ይድረስ በአገር ውስጥም ሆነ ከውጭው አለም በክፋት ለምትራወጡ ወገኖቼ። መቼስ ወገን ናችሁና እንኳን ለፈረንጆቹ ገና በአል አደረሳችሁ በውጭው ላላችሁት።
እንዲህ ነው ጉዳዩ!
ያለኝ መልእክት በጣም አጭር ነውና በጥሞና አድምጡኝ። እስካሁን ኢትዮጵያዊነትን ሆን ብላችሁ ከውስጥና ከውጭ ገዝግዛችሁ አልተሳካላችሁም። ወደፊትም አይሳካላችሁም። ይህን ቅን መሪ ቆም ብላችሁ መርምሩ። እንደናንተ ሙዋርተኛና ክፉ ሰው አይደለም። የወጣበትን መንደር ለይቶ የሚያውቅ፣ የወደፊቱን አርቆ የሚመትር ጀግና ሰው ነው ያገኘነውና እባካችሁ ቆም በሉና አስተውሉ። ይህ መልእክት በተለየ ለአማራውና ዖሮሞ አክራርያን ነው። ወያኔዎቹን አይመለከትም። እናንተን ፍርዱን የሚሰጣችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው። የሰው እርጉሞች። ምቀኞችና ሰብአዊነት የጎደላችሁ ክፉዎች። ከ 28 አመት በሁዋላም ትክክል ነን ባዮች። አገራችንን ምስቅልቅሏን አውጥታችሁ ዛሬም አለኛ በቀር መዳኛ የላትም የምትሉ መካሪ ያጣችሁ ደመነፍሶች። ፈጣሪ ይቅር አይበላችሁ እንኩዋንስ ወገን።
አክራርያን ወገኖች። በጣም ግራ የሚገባኝ ብዙዋቻችሁ የውጭውን አለም አይታችሁዋል። ለምን የሰለጠነ የአክራርያን ፓርቲ በህብረት መስርታችሁ በጋራ አቢይን አትሞግቱም? በሀሳብ ሞግቱኝ እኮ ነው የሚሉት ሰውዬው። በራሳችሁ ቁሙና ሞግቱ። ወያኔ ስር መርመጥመጡ ይቁም ። እራሳችሁን ቻሉ እስቲ። በፌዴራሊስት ስም ከነሱ ጋር ከመርመርመጥ ለምን የራሳችሁን የጋራ ሸንጎ መስርታችሁ አትሞግቱም? ከተጫረሳችሁም እርስበርስ አድርጉት። የደሀውን መስጊድና ቤተክርስትያን አትንኩ ወይም አባሪና ተባባሪ አትሁኑ። የደሀውንም ደም በከንቱ እንዲፈስ አታድርጉ ወይም በቀጥታም ይሁን ተዘዋዋሪ አትተባበሩ። ጀግና ከሆናችሁ ማ ምን እንደሆነ ትተዋወቃላችሁና እዚያው ተጨራረሱ። የኢትዮጵያን ህዝብ ለቀቅ አድርጉት። በዚች አመት ተኩል፣ ሰው ተዘቅዝቆ በተሰቀለባት አገር እነሆ ሳተላይት ወደህዋ መጠቀች። የኡትዮጵያ አምላክ አያሸልብም የምንለው የዋዛ አይደለምና። ይህንኑም ደግሞ አቃቂር የምታወጡትን ታዝቤአለሁ። ሳተላይቱ ከሱሉልታም ትሁን ከእንደርታ ለታዳጊዎች ሌላው ቢቀር ፖዘቲቭ ኢነርጂ ነች። ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም በላይ ነው። የሚያምርብንም እንደዛ ስናስብ ነው። ክብሩ ይስፋና አቶ ለማም ይህው ወደ ህሊናው ተመለሰ ማለትን ሰማሁ። እውነት ከሆነ ደስ ይላል ። እንደሚመለስም ተንብዬ ነበር። እናንተ አክራሪ ገልቱዎች አሳስታችሁት እንጂ አጀማመሩ መልካም ነበር።
ውድ አክራርያን!
ሁሉን ሞከራችሁ። ኢትዮጵያ እንዲህ እንዳሰባችሁት የምትከስም የዋዛ አልሆን አለችባችሁ። እንግዲህ ምን ቀራችሁ? እውነት ህዝቡ መተላለቅን ነው ወይስ አብሮ ድህነቱን መጋፈጡ ይቀለዋል? እንደናንተ ፖለቲካውን ጥርሴን ባልነቅልበትም እንደው ከላይ ሳየው የምትከተሉት መንገድ በፈጣሪም ይሁን በሰው ዘንድ አያዋጣም። እስቲ ሰከን በሉ። እስከመቼስ እነዚህ በቁም ