንቅስቅሴ በአምላክም ረዳይነት ሆነ በሕዝቡ አሻፈርኝነት አልሳካ ሲላቸው “ኢትዮጵያን እንዳሰብነው ለመሰባባር ፣ ለመገነጣጠል እና ለመበጣጠስ ያልቻልነው አማራው ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ስላለው እና በሃገሩ ጉዳይ የማይደራደር በመሆኑ ነው” በማለት አጀንዳቸውን ቀይረው ህውሃት እና ኦሮሞ ብልፅግናን በገንዘብ ፣ በመሳሪያ እና በቁሳቁስ በመደገፍ እና በማደራጅት በአማራ ሕዝብ ላይ እንዲነሳሱ ፣ የአማራን አፅመ እርስቱን  በጋራ እንዲቀራመጡ እና የተፈጥሮ ሃብቱን በደቦ እንዲመዘብሩ ለእነዚህ ሃገር አጥፊ ቡድኖች የአይዟችሁ ባይነቱን እና ይሁንታቸውን በመስጠት አሁን ላሉበት ቅጥ ያጣ ፣ የሃገር አፍራሽነት ፣ የመገንጠል ፣ የሁሉ የኛ ነው እና አጉራ ዘለል ባህሪ እንዲላበሱ ትልቁን ሚና አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ተጫውተዋል።

 

እነዚህ ጉግ-ማንጉግ ቡድኖች ሲመቻቸው ፣ ለጥቅማቸው እና ለዝርፊያ ሲያስቡ “ኢትዮጵያን” በስሱ እያቆለጳጰሱ ፣ ሳይመቻቸው ደግሞ “ኢትዮጵያ በቃችን” እያሉ እና እያደናበሩ ለዘመናት በአማራው ቸልተኝነት ፣ በምን ያመጣሉ ህሳቤ እና በበይ ተመልካችነት ያሻቸውን በማድረግ ለሃምሳ ሃመታት ዘልቀዋል።

 

እነዚህ እኩያን ቡድኖች ሃገር ኢትዮጵያን  ለመበጣጠስ ካላቸው ህሳቤ አልፈው ለምን አማራውን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ተነሳሱ የሚለውን ደግሞ በመጠኑ መዳሰሱ የግድ ስለሚል እስኪ ገረፍ ገረፍ እያደረግን እንዳስሰው።

 

የኦሮሞ ብልፅግና የራሱን ክልል የሚያተራምሰውን የኦሮሞ ሸኔ ትጥቅ ሳያስፈታ “ፋኖን ትጥቅ ላስፈታ ነው” በሚል እንደ አስራ አራተኛው ክፍለዘመን የግራኝ መሀመድ ወረራ በአማራ መልክአ ምድሮች የገባበት ጦርነት እንዳሰበው ካለመሆኑ ባሻገር ሰራዊቱም እንደ አሸን እየረገፈ ፣ ፋኖም ድል እየቀናው ይገኛል።

 

እንግዲህ የትግራይ ሕዝብ ሞት የማይገዳቸው ያፈጁ እና ያረጅ የህውሃት ባለሥልጣኖች ጎረቤታቸውን ፣ ቀላቢያቸውን ፣ የክፉ ቀን አለሁ የሚላቸውን ፣ ቀለብ የሚሰፍርላቸውን ፣ አስጠጊያቸውን ወ.ዘ.ተ. የአማራን ሕዝብ ከኦሮሞ ብልፅግና ጎን ሁነው ለመውጋት በመደራደር ላይ ከመሆናቸው ባሻገር የፋኖን የትግል እምርታ ለማጨናገፍ “ የቀቢፀ ተስፋ የውል ሰነድ ለመፈረም በመንደርድር ላይ ይገኛሉ ።

 

ህወሃት “የአማራን ሕዝብ ቋሚ ጠላቴ እና ሂሳብ አወራርዳለሁ” ብሎ ደደቢት በርሃ ከወረደ ማግስት ጀምሮ ይህን ህሳቤ የያዘና ብዙ ጊዜ ሞክሮ ያልተሳካለት ቢሆንም በዚህ ህሳቤው ከቀጠለ የአማራ ሕዝብ “በሶ ጨብጦ” የሚጠብቀው መስሎት ከሆነ የምናየው ይሆናል። ያም ሆነ ይህ “ በእንቅርት ላይ ጀሮ ገድፍ” እንዳይሆንበት እኛ የአማራ ሕዝቦች “ምከረው ምከረው ካልሆነ መከራ ይምከረው” እንዲሉ ለህውሃት ከወዲሁ የማስጠንቀቂያ ድወል በመላው የአማራ ሕዝብ ስም ፅኑ መልክታችንንን እናስተላልፋለን።

 

የኦሮሞ ብልፅግና እና ህወሃት የሚያመሳስላቸው እና የሚጋሩት ፅዩፍ ባህሪ አላቸው እሱም ተስፋፊነት ፣ ስግብግብነት እና “ሁሉ የኛ” ማለትም በነሱ አነጋገር “ ኬኞ እና ኩሉ አነ” በሚል ርኩስ አስተሳሰብ እና በግለኝነት አባዜ የተለከፉ ናቸው።

 

እነ ኦሮሞ ብልፅግና እና ህወሃት “አዲስአበባ ፣ ወልቃይት ፣ ራያ ፣ ደራ ወ.ዘ.ተ. “ የኛ ነው እያሉ ይዘባርቃሉ።

 

መጤ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ “የኔ ነው” ካለ የኢትዮጵያ የዕርስት ባለቤት የሆነውን የአማራን አፅም እርስቶቹ  “የአንተ እይደለም ፣” ከተባለ እና ድፍረት በተሞላበት ህሳቤ ይህን ፅንፍ ህሳቤ ካራመዱ የሚሆነውን ሁሉ ወደፊት የምናየው ይሆናል።

 

ኦነግ ብልፅግና እና ህውሃት ሆን ብለው ይህን የሚያደርጉት በጋርዮሽ ፣ ተካፍለን እና አካፍለን በጋራ እንኑር የሚል ህሳቤ በአዕምሮአቸው ስላልተፈጠረ ፣ በድህነት እና በጠባብነት አስተሳሰብ አባዜ ስለተለከፉ እንዲሁም በጋራ ያፀደቁትን ፉርሽ ፣ መላ ሃገረ ኢትዮጵያን በይበልጥኑ የአማራን ሕዝብ የማይወክለውን ገንጣይ ፣ አስገንጣይ ህገ-መንግስታቸውን መሰረት በማድረግ ፣ በጉልበት እና በአጉራዘለልነት የአማራ አፅም እርስቶችን እነሱ በሳሉት ካርታ አጠቃለው የውጭ ሃገር መንግስታት አስጎባሻቸው በአሜሪካ ፣ በምዕራብውያን ሀገሮች አይዞህ ባይነታቸው ታክሎቡት በመገንጠል ሃገር ሆነው ለመኖር ስላሰቡ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።

 

ህውሃትና የኦሮሞ ብልፅግና በለውጥ ተብየው የአምስት ዓመት ክራሞታቸው  የገቡበትን ፍትጊያ ፣ ጦር ያማዘዛቸው ጉዳይ ፣ አሻጥራቸውን እና እንደገና ከተገዳደሉ በኋላ ጥምረት የመፍጠር  “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል የአነገቡት አካሄድ፣ሴረኛነታቸው ስግብግብነታቸውን ለማየት ብዙ እርቀት መሄድ አያስፈልግም።

 

የኦሮምያው ብልፅግና ቆዳውን ቀይሮ የትግራይን ሕዝብ “የደረሰብህ በደል ያንገፈግፋል ፣ አማራው አታሎናል፣ አማራ የጋራ የብሔር ጭቆና አድርሶብናል ፣ ወልቃይትና እራያ ያንተ ነውና የጋራ ጠላታችን አማራ ነው” እያለ እየወሸከተ ሃገርና ሕዝብን ለሌላ እልቂት እያንደረደረ ሲሆን “እባብ ለእባብ” እንዲሉ ህውሃትም ይህን የሸፍጥ አካሄድ ልቡ እያወቀ እየገፋበት ይገኛል።

 

በልምድ እንደታየው የሃገረ ኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ውድቀት ሊያመሩ ሲሉ “ታስሮ እንደተፈታ ወይፈን” ይደነብራሉ ፣ ግራ ይገባቸዋል ፣ መስመራቸውን ይስታሉ፣ እውር ድንብሩን ይጓዛሉ፣ ዘላቂ ወዳጃቸውንና አጥፊያቸውን መለየት ይሳናቸዋል።

 

በኦሮሙማ የበላይነት የተዋቀረው ጅላንፎው የብልፅግና መንግስት “ ታሪካዊ የጋራ ጠላታችን አማራ ነው ፣ አማራን ደግሞ ማበርከክ የምንችለው ከውጭ ጎረቤት ሃገራት  የሚያገናኘውን የአማራን ለም መሬት ወልቃይትን እና ኩሩውን የራያን መሬት ወደ ትግራይ አጠቃለን በማካለል ብቻና ብቻ ነው” በሚል የከረፈፍ አካሄድ ከህወሃት ጋር ደም መቃባቱን ወደጎን ብሎ ተማምሎ የጋራ የጥፋት ጉዟቸውን ጀምረዋል።

 

ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረውን የህወሃት አካሄድ ተከትለን አማራን ፀጥ አድርገን ፣ እረግጠንና አንገላተን በተለመደው መልኩ ካልገዛነው አማራ ይውጠናል  የሚለውን የደናቁርት ህሳቤ ህወሃት በለመደው አስማቱና ሽወዳው ለኦሮሙማው ብልፅግና ሹክ ብሎት “ጭዋታ ፍርስርስ ያደረ እንጀራ ቁርስርስ” ዓይነት የልጆች ጭዋታ”ና “የነተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ” እንዲሉ ይህን በመርዝ የተለወሰ የደባና የተንኮል ውሳኔ ተከትለው ከተጓዙ እነ ብልፅግና “የፈንጅ ወረዳ”  እንደረገጡ ይቁጠሩት።

 

“አያ በሬ ሆይ ሳሩነን አይተህ ገደሉን ሳታይ” እንዲሉ የኦሮሞ ህዝብ ከሰላሳ ዓመት የህውሃት መወገር ፣ መታሰር ፣ መደፈር ፣ ስቃይና እንግልት እንዲላቀቅ “ የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” ብሎ ከጎኑ የቆመውን ፣ በህግ ማስከበር የህልውና ጦርነት ወቅት ከቆላ ተምቤን ተነስቶ አዲስ አበባ ጫፍ አካባቢ ደርሶ ብልፅግናን ከስልጣኑ ሊያስፈነጥረው የነበረውን ህወሃትን መልሶ ወደ ሸጎሬው ቆላ ተንቤን የመለሰለትን  የአማራ ሕዝብ ክዶ “ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል አጓጉል ህሳቤ  በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ደባና የጦርነት ጉሰማን የኦሮሞ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኖ ካየ ለወደፊቱ ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን ሊረዱት ይገባል።

 

የህውሃት የክህደት አካሄዱ በሃያ ሰባት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ ያሳየው ፣ በአማራውም ሆነ በኦሮሞው ላይ የተገበረው በመሆኑ “የቆየ ይየው” እንዲሉ ለወደፊቱ ህወሃት እና ብልፅግና ሥልጣን ላይ ከሰነበቱ እርስ በርሳቸው እንደሚባሉ እና ጦር እንደሚማዘዙ”  እኛ የኢትዮጵያዊያንና የአማራ ሕዝቦች አስረግጠን እንናገራለን ፣ “የዛ ሰው ይበላችሁ” እንላለን። ህወሃት በ1983 ስልጣን በያዘ በሽግግር መንግስት ወቅት፣ በሕገ መንግስቱ ማርቀቅ እና ማፅደቅ ማግስት እንዴት አርጎ የእነ “ሌንጮ ለታን” የኦነግ ቡድን  ቁማር እደበላው እና እንደጨፈጨፈው ሊታወስ ይገባል።

 

ይህን ያልንበት ምክንያት “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” እንዲሉ እነብልፅግና በአለበሌለ የጦር መሳሪያ ፣ በሚሲያል፣ በድሮን፣ ከአየር ላይ በሚወረወር ክላስተር ቦንብ ምድረ ትግራይን  አጋይተው እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የትግራይን  ሕዝብ ከጨፈጨፉ በኋላ “ወልቃይትና ራያን” በካሳ በመቸር ለመታረቅና እንደገና ጋብቻ ለመፈፀም መዳዳታቸው ከማሳቅ አልፎ ያንከተክታል።

 

እንደ ቀላል  የባልና ሚስት ተጣልቶ መታረቅ አይነት ጉዳይ ካደረጉት የሚጎዳውና ይበልጥ ዋጋ የሚከፍለው ኦሮሞ እና  የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

 

እንደ እስቆሮቱ ይሁዳ የአማራን ሕዝብ “የኦሮ- አማራ ጥምረት ብሉው ጉንጭ ስመውና በሕግ ማስከበሩ አድኑን” በለው የአማራን ሕዝብ ከተማፀኑና ስልጣናቸውን ካስጠበቁ በኋላ እነ ኦሮሞ ብልፅግና አማራን መካዳቸው ታሪክ የማይረሳው ጠባሳና የሚያስተዛዝብ አካሄድ እንደሆነ ሊገነዘቡት የግድ ይላቸዋል እንላለን።

 

ከዚህ ባሻገር ሊታወቅ የሚገባው “ቦ ጊዜ ለኩሉ” እንዲሉ አማራ ቢገደል ፣ ቢሰቃይ ፣ ቢፈናቀልና ቢንገላታ ለነፃነቱ መታገል ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰው ስለሆነ መስዋህትነት ሊይስከፍል ይችል እንደሆን እንጂ አሸናፊው ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊውና የሃገር ካሳማና መከታ የሆነው የአማራ ህዝብ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

 

ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ  ከዕርስት ባለቤታቸው  አማራ ምድር ጋር ሆነው ለዘለዓለም እንደሚቀጥሉ የሚጠራጠርና የሚያቅማማ አማራ እንደሌለ ቁርጣችሁን እወቁ እንላችዋለን።

 

ይህን ሃቅና እውነታ እቀለብሳለሁ ብሎ የሆነ ቡድን ከመጣ ግን እንደ ታይዋኗ የቻይና አካል ፣ እንደ ካሽሚር ፣ እንደ ዮክሬን ፣ ፓሊስትያን ፣ ከርድሽ ና ሌሎችም የትግል አካሄዶች ፍልሚያው ይቀጥላል ።

 

የአባቶቻችንን የከለው አማራ ነገድ ምድርን  እንደ ቁራሽ እንጀራ እኛ አማሮች የትዕብታችንን መገኛና መቀበሪያ ምሬታችንን ለማንም አሳልፈን  አንሰጥም ፣ እርማችሁን አውጡ።

“አማራ ያቸንፋል”

“አዲስ አበባ ፣ ወልቃይት ፣ ራያ እና መተከል የአማራ ሕዝብ ቀይ መስመሮች ናቸው”

 

 

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

“አዲስ አበባ ገብተናል” ፋኖ | ፋኖ ባህርዳርን ሊቆጣጠር ነው | አቡነ አብረሀም በአብይ የበቀል እርምጃ ተወሰደባቸው | የአብይ የባህርዳር ጉዞ አደጋ ውስጥ ገባ | “አዳነች ከእግ/ር ትበልጣለች” ዶ/ር እመቤት |

 

 

 

በቅርቡ ለህዝባችን አንድነታችንን እናበስራለን | “አብይ ክዶናል፣ ህዝቡ ጠልቶናል” ክፍፍል ተፈጠረ | ወልቃይት ሁለቱም ተፋጠዋል

 

ታሪክ ራሷን ደገመች ኢትዮጲያ በሌላ ግፈኛ መሪ መዳፍ ስር ወደቀች

ታሪክ ራሷን ደገመች ኢትዮጲያ በሌላ ግፈኛ መሪ መዳፍ ስር ወደቀች

ታሪክ ራሷን ደገመች ኢትዮጲያ በሌላ ግፈኛ መሪ መዳፍ ስር ወደቀችበሃገራችን ኢትዮጲያ ከጥንት ከነገስታቱ ዘመን ጀምሮ  በጎ ታሪኮችም ክፉ ታሪኮችም  በመሪዎች ሲካሄዱ ኖረዋል:: ጸሃፍቱና መገናኝ ብዙሃን/ ሚዲያን የሚቆጣጠሩት  መሪዎች በመሆናቸው የመሪዎቹ ታሪክ ጸሃዩ ንጉስ ቆራጡ ፕሬዚዳንት ብልሁ አስተዋዩ ጠቅላይ ሚንስትር እየተባለላቸው ዛሬ ደርሰናል  ግፉም  እንዲሁ  ካንዱ መሪ ወደሌላው ታሪክ ተደገመች  ሆኖብናል::

በደርግ መንግስት  ቀይሽብር በተባለው ዘግናኝ  ጭፍጨፋ  ተጠያቂ የነበሩትን ለህግ የማቅረብ ሂደት ቀጥሎ አትሌት  ሻምበል ማሞ ወልዴ የኪነጥበብ ባለሙያ አስር አለቃ ተዘራ ሃይለሚካኤልና መሰሎቻቸው ሳይቀሩ ተይዘው ምርመራው ሲቀጥል ጥቆማው  ወደሁሉም የደርግ ሃላፊዎችና ባለስልጣናት ሲያመራ የዝግ ችሎቱን ያካሂዱ የነበሩት አፈንጉስ ተሾመ ቅጣው  ጉዳዩን በይደር እያቆዩ  ደርግ ተጠያቂዎቹን በሙሉ ማቅረብ  ያለመፈለጉን ሲረዱ ያንዳንዶቹም ምርመራ እንዳይካሄድ ሰሞኑን ዶ/ር  አብይ ባዘዙት መልክ ሲያግድ አፈንጉስ ተሾመ በጤና ምክንያት ብለው ከሃገር ተሰደው በዚያው ቀርተዋል::

አፈንጉስ ተሾመ በክፉ ቀን መሸሸግ እንደሚሻል “ክፉ ቀንና ቅምዝም ዱላን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ነው” በሚል ምሳሌያቸው የሚታወቁ ሲሆኑ  ትክክለኛው  የፍትህ መንበር ቅምዝሙን ሳይፈራ  ፍትህን የሚዳኝ መሆኑን በታሪክ በቅን ፍርዳቸው የተጋዙ የተገደሉ የተሰደዱ የሃገራችንም ሆነ የሌሎች ሃገሮች  ዳኞች ወርቃማ ምስክርነት ይገኛል:: በዚህ አጋጣሚ የወያኔን የካንጋሮ ችሎት ሳትፈራ  ወያኔ በግፍ ያሰራቸው የራሱን ባልደረቦች እነስዬ አብርሃን በነጻ ያሰናበተች ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን ከወቅቱ የፖለቲካ ምልከታዋ  በማይገናኝ መልኩ ሙያዊ ብቃትዋን ላደንቅ እወዳለሁ::

የመቂው ጎልማሳ ባቲ ባልተለመደ ከኦነግ ፖለቲከኛንና ምሁራን በተለየ በመድረክ ውይይት ከሌሎች የኢትዮጲያ ፖለቲከኞች ጋር የሚወያይ ባለተስፋን ሰው ግድያ ዶ/ር አብይ ከፎከሩበት በፓርቲያቸው ላይ የሚነሳ አመጽን ከኢሃአፓ ጊዜ በበለጠ እጥፍ እንበቀላለን ያሉትን ለመጀመራቸው ማረጋገጫ  ሲሆን  የሚያሳዝነው ግን በዚህ መልኩ ለግል ስልጣን የሰዎችን ደም የሚያፈሱ መጨረሻቸው ለራሳቸውም ለልጆቻቸውም ሃፍረት መሆኑን  ምንም የተማረች ሃገሯን የትምትወድ ቢሆንም የደርጉ ጨፍጫፊ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ልጅ ዶክተር ትእግስትን በየሚዲያና በየመደረኩ የሚደርስባት ወከባ ማዋረድ ምስክር ነው:: የሌሎቹ አምባገነኖች ልጆች የስታሊን ልጅ እንዳደረገችውን ወላጅ አባትዋን ክዳ  ከሩሲያ ህዝብ ጎን በመቆም ለስደት የተዳረገችው ትገኛለች::

ስለዚህ ዶ/ር አብይ የሰው እድሜ ቢበዛ ሰባ ሰማንያ በሚለው ቅዱስ መጽሃፍ ግማሹን በሰላም ይፈጽሙ ዘንድ  የሰው ደም በፖለቲካ ሴራ  ፈስሶ እንዳይቀር  የሚቻልዎትን ያድርጉ በክፉ የዘር ፓለቲካ ወክለዋለሁ በሚሉት የኦሮሞ ክልል ጭምር የሚያልቀው ህዝባችን   ጉዳይ ግድ ብሎት ባፋጣኝ ስልጣኑንን የኔታ ፕሮፌሰር መስፍን  ለደርግ በሰጡት ምክር ለህዝብ ባላደራ በቶሎ ያስረክቡና ከምድራዊም ከዘላለምዋም ቁጣ ይተርፉ ዘንድ ምክሬን ለግሳለሁ:: የኤቤል ደም በከንቱ ፈስሶ እንዳልቀረ ሁሉ የወገኖቻቻን  ደምም  በከንቱ ፈስሶ እንደማይቀር መጽሃፉ/ ኪታቡ ታሪክም ባህላችንም ምስክር ነው

 

ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

 

የኢዜማ ወጣቶች እየታደኑ ነው | አገኘሁ ታፈነ የእጅ ስልኩን አብይ ነጠቀው | የባህዳር ደብረ ማርቆስ መንገድ ተዘጋ | “ኦሮሞዎቹ ይታጠቁ፣ ሌሎች ትጥቁን ያውርዱ” አብይ አህመድ

 

 

 

 

 

የገዛ ራሳችንን የውድቀት አዙሪት ለመጋፈጥ የተሳነው የእንኳን አደረሰንና የመልካም ምኞት መግለጫ

ለመሆኑ  የከሞት በኋላ ህይወት መንገዱና መግቢያው ምንድን ነው?
ገዳይ አብይ አህመድ መመለስ ያለበት ጥያቄ
ለመሆኑ  የከሞት በኋላ ህይወት መንገዱና መግቢያው ምንድን ነው?
ገዳይ አብይ አህመድ መመለስ ያለበት ጥያቄ

ጠገናው ጎሹ
May 5, 2024

በዓለ ትንሳኤውን አስመልክቶ ከሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው የተላለፉትን የእንኳን አደረሳችሁና የመልካም ምኞት “መግለጫዎች” ዋው! በሚያሰኝ አኳኋን እንኳ ባይሆን ለዘመናት ተዘፍቀን የመጣንበትን፣ ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ከደመ ነፍስ እንስሳት በታች ያዋለንን እና የዓለም ከንፈር መምጠጫና መሳለቂያ ያደረገንን ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት የሚመጥን ቁም ነገር ይኖረው ይሆን? በሚል አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ደግሜ ተከታተልኩት።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክዊ እምነት መሠረት ከዓብይ የፆምና የፀሎት ወቅት በኋላ የሚከበረውን የትንሳኤውን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሰንና የመልካም ምኞት መልእክት ማስተላለፍና መለዋወጥ የሚሰጠውን ጥልቅና መልካም የሆነ መንፈሳዊና ማህበራዊ ስሜት ለመረዳት (ለማወቅ) የሚዛናዊ፣ የቅን፣ የመቻቻል፣ የመከባበር ፣ ወዘተ ህሊና ባለቤት መሆንን እንጅ የግድ ሊቅነትን ወይም ሊቀ ሊቃውትነትን የሚጠይቅ አይመስለኝም።

ከምር በሆነ የሃይማኖታዊ እምነት አማኝነት እና የሰብአዊና የዜግነት መብት ተሟጋችነት አቋምና ቁመና ላይ ሆነን የባለጌዎችንና የጨካኞችን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት በቃ ለማለት ባለመቻላችን ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው በእርሱና በካምፓኒው (በግብረ በላ ሠራዊቱ) ምክንያት የሆነውንና እየሆነ ያለውን ግዙፍና መሪር እውነታ በአፍ ጢሙ ደፍቶ “እንደ ክርስቶስ እመኑኝ” ሲል በእውነተኛው የክርስቶስ ህማምና ትንሳኤ ላይ ተሳልቋል።

ከልጅነት እስከ ጎልማሳነት እጅግ መርዘኛ በሆነ የጎሳ አጥንት ስሌት ካድሬነት ብቻ ሳይሆን እጅግ ሥር በሰደደ የሰብእና ቀውስ ውስጥ የኖረው እና ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የዚህን ትውልድ በስሜት ፈረስ የመጋለብ እጅግ የወረደና አዋራጅ ፖለቲካዊና ሞራላዊ ቁመና ተጠቅሞ ዙፋኑን ከአሳዳጊዎቹ (ከህወሃቶች) የበላይነት በመንጠቅ አገርን ፈፅሞ ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ ምድረ ሲኦል ያደረገና ያስደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየ ሁሌም እንደሚያደርገው የቃላትና የተግባር ውህደት ውጤትና ፍፁም ቅዱስ የሆነውን የክርስቶስ ህማምና ትንሳኤ ልክ የሌለው የርካሽ ፖለቲካ ቁማሩ አካል አድርጎታል።

ከሦስት አሥርተ ዓመታት በፊት በጎሳአጥንት ስሌት ላይ በተመሠረተ ህገ መንግሥት በይፋ ተግባር ላይ የዋለው የጥላቻ፣ የመለያየት፣ የመጠላለፍና የመጠፋፋት ፖለቲካ ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የሰብእና ቀውስ በተጠናወተው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየ መሪነት በአስከፊ አኳኋን እንዲቀጥል የተደረገው የእኩያን አገዛዝ ተወግዶ እንደ ሰብአዊ ፍጡርና እንደ ዜጋ ተከብሮና ተከባብሮ መኖር የሚቻልባትን ዴሞክራሲያዊት አገር እውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ እንኳንስ ወዳጅን ጠላትንም የሚያስደምም ተጋድሎ እያደረጉ ያሉትን የነፃነት ፋኖዎችን/አርበኞችን/ጀግኖችን የጥፋት መልእክተኞች እና ራሱንና ግብረ በላዎቹን ግን ክርስቶሳዊያን አድርጎ ለማሳየት በመሞከር በህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በራሱ በፈጣሪ ላይም ተሳልቋል ።

መቸም መሪሩን እውነታ መጋፈጥ ሲያቅተን ወይም እንደ ሰው እና እንደ ዜጋ የአገር ባለቤት ሆኖ ለመኖር የሚያስችለንን ፍኖተ ነፃነትና ፍትህ ከለየላቸው ፀረ ሰላም፣ፀረ ፍትህና ፀረ ነፃነት ገዥ ቡድኖች ሥርዓት አስለቅቀን ከህዝብ፣ በህዝብና ለህዝብ የሆነ ሥርዓት እውን ማድረግ ሲያቅተን በዚያው በመጣንበት የድንቁርና እና መከራን የመለማመድ ክፉ ደዌ እንቀጥል ካላልን በስተቀር በፈጣሪ አምሳል በተፈጠረውና ክቡር በሆነው ሰብአዊ ፍጡርነታችን ብቻ ሳይሆን በራሱ በፈጣሪ ላይም እየተሳለቁ መቀጠላቸውን በትእግሥተኞነት ስም እያሳበቡ ማለፍ ትእግሥት ሳይሆን ቦቅቧቃነት (ልክ የሌለው ፍርሃት/የቁም ሙትነት ) ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል።

የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችም የትንሳኤውን በዓል ምንነት፣ ለምንነትና እንዴትነት በተመለከተ ያስተላለፏቸውን መልእክቶች በአትኩሮት ተከታትያቸዋለሁ። በመሠረቱ እያንዳንዱ ሃይማኖታዊ በዓል የየራሱ መነሻና ታሪክ ስላለው ይህንኑ ለትውልድ የማስተማሩ፣ የማስጨበጡና እንዲጠቀምበት የማድረጉ አስፈላጊነት አያጠያይቅም። የህማማቱንና የትንሳኤውን ምንነት፣ ለምንነትና እንዴትነት በትክክል መረዳታችንና ማመናችን የምናውቀው ግን ከአገራችን ግዙፍና መሪር እውነታ አኳያ ለማየትና ለመረዳት ስንሞክር

ነው።

በሌላ አገላለፅ ጥያቄው የምናስተምርበትንና ቁም ነገር የምናስጨብጥበትን አቀራረብና ይዘት ለዘመናት ከመጣንበትና ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፈፅሞ ከደመነፍስ እንስሳት በታች ያወረደንና እያወረደን ያለውን የጎሳ/የነገድ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞችን ሥርዓት የሚመጥን ነው ወይ ? እንጅ ስለ በዓሉ ሃያልነት ለምን ትናገራላችሁ ወይም መግለጫ ትሰጣላችሁ አይደለም ጥያቄው።

አዎ! ፈታኙ ጥያቄ “በዓላትን ወይም ሌላ አጋጣሚን እየጠበቃችሁ የምትሰጡት መግለጫ ወይም ስብከት የመከረኛውን ህዝብ መንፈሳዊና ዓለማዊ ህይወት ምስቅልቅሉን ያወጡትንና እያወጡት ያሉትን እኩያን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ነጋዴዎች ሴራና ጭካኔ የሚመጥን አይደለምና ይህንን ለማማስተካከል ፈቃደኞች ካልሆናችሁ እና ተግባራዊ አርአያነታችሁን ካላሳያችሁኝ ባዶ ስብከት አትንገሩኝ (do not just tell me, show me)” የሚል የትውልድ ፈተናን ለመወጣት በሚያስችል አቋምና ቁመና ላይ ነን ወይ ? የሚለው ነው ።

መከረኛው ህዝብ ከተለመደ የፖለቲካና የአስተዳደር ብልሹነት አልፎ እጅግ አስከፊ የግፍ ጭፍጨፋ እና የሁለንተናዊ የሰብአዊ መብት ጉስቁልና ሰለባ የሆኑባት አገር የሃይማኖት መሪና አስተማሪ በመጀመሪያው የአጥፊነትና የተጠያቂነት ረድፍ ላይ ያሉትን እኩያን ገዥ ቡድኖችን በግልፅና በቀጥታ ለመገሰፅ የሞራል ልእልና የሚገደው ከሆነ እና በፈጣሪ አምሳል ለተፈጠሩ ንፁሃን ኢትዮጵያዊያን የሚበጅ ሥርዓት እውን ለማድረግ መስቻል የትንሳኤ መገለጫ መሆኑን አስረግጦ ለመናገር የሚሳነው ከሆነ ስለ ምን አይነት ትንሳኤ እንደሚያስተምር ለመረዳት ያስቸግራል። ለምን? ቢባል ክርስቶስ ህማሙን የታመመበትን፣ ስቅላቱን የተቀበለበትን እና በመጨረሻም ሞትን አሸንፎ የተነሳበትን ሚስጥር የሰው ልጆችን ከመታደግ የተጋድሎ ምንነት ጋር ካላያያዝነውና ለዚህም ሰብአዊ ተፈጥሯችንና ባህሪያችን በሚፈቅድልን መጠን አስፈላጊውን አድርገን ካልተገኘን ተግባር አልባ የሆነ እናምናለን ባይነት ፈፅሞ የትም አያደርሰንምና ነው።

አለመታደል ወይም የፈጣሪ እርግማን ሆኖብን ሳይሆን ከረቂቅ የማሰቢያ አእምሮና ከብቁ አካል ጋር የተፈጠርንበትን እጅግ ድንቅ ዓላማ ከፈጣሪ እገዛ ጋር ለማሳካት ያልቻልን ደካሞች በመሆናችን ምክንያት ዛሬም ማነፃፀሪያ በማይገኝለት ፖለቲካ ወለድ የመከራና ውርደት ማእበል ውስጥ እየጎጎጥን የቃልና የተግባር ውህደት ውጤት ስለሆነው ትንሳኤ የተፃፉትንና የተነገሩትን ድንቅ ሚስጥራት እየጠቀስንና እያጣቀስን ከመናገርና ከመንገር አላለፍንም።

የእኛና የአገራችን ትንሳኤ የሚረጋገጠው የመከራና የውርደት ባሪያዎች ያደረገንን እና ጥንብ ነው እያልን የምንጠራውን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት ከፈጣሪ እገዛ ጋር አጥብቆ በመታገልና ወደ ተሻለ ሥርዓት በመሸጋገር እንጅ ድርጊት አልባ በሆነ እግዚኦታ፣ ፀሎትና እናምናለን ባይነት ከቶ አይሆንም። እንዲህ አይነቱን ወለፈንዲነት ፈቅዶ የሚቀበል እውነተኛ አምላክ የለም። እውነተኛው አምላክ ወዲ የሚቀበለው ተግባራዊ በሆነ እና ከመከራና ከስቃይ ወደ ትንሳኤ የሚያሸጋግረውን መንገድ ነው። አስፈላጊውን የአእምሮና የአካል ስጦታ የሰጠን ከፈጣሪነቱ እገዛ ጋር እንደ ሰው ሰውና እንደ ዜጋ የአገር ባለቤቶች እንድንሆን እንጅ ሁሉን ነገር ለእርሱ (ለፈጣሪ) እየተውን መከራ ሲጫነን እግዚኦ እና መከራው የቀለለልን ሲመስለን ደግሞ ራሳችንን ፃድቆች የምናደርግ ገልቱዎች (ደካሞች) እንድንሆን አይደለም።

እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝበትን የአሁኑን እኛነት ጨምሮ ከሦስት አሥርተ ዓመታት ፖለቲካ ወለድ የግፍና የመከራ ዶፍ በኋላም የትንሳኤን ምንነትና እንዴትነት የገዛ ራሳችንን ግዙፍና መሪር እውነታ በሚያሳይና በሚመጥን አቀራረብና ይዘት ለመግለፅ አልሆነልንም። ይህንን ግልፅና ቀጥተኛ ሂሳዊ አስተያየት እንደ ፈጣሪ አልባነትና የሃጢአት መንገድ አድርገው የሚቆጥሩ ወገኖች ቢኖሩ አይገርመኝም። ይጣመንም ወይ ይምረረን ትንሳኤን አስመልክቶ በሃይማኖት መሪዎች የተላለፈው መግለጫ (መልእክት) ለዘመናት መሬት ላይ የሆነውንና በአሁኑ ወቅት እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ እየሆነ ያለውን ግዙፍና መሪር እውነት ፈፅሞ አይመጥንም። የሃይማኖት መሪ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ? የሚል ጥያቄ ሊሰነዘር እንደሚችል እገምታለሁ። ለዚህ ያለኝ መልስ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ወገኑ የገዛ ወገኑ ፖለቲካ ጠለድ ጨካኝ ሰይፍ (የግፍ ግድያ) እና የቁም ሞት ሰለባ ሲሆን አስፈላጊውን (የሚችለውን ሁሉ) በማድረግ የማይታደግ የሃይማኖት መሪና ሰባኪ ስለ የትኛው መስዋእትነት፣ ሰማእትነትና ትንሳኤ ነው የሚሰብከንና እመኑኝ የሚለን? የሚል ነው ።

ለመሆኑ፦

· እጅግ ዘመን ጠገቡ፣ ግዙፉና መሪሩ ጥያቄ አምላክ በክርስቶስ አማካኝነት ወደዚህ ዓለም የመጣበት ፣ ሥጋ ለብሶ የተወለደበት ፣ ያስተማረበት፣ የፆመበት፣ በጥምቀተ ባህር የፈጣሪ ልጅነቱን ያገለፀበት ፣ ከስቅላቱ በፊት የቁም ስቃይ የተቀበለበት ፣ ለብልግና እና ለፍፁማዊ ሥልጣናቸው አደጋ እንደሆነ በሰጉ የዘመኑ ገዥዎች ወንበዴ ናቸው ከተባሉ ጋር በመስቀል ላይ የተሰቀለበት እና በመጨረሻ ግን ሞትን አሸንፎ የተነሳበት እጅግ ሰፊውና ጥልቁ ምስጢር የሰው ልጆች ድነትና ደህንነት ጉዳይ እንጅ አሜንና አናምናለን በሚል የመማልና የመገዘት ጉዳይ ብቻ ነው እንዴ?

 

· ይህንን የገዛ ራሳችንን ግዙፍና መሪር እውነታ ከፈጣሪ እገዛ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ ድርጊት አልባ የሃይማኖታዊ በዓል መግለጫ ( የመሃል ሰፋሪነት ስብከት) የት አደረሰን? የትስ ያደርሰናል?

· በአግባቡ አካፋን አካፋ ብሎ በመጥራት አገርን ምድረ ሲኦል እያደረጉ ያሉ እኩያን ገዥ ቡድኖች የሃይማኖታዊ በዓላትን እየጠበቁ ከሚደሰኩሩልን ዲስኩር አልፈው በንፁሃን ደምና የቁም ሰቆቃ የተጨማለቀ ማንነታቸውን ከክርስቶስ ህማም፣ ስቅለትና ትንሳኤ ጋር እያመሳሰሉ በንፁሃን አማኞች ላይ ሲሳለቁ ቢያንስ ነውር ነው ለማለት መሠረታዊ የሞራል አቅም ያላቸው የሃይማኖት ተቋም መሪዎችንና ሊቃውንትን ፈልገን ለማግኘት ያልቻልነው ለምንድነው?

 

· ለእኩያን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሽፋን ሰጭነት (አሻንጉሊትነት) ሲባል በአዋጅ ለተፈጠረው (ለተቋቋመው) አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተብየ ኮሚሽነርነት ተሰይሞ (ቅብአተ ብልፅግና ተቀብቶ) በማገልገል ላይ የሚገኝ የሃይማኖት ተቋም መሪ የሚያስተላልፈው የእንኳን አደረሳችሁና የመልካም ምኞት መግለጫ ምን ያህል ሚዛን እንደሚደፋ ለመረዳት አያስቸግርም እንዴ?

 

· አብይንና ካምፓኒውን (ፓርቲውን) በይፋ በማሞገሥና በማወደስ በንፁሃን የግፍ አሟሟትና የቁም ሰቆቃ ላይ የተሳለቁ የሃይማኖት አልባሳት ለባሽ የብልፅግና ካድሬዎችን እሹሩሩ የሚልና ከላይ በተጠቀሰው ኮሚሽን ተብየ አባል ለመሆን የተማፅኖ ደብዳቤ የፃፈ እና በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኗ ፣ በአገልጋዮቿና በተከታዮች ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የመከራ ና የውርደት ዶፍ ማስቆም ባይቻላቸውም እንኳ ትርጉም ያለው ሥራ ያልሠሩ የሃይማኖት መሪዎች በዓላትንና ሁኔታወችን እየጠበቁ በሚሰጡት መግለጫ ላይ ጥያቄ ማንሳት የሃጢአት መንገድ ይሆን?

 

· ሥልጣነ መንበሩ የእኛ ሆኗልና ደስ ይበልን የሚል አይነት እጅግ የወረደ አስተሳሰባቸውን በአደባባይ ሲነግሩን ህሊናቸውን ፈፅሞ የማይጨንቀው የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ነን የሚሉ ወገኖች ጋዜጠኞቻቸውን ጠርተው ለሰው ልጅ ድነት፣ ደህንነት፣ ነፃነት ፣ ፍትህ ፣ እኩልነት ፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ወዘተ ሲባል የተከፈለውን መስዋእትነትና በትንሳኤው የታተመውን ወርቃማ ሃይማኖታዊ እሴት እነርሱም እየኖሩት እንደሆነ አስመስለው ሲነግሩን ንፁሃን ወገኖች (ዜጎች) መግልፅ በሚያስቸግር ፖለቲካ ወለድ የመከራና የውርደት ዶፍ ሰለባዎች ሲሆኑ የት ነበራችሁ? ምን አላችሁና ምን አደረጋችሁ? አሁንስ ምን እያደረጋችሁ ነው? ነገና ከነ ወዲያስ? ብሎ መጠየቅን እንደ ድፍረትና ሃጢአት የሚቆጥር እውነተኛ አምላክ አለ እንዴ?

 

· አዎ እርግጥ ነውእንኳንስ እንደኛ አይነት ከጥቂቶቹ በስተቀር ህዝበ አዳሙ/ሔዋኑ በህሊና ቢስና እኩያን ገዥ ቡድኖች ምክንያት ልክ የሌለው ሁለንተናዊ የድህነት፣ የመከራና የውርደት ዶፍ ሰለባ በሆነበት አገር በአንፃዊነት በዴሞክራሲያዊ እሴቶችና በኢኮኖሚ በልፅገዋል በሚባሉ አገሮችም የወገንን እርዳታ የሚሹ የህብረተሰብ አባላት አሉና ሁሉም የሚችለውን የማድረጉ አስፈላጊነት አያጠያየቀንምና እኛም ይህንኑ ማድረግ ከተገቢም በላይ ተገቢ ነው። በተፈጥሮም ሆነ በሠርቶ አዳሪ ህዝብ ያልቸገራትን አገር የድህነትና የተመፅዋችነት መናኸሪያ ለምን ሆነች ብለው የሚጠይቁትንና የሚቃወሙ ወገኖችን ብቻ ሳይሆን የጎሳ/የነገድ አጥንት ስሌት እያሰሉ በንፁሃን ላይ የግፍ ግድያ ሲፈፅሙና የቁም ሰቆቃ ሲያደርሱ ቆመን እያየን ወይም የመከራና የውርደቱን ምንጭ ለማድረቅ ጥረት ሳናደርግ ምፅዋት እየወረወርንና እየለመን ስንት ዘመን ሆነን? ስንትስ ዘመን ነው በዚህ አይነት እጅግ አስከፊ የመከራና የውርደት አዙሪት ውስጥ እየጓጎጥን የምንቀጥለው? ከመከራና ከተመፅዋችነት ጋር በአሳፋሪ ሁኔታ የመለማመዳችን አሳፋሪ እኛታችን የሚታዘብ ዓለም መሳለቂያና ከንፈር መምጠጫ ሆነን የምንቀጥለው እስከየትና እስከመቸ ነው? ትንሳኤውን ትንሳኤያችን የሚያደርግ ተግባራዊ (የሚጨበጥ) እና ትውልድ ተሻጋሪ ተጋድሎ ሳናደርግ የሃይማኖት በዓላትንና ሌሎች አጋጣሚዎችን እየጠበቅን የምናዥጎደጉደው ስብከትና ዝማሬ የት አደረሰን? የትስ ያደርሰናል? ይህንን አይነት ወለፈንዲነት የሚሰማና የሚባርክ እውነተኛ አምላክ አለ ወይ? እንኳንስ የተሻለ ዛሬንና በጣም የተሻለ ነገን ልንፈጥር እንደ ሰው ሰው ሆነን እና እንደ ዜጋ የአገር ባለቤቶች ሆነን ለመኖር ያልሆነልን ለበዚህ ምክንያት አይደለም እንዴ?

 

 

የፈጣሪን እገዛ ሳይዘነጉ ከተገፉት ወገኖች ጋር ሆኖ ግፍንና ግፈኞችን በመቃወም ለሁሉም የሚበጅ ሥርዓተ ማህበረሰብን እውን ከማድረግና ዘለቄታነቱን ከማረጋገጥ የበለጠ የትንሳኤ መንገድና ዋስትና የለም።

ሁሉንም አይነት የሰብአዊና የዜግነት መብቶች በሚጨፈልቅ የእኩያን ገዥ ቡድኖች ሥርዓት ሥር ተለይቶ የሚከበር እውነተኛ የሃይማኖታዊ እምነት መብትና ነፃነት ፈፅሞ አይኖርም። ኖሮም አያውቅም። በዓል እየቆጠርን የምንሰጠው የእንኳን አደረሰንና የመልካም ምኞት መልእክት የዘልማድ ድግግሞሽ እየሆነብን በእጅጉ የተቸገርነውም በዚሁ ምክንያት ነው።

እናም ለዚህ ነው በአማራ ፋኖዎች እና ምክንያታቸውንና ዓላማቸውን ተጋርተው ተጋድሎ በሚያደርጉ ወገኖች ግንባር ቀደም ተሰላፊነት ህልውና፣ ነፃነት ፣ ፍትህ፣ እኩልነት ፣ መተሳሰብ፣ ፍቅር ፣ ሰላምና የጋራ እድገት የሚረጋገጥባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የሚያደርገውን ትግል ገንቢ በሆነ ሂሳዊ ድጋፍ መደገፍ የሞት ወይም የነፃነት ጉዳይ የሚሆነው ።

ፕሪቶሪያና ሃላላ ኬላ – ኤፍሬም ማዴቦ

ሃላላ ኬላ ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ አስደናቂና ውብ ቦታ ነው። ዳውሮ ዞን ውስጥ የሚገኘው ሃላላ ኬላ ስሙን ያገኘው ዳውሮን ከጠላት ለመከላከል ግንባታው በ16ኛው ምዕተ አመት ተጀምሮ በ18ኛው ምዕተ አመት አጋማሽ አካባቢ ካለቀውና ዳውሮን ዙሪያዋን የከበባትን ግንብ ስራ ካስጨረሰው ከንጉስ ሃላላ ነው። ዳውሮ ዳግማዊ ምኒልክ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ግዛት በተለያየ አቅጣጫ ሲያስፋፉ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት ግዛት አካል ያደረጉትና፣ እስክ 1883 ዓም ድረስ የራሱ ተከታታይ ነገስታት የነበሩት ቦታ ነው። ሃላላ ኬላ በሰው ሰራሹ ሃላላ ግንብ፣ በጫካና በውኃ የተከበበ ተፈጥሮ ውበትን እንካ ብሎ ያደለው አይን የሚማርክ ውብ ቦታ ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ጆግራፊ ስንማር የራሳችንን ውብና ማራኪ ቦታዎች ትተን፣ ቪክቶሪያ ፎልስ፣ ናይግራ ፎልስ፣ጎልደን ጌት ቢሪጅ፣ ቻይና ግንብ፣ ታጅማሃል ወዘተ እያልን የሌሎችን አስደናቂ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ውበት ስለምንማር ነው እንጂ፣ የራሳችን የሆኑ ሃላላ ኬላን፣ሐርር ግንብን፣ሰሜን ተራራ፣ባሌ ተራራ፣ሶፎኦማርን፣አጆራ ፏፏቴን፣ጢስ እሳትንና ላሊበላ፣ጎንደርና አኩስምን የመሳሰሉ ታይተው የማይጠገቡ ቦታዎች አሉን።

እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪና ጨዋ የሆነ ህዝብ የሚኖርባት የዳውሮ ዞን ውብት ምልክት የሆነቸውን የሃላላ ኬላን ስም በጥሩ ከሆነ በቀር በክፉ ማንሳት አይቻልም። ዛሬ ሃላላ ኬላን ይዤላችሁ የመጣሁት መታጠቢያ ቤት መሄድ ሲገባቸው ከነቆሻሻቸው ሃላላ ኬላ ሄደው በዚህች ውብና ታሪካዊ ቦታ ላይ አሳፋሪና ታሪካዊ ክህደት የፈጸሙትን ህወሓትን እና ብልጽግናን ለማንሳት ነው እንጂ፣ ሃላላ ኬላማ ምን ግዜም ሃላላ ኬላ ናት።

የፕሪቶሪያው ስምምነት 15 አንቀጾችና ብዙ ንዑስ አንቀጾች አሉት። ህወሓት ሥልጣን ላይ በነበረበት ግዜና ከሥልጣን ከተወገደም በኋላ በተለይ ከ2013-2015 ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰውን ይህ ነው ተብሎ የማይነገር በደልና ሰቆቃ ለሚያውቅ ለማንም ሰው የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹና በቅድሚያ ተግባራዊ መሆን የነበረባቸው የፕሪቶሪያው ስምምነት አንቀጾች ናቸው። የህወሓት ማን አለብኝነት የሚመነጨው ከዕብሪቱ ነው፣ የዕብሪቱ ምንጭ ደሞ የታጠቀው የጦር መሳሪያ ነው።

 

  • ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው
  • የህወሓት ኃይሎች ትጥቅ የሚፈቱበት (Disarmament)፣ከወታደራዊ ህይወት የሚላቀቁበት (Demobilization) እና ከማህበረሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበት (Reintegration) ሁሉን አቀፍ ፕሮግራም ይዘጋጃል
  • የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ ከ5 ቀን በኋላ የሁለቱ ኃይሎች (የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት) ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተገናኝተው የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት መንገድ ተወያይተው ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። ሁለቱ ኃይሎች ተገናኝተው ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ባሉት 10 ቀኖች ውስጥ ህወሓት ከባድ መሳሪያውን ሙሉ በሙሉ ይፈታል
  • የፕሪቶሪያው ስምምነት በተፈረመ በ30 ቀን ውስጥ ህወሓት ቀላል መሳሪያውን ይፈታል።
  • ሁለቱ ኃይሎች (የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት) ተነጋግረው ትግራይ ውስጥ ሁሉን አቀፍየሽግግር መንግስት ያቋቁማሉ

የፕሪቶሪያዉ ስምምነት የተፈረመው ጥቅምት 23,2015 ዓም ነው። አሁን ያለነው ሚያዚያ 2016 መገባደጃ ላይ ነው። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ህወሓት ህዳር 23 ቀን 2015 ዓም የታጠቀውን ትጥቅ (ከባድና ቀላል መሳሪያ) ሙሉ በሙሉ መፍታት ነበረበት። ሆኖም የህወሓት የክርስትና ልጆች የነብስ አባታቸው ህወሓት ትጥቅ እንዲፈታ ባለመፈለጋቸው የሀወሓት ወራሪ ሠራዊት በያዝነው ወር ራያ ገብቶ አንዳንድ ቦታዎችን በኃይል ተቆጣጥሯል። ከሰሞኑ ደሞ የትግራይ ክልል ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ህወሓትና ብልፅግና ወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ላይ የደረጉት ስምምነት ምን እንደሚመስል በይፋ ተናግረዋል።

ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓም በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማጆር ሹም ብርሃኑ ጁላና በህወሓት ከፍተኛ ወራደራዊ ባለሥልጣን ታደሰ ወረደ የሚመራ ቡድን ናይሮቢ ላይ ተገናኙ። እነዚህ ከአዲስ አበባና ከመቀሌ የሄዱ ባለሥልጣኖች ናይሮቢ ላይ መልካቸውን ነው ያሳዩን እንጂ ምን አይነት ስምምነት ላይ እንደደረሱ ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ያሳወቁት ነገር አልነበረም። ከጥቂት ቀናት የናይሮቢ ሠርግና ምላሽ በኃላ በጠሚ አቢይ አህመድ የሚመራ የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ቡድንና የህወሓት መሪዎች ሃላላ ኬላ ላይ ስብሰባ መቀመጣቸው ተነገረ። የሃላላ ኬላው ሰርግና ምላሹ፣ግብዣው፣መንቆለጳጰሱ፣ መተቃቀፉና መሸላለሙ መሃል አዲስ አበባ እስከሚገኘው ወዳጅነት ፓርክ ደረሰ። ሁለቱ ህዝብ ያፋጁት ከሃዲዎች ወዳጅነት ፓርክ ውስጥ ተቃቀፈው ተሳሳሙ። ልጇ እንደወጣ የቀረባት የትግራይ እናት፣ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ልጇ የተደፈረባት የአማራ እናት፣ ባሏ የሞተባት ሚስትና ልጆቹ የተበተኑበት አባትና የታንንክ፣የመድፍና የሌላም ከባድ መሳሪያ ጥይት በተከታታይ እንድ ዝናብ የወረደበት የአፋር ህዝብ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ምን ጉድ መጣ እያለ አለቀሰ።

ምንድነው ህወሓትና ብልፅግና ሃላላ ኬላ ላይ የተስማሙት? Politically correct መሆን የፈለገ ሰው እነሱ አልነገሩንም፣እኔም ቦታው ላይ አልነበርኩም ስለዚህ አላውቅም ሊል ይችላል። ይህንን ጥያቄ የብልፅግና ደጋፊዎችና የአቢይ አህመድ አምላኪዎች ቢጠየቁ መልሳቸው ጠሚ አቢይ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እንጂ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ስምምነት ላይ አይደርሱም የሚል ነው። እኛስ የፕሪቶሪያው ስምምነት ምን እንደሆነ የምናውቅ፣ ከሃላላ ኬላ በኋላ የፕሪቶሪያው ስምምነ የት እንደደረሰ የምናውቅና እንዲሁም ራያ ውስጥ ሀወሓት ያካሄደውን ወረራና በዚህ ሳምንት ታደሰ ወረደ ራያንና ወልቃይት ጠገዴን አስመልክቶ ያፈረጠውን እውነት በጆሯችን የሰማን ሰዎች፣የሃላላ ኬላው ስምምነት ምንድነው ተብለን ብንጠየቅ መልሳችን ምንድነው የሚሆነው?

ሃላላ ኬላ ላይ ህወሓትና ብልፅግና ያደረጉት ስምምነ በአገር ላይ የተሰራ ክህደት መሆኑን ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ የለብንም። ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓም ዕለተ ሰኞ ወደማክሰኞ ከመለወጡ በፊት 100% የታጠቀውን ትጥቅ መፍታት የነበረበትና ሰራዊቱም መበትን የነበረበት ህወሓት በያዝነው ሚያዚያ ወር (2016) አማራ ክልል ገብቶ በጦርነት ቁልፍ ቦታዎችን መቆጣጠር እንዲችል መንገድ የጠረገለት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይሆን የሃላላ ኬላው ክህደት ነው። ህወሓት ትጥቁን ሳይፈታ የፌዴራል መንግስት በሌለበት ቦታ ህወሓቶች ብቻ ተሰብስበው ህወሓት ብቻ ያለበትን የሽግግር መንግስት እንዲመሰርት ያደረገው የሃላላ ኬላው ክህደት ነው፣በሌላ በኩል ደሞ ህወሓት አገርን ማሸበር እንዲችል የልብ ልብ ከሰጠው ሙሉ ትጥቅና ከ250ሺ በላይ የታጠቀ ሰራዊቱ ጋር ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ እንዲሰረዝ ያደረገውም የሃላላ ኬላው ክህደት ነው።

የሃላላ ኬላው ስምምነት ከተደረገ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የክልል ልዩ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው የሚል ህግ ያወጣው የጠሚ አቢይ አህመድ መንግስት ለምንድነው ህጉ ወጥቶ ሳይውል ሳያድር አማራን ትጥቅ ለማስፈታት ጦር ይዞ አማራ ክልል የዘመተው? የጠሚ አቢይ መንግስት በአንድ በኩል ከአማራም ከፌዴራል መንግስትም ጋር ፊት ለፊት ጦርነት የገጠመውን ህወሓትን በአደባባይ እየሸለመ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ያደረገውን የአገርህን አድን ጥሪ ተቀብሎ ኢትዮጵያን ከአደጋ ካዳነው ከፋኖና ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር ጦርነት ውስጥ ለመግባት የቸኮለው ለምንድነው?

 

በአንድ ወቅት ጠሚ አቢይ አህመድና የጦር መሪዎቻቸው አመድ አደረግነው ብለው የፎከሩበት ህወሓት ከሞት እንዲነሳና ከዕብሪቱና ከሙሉ ትጥቁ ጋር ህወሓት ሆኖ እንዲቀጥል ከሆነ የተፈለገው፣ ያ ሁሉ የፌዴራል ወታደር፣ ያ ሁሉ የአማራና የአፋር ወጣት ለምን ሞተ? ለምንስ የአገር ኃብት በከንቱ ባከነ? ባጠቃላይ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ከፍታዋ መመለስ የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው ብለው የተናገሩት ጠሚ አቢይ አህመድ፣ እቺኑ ኢትዮጵያ ጠላት ብሎ ፈርጆ የወጋት ህወሓት እስካፍንጫው የታጠቀውን መሳሪያ እንዲፈታ ያልፈለጉት ለምንድነው?

የአገር መከላከያ ሠራዊትን በተኛበት ያረደ፣በቅርብ ግዜውም በሩቁም የኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ የጦር ወንጀል በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸመውና፣ የኢትዮጵያን እንደ አገር መቀጠል ትልቅ አደጋ ላይ ጥሎ የነበረው ህወሓት፣ ለእንደዚህ አይነት ክፋትና ዕብሪት ያበቃውን ትጥቅ ሳይፈታ መንግስት መስርቶ እንደገና ትግራይን እንዲመራ የተደረገው ለምንድነው? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ያለው የሃላላ ኬላው ስምምነት ላይ ነው። ይህ ስምምነት ነው አማራን የህልውና ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው፣ ይህ ስምምነት ነው ህወሓት አማራ ክልል ገብቶ አላማጣንና አካባቢውን እንደገና የጦርነት ቀጣና እንዲያደርግ የፈቀደለት። የሃላላ ኬላው ስምምነት ነው ታደሰ ወረደ ሜዲያ ላይ ወጥቶ ወልቃይትና ራያ ላይ የትግራይ አስተዳደር ይመሰረታል እንዲል ያበቃው። የሃላላ ኬላው ስምምነት ነው ከህወሓት ጋር በተደረገው የሁለት አመት ጦርነት ለኢትዮጵያ አጋር የሆኑ ኃይሎች ተክደው ጭራሽ እንደ ጠላት እንዲታዩ ያደረገው።

ለምንድነው ብልፅግና እና ህወሓት ፕሪቶሪያን ትተው ሃላላ ኬላ ላይ ሌላ ስምምነት የተስማሙት? ከ1966ቱ አብዮት በኋላ ህወሓቶች ጫካ ገብተው የትግል ማኒፌስቷቸውን ሲጽፉም ሆነ ታጣቂዎቻቸውን የፖለቲካ ትምህርት ሲያስተምሩ ጠላት ነው ብለው የፈረጁት አማራን ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ በነበረበት 27 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ በማንነቱ ከፍተኛ በደል የደረሰበት የአማራ ህዝብ ነው። በሰኔ ወር 2013 ዓም ህወሓቶች ልኩን እናሳየዋለን ብለው ውጊያ የከፈቱት በአማራ ህዝብ ላይ ነው። የማይካድራ፣የቆቦ፣የጭና በቅርቡ ደሞ መርዓዊ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ህዝብ ላይ ነው።

ባለፉት ሃምሳ አመታት የኦሮሞ ልህቃን የኦሮሞ ናሺናሊዝምን ሲገነቡ ገዝቶናል፣ረግጦናል፣ጨቁኖናል ብለው እንደጠላት የተመለከቱት አማራን ነው። ደርግ ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ በነበሩት የመጀመሪያው ሁለትና ሦስት አመታት ያለምንም መከልከል አርሲ፣ሐረርጌና ወለጋ ውስጥ በግፍ የተገደሉት የአማራ ተወላጆች ናቸው። ጠሚ አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቤዎች በጅምላ የተጨፈጨፉትና አሁንም በግፍ እየተገደሉ ያሉት የአማራ ተወላጆች ናቸው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት አዲስ አበባ አትገቡም እያለና ከአውቶቡስ ላይ እያስወረደ የሚያንገላታው የአማራን ተወላጆች ነው። ባለፉት ሦስት ወራት አዲስ አበባ ውስጥ በጅምላ የታሰሩትና አሁንም በመታሰር ላይ ያሉት የአማራ ተወላጆች ናቸው። እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የተለያዩ ወንጀሎች በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት ደሞ ህወሓት፣ ኦነግና ብልፅግና ወይም የእነዚህ ኃይሎች ጥምረት ነው። የሃላላ ኬላውን ስምምነት የተስማሙትም ከእነዚህ ሦስት ኃይሎች ውስጥ ሁለቱ ናቸው።

የኦሮሞ ልህቃንና የትግራይ ልህቃን የዛሬዋን ኢትዮጵያ በተመለከተ የሚጋሩት ትልቅ እሴት አለ፣ ይህ እሴት የብሔር ፖለቲካ ነው። ለሁለቱም ልህቃን ኢትዮጵያ የሚለው ስም የሚዋጥላቸው የብሔር ፖለቲካ እስከቀጠለና የሁለቱን ልህቃን የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅምና ፍላጎት ተራ በተራ እስካስጠበቀ ድረስ ብቻ ነው። የብሔር ፓለቲካና የዚህ ፖለቲካ መሠረት የሆነው ህገመንግስት ሳይሸራረፍ መከበር አለበት የሚለው አቋም ደሞ ብልፅግናዎችም ደረታቸውን ነፍተው የሚናገሩት አቋም ነው። እነዚህ ሁለት ኃይሎች የብሔር አጀንዳቸውን ኢትዮጵያ ላይ ተግባራዊ ማድረግና ኢትዮጵያ እነሱ በፈለጉት አቅጣጫ ብቻ እንድትሄድ ይፈልጋሉ። ትናንትም፣ዛሬም ነገም ይህ እርኩስ አላማቸው ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት ነው ብለው የሚያስቡት የአማራን ማህበረሰብ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሓቶች ተቋማዊ መልክ የሰጡት የብሔር ፖለቲካ የትግራይና የኦሮሞ ልህቃንን ከየትኛውም የኢትዮጵያ ልህቅ በተለየ መልኩ ያቀራርባቸዋል። ይህ ደግሞ ከህወሓት ጋር በተደረገው ጦርነት፣ በወልቃይት ጠገዴ ጥያቄና በቅርቡ የኦሮሞ ኃይሎች የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለመከፋፈል ባደረጉት ጥረት በግልፅ የታየ ሃቅ ነው። የብሔር ፖለቲካን፣ የብሔር ፌዴራሊዝሙንና ባጠቃላይ ዛሬ በስራ ላይ ያለውንና ሁለቱ አብረው የጻፉትን ህገ መንግስት ለማስቀጠል የትግራይና የኦሮሞ ልህቃን እጅና ጓንት ሆኖ መስራታቸው አይቀርም። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይና የኦሮሞ ልህቃን በአማራ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፣ሁለቱም አማራ ትንሽ ሆኖ ማየት ይፈልጋሉ፣ ደግሞም ከሃላላ ኬላው የብልፅግና እና የህወሓት ስምምነት በኋላ በግልጽ እንደታየው እነዚህ ሁለት ኃይሎች ፀረ-አማራ ግንባር ከመፍጠር የማይመለሱ ናቸው። ይህንን ደሞ የራሳቸው በተለይ የብልፅግና በለሥልጣኖች ሳይደብቁ ተናግረዋል። After now its all about connecting the dots.  እርግጠኛ ነኝ ነጥቦችን ማገናኘት የሚችል ሰው የፕሪቶሪያው ስምምነት ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተጥሎ ሃላላ ኬላ ለምን እንደተፈለገ ለማወቅ ግዜ የሚወስድበት አይመስለኝም።

ከHigh School ጀምሬ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ ተከታትያለሁ። ያለፉት 30 አመታት ህይወቴ ከፖለቲካ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነበር። ባለፉት 10 አመታት ደሞ ሙሉ ህይወቴን ለኢትዮጵያ ፓለቲካ ሰጥቻለሁ። እነዚህ አጋጣሚዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማን ማነው የሚለውን በሚገባ እንድገነዘብ ረድተውኛል። በተለይ ከ2010 ዓም መጨረሻ እስከ ግንቦት 2015 ድረስ በነበሩት 5 አመታት አገር ውስጥ ሆኜ ከአገር መሪ፣ከከፍተኛ የክልል ባለሥልጣኖች፣ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ከሲቪክ ድርጅት መሪዎች፣ ከወጣቶች፣ክሴቶችና ከተለያዩ ምሁራን ጋር በተደጋጋሚ የመገናኘት ዕድል አግኝቻለሁ። ከዚህ ቀደም በጻፍኳቸው፣ በዚህ ጽሁፍና ወደፊትም በምጽፋቸው ጽሁፎች ላይ የሚንጸባረቁ ብዙ ህሳቦች ከዚህ የረጂም ግዜ ልምድ የሚመነጩ ናቸው። እንዲህ ሲባል ግን ከልምድ የሚመነጩ ናቸውና እንዳለ ውሰዷቸው ወይም ሁሉም ትክክል ናቸው ማለት አይደለም። አንድ ነገር ግን ደፍሬ መናገር እችላለሁ፣ ህወሓትና ብልፅግና አማራ ላይ ያነጣጠረ ግዜያዊ ጥምረት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይህንን ለማለት የደፈርኩት ብልፅግና እና ህወሓት ሃላላ ኬላ ላይ ከተገናኙ በኋላ እንዳይሆን የተደረገውንና እየሆነ ያለውን ክስተት ከተመለከትኩ በኋላ ነው።

ህወሓቶች ተንኮለኞች ናቸው፣ ምንም ነገር ላይ ሲደራደሩ የራሳቸውን እቤታቸው አስቀምጠው በሌላው ድርሻ ላይ ነው የሚደራደሩት እንጂ፣ የነሱ የሆነውን ለድርድር ይዘው አይመጡም። ከብልፅግና ጋር ስምምነት ላይ ቢደርሱም ስምምነቱ እነሱን ወደፊት አጉልቶ የማያመጣ ከሆነ ግዜ ለመግዣ የሚሆን ሃሳብ ይዘው ይመጣሉ እንጂ ሰጥቶ መቀመል (Compromise) የሚባል ነገር አያውቁም። የብልፅግና አሸሼ ገዳሜዎች ግን እንደ በሬው ሰርዶ ሰርዶውን እንጂ ገደሉን በጭራሽ አያዩም። ደሞም ህወሓቶች ብልፅግናዎችን በሚገባ ያውቋቸዋል . . .  ወልደው፣ኮትኩተው ያሳደጓቸው እነሱ ናቸዋ! ብልፅግናዎች ህወሓቶችን በፍጹም እንደማያውቋቸው ወይም ምንግዜም እንደ ክርስትና አባታቸው እንደሚመለከቷቸው ግና 3 ዙር ከህወሓት ጋር የተዋጋነው ጦርነት፣ከጦርነቱ በፉት የነበሩት ሁለት አመታትና የሃላላው ኬላው ስምምነት በግልጽ አሳይቶናል።

ስለዚህ ብልፅጋና እና ህወሓት ፀረ-አማራ ጥምረት ፈጥረው መንግስት ቢመሰርቱም፣ የኦሮሞ ልህቃንን በተመለከተ ጥምረቱ የሚዘልቀው ከዚህ በፊት ኦፒዲኦና ህወሓት በተጣመሩበት መልክ ሆኖ የጥምረቱ መሪ ኦሮሞ ከሆነ ብቻ ነው። ነገር ግን ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ህወሓት የሁለት አመቱ ጦርነት ያጎበጠው ጀርባው ቀና እስኪልለት ድረስ ከብልፅግና ጋር ተስማምቶ ሊሰራ ይችላል፣ የነሱ ሚና ሁለተኛና ሶስተኛ ሆኖ ግን ከብልፅግና ጋር ለዘለቄታው በፍጹም አይቀጥሉም። ለዚህ ነው ብልፅግና እና ህወሓት አማራ ላይ ቢጣመሩም ጥምረቱ ግዜያዊ ነው ያልኩት። እዚህ ላይ የሚያሳዝነው ግን ሁለቱ ዝሆኖች ሲጣሉ የሚጎዳው ሳሩ ነው እንደሚባለው፣ የህወሓትና የብልፅግና የፖለቲካ እሹሩሩ ብልጭ ድርግም እያለ በቆየ ቁጥር የምትጎዳው አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ስለዚህ የብልጽግናን እና የህወሓትን ጥምረት. . . . . ህወሓቶች ባበዱ ቁጥር ልጆቹ ላይ የጥይት ዝናብ የሚወርድበት የትግራይ ህዝብ፣የሃላላ ኬላው የህወሓትና የብልፅግና ስምምነት የህልውና አደጋ ውስጥ የከተተው የአማራ ህዝብ፣ምንም ጥቅም ላያገኝ ነገር በቃኝን የማያውቁ ልጆቹ በየቀኑ በሚሸርቡት የፖለቲካ ሴራ እንደ ገና ዳቦ ከላይም ከታችም የሚቃጠለው የኦሮሞ ህዝብና፣ የኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል አደጋ ውስጥ በገባ ቁጥር የወደፊት ዕጣው ምን እንደሆነ እንኳን በውል የማያውቀው የደቡብ ኢትዮጵያ፣የጋምቤላ፣ የአፋርና የሱማሌ ህዝብ፣ አንድ ላይ ሆነው ለህወሓትና ለብልፅግና ዕብደት ፍቱን መድኃኒት መፈለግ አለባቸው። እንዲህ አይነቱ አንድነትና እንዲህ አይነቱ ጥምረት ብቻ ነው ትግሬውንም፣ አማራውንም፣ ኦሮሞውን እና የደቡብ፣ የምስራቅ፣የሰሜን ምስራቅና የምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝብ ሠላም፣ መረጋጋትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መበት መከበር ማረጋገጥ የሚችለው። እንደዚህ አይነቱ ትብብር ብቻ ነው ብልፅግናን አስገድደን ሁላችንም እናታችን ብለን የምንጠራትን ኢትዮጵያን በጋራ መፍጠር የሚያችለን !!!

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com )

 

 

የትግሬ አዲስ አጀንዳ…

የትግሬ አዲስ አጀንዳ…

“…የፕሪቶሪያው ውል የተግባር መርሀ ግብር ላይ የራያንና የጠለምትን ጉዳይ እስከ ግንቦት 30/2016 ዓም የወልቃይት ጠገዴን ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓም ለመጨረስ ስምምነት ፈጽመን ወደ ሥራ ገብተናል። (ታደሰ ወረደ)

“…ይህ ዛሬ በድምፂ ወያነ የተለቀቀው ዜና የሳይበሩን ዓለም እንዲሞላው ተደርጓል። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከብልፅግና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ጋር በመሆን ስለ ሌላ ዙር ጦርነት ዝግጅት፣ ስለ ሌላ ዙር የይግሬና የዐማራ መከራ፣ ስለ ሌላ ዙር የጅምላ ብሔራዊ መርዶ ዝግጅት ጽፈዋል።

“…አገዛዙ ይሄ ክረምት እስኪያልፍለት ድረስ የዐማራው ትኩረት ትግራይ ብቻ እንድትሆን አቅዶ እየሠራ ነው ባይ ነኝ። ጦርነቱን በማጓተት ስትራቴጂ አድርጎ እየሠራ ነው። የትኩረት አቅጣጫን በማስቀየር በተለይ ይህችን ክረምት እንደምነም የፋኖን ትኩረት ወደ ራያና ወልቃይት በማዞር ለሚመጣው በጋ በድሮን እና በከባድ መሣሪያው ለመጠቀም ያስባል። ለማንኛውም ፋኖ ለሁለቱም ከወዲሁ መዘጋጀት ይኖርበታል ባይ ነኝ። በተለይ ትኩረቱን መንግሥት ላይ አድርጎ ለ4ኪሎ መዋጋት አለበት። ወያኔ እንደሆነች ዛሬ ብትገባ ነገ በዐማራው መነጠቋ አይቀርም። ኦሮሙማው አያዛልቃትም የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

“…የብአዴንን ዝተት መግለጫ፣ የተመስገን ጥሩነህ ዛቻ፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ ሚንስትር ለገሰ ቱሉን ቱሪናፋ ቀደዳ፣ ከመቀሌ ከመሴ፣ ከመቀሌ ደብረታቦር በሲሚንቶ ጫኝ መኪና ውስጥ መትረየስ፣ ቦንብ ለፋኖና ለሸኔ ሊላክ ሲል ተያዘ ወዘተ የሚለው የማደናገሪያ ዜና አይሠራም። ትግሬ ከኦሮሞ ጋር ሆኖ እየፎከረ ነው። በራያ ዘረፋው እንደተጧጧፈ እየተሰማ ነው። የጁላ ጦር የገበሬ ቤት በእሳት እየለኮሰ እያነደደ ነው ተብሏል። መፍትሄ ጨካኝ መሆን ብቻ ነው።

  • በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ…
  • እንመጣለን ነው የሚለው ትግሬው።

“…መከላከያ ሠራዊቱን አቁሞ ነው የሚያጠጣው። ዱርዬ የሚለው ዐማራን ነው የዐማራን ፋኖ። ህጻናት፣ ሴቶች፣ ባንዲራ ይዘን አይደለም የምንመጣው። ይዘን የምንመጣው ምን እንደሆነ በሁሉ ዘንድ ይታወቃል ነው የሚለው። አይደለም ዱርዬው የዐማራ ፋኖ መከላከያ ራሱ ያውቀናል ነው የሚለው።

“…አንዳንድ ምስኪን ዐማሮች በትግሬ ነፃ አውጪ በህወሓት ካድሬዎች ምላስ ሲደነዝዙ አያለሁ። ህወሓት በሕይወት እያለች አበደን ቃለ ለሰማይ ቃል ለምድር ዐማራና ትግሬ አይታረቁም። አይቀራረቡም።

“…ትግሬ ደም የፈሰሰበት ቦታ በበጋ አይዋጋም። ሰይጣኑ ክረምት ጠብቆ ወይ ዝናብ ጠብቆ ነው ለደም ግብር የሚገፋው፣ የሚነዳው። አሁን ክረምቱ መጥቷል። ትግሬም ቀሪ ሕዝቡን፣ ወጣቱን መገበር አለበት። ለዚያ ነው እንዲህ የሚሠራ የሚያደርገውን የሚያሳጣው።

“…በሱዳን ያለው የማይካድራው ጨፍጫፊ አራጅ ሳምሪ ቡድን ወደ ሁመራ፣ ወደ ወልቃይት ይንቀሳቀሳል። በሽሬ በኩልም የሚመጣ አለ። ወልቃይት የሚገባም አለ። መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቋል። ስዩም ተሾመ በግልፅ ተናግሯል። ቀለብም እንደጉድ በርዳታ መልክ ገብቷል። በጀትም በቢልዮን የሚቆጠር ብር ለህወሓት ከኦሮሙማው ተለግሷል። የሚቀረው በሰሜን ጎንደር፣ በወልቃይትና በሰሜን ወሎ ከዐማራ ጋር መፈሳፈስ ነው።

“…አሁንም ሌላ ዙር ሺ ቆማጣ፣ ሚልዮን አስከሬን፣ ውድመት፣ እሪታ፣ ኡኡታ፣ ቁቁታ ተዘጋጅቷል። አቢይ አሕመድ አያስጥልህም። የማትኖርበት ቤት አታምሽ። የትግሬንም የዐማራንም የመከራ ዘመን በኦሮሙማው ሴራ አታርዝም።

“…ዐማራ ዱርዬ የተባልከው ፋኖ አትራራ፣ እንደ እስራኤል ፍፁም አረመኔ ጨካኝ ቆራጥ መሆን ነው የሚጠበቅብህ። ዐማራና ትግሬ አንድ ሕዝብ ነው የሚለውን የሂዊ ሰበካ ለጊዜው ኢግኖር ግጨው።

 

• ሲያበሽቁ እኮ በማርያም… ዘመዴ

 


 

Share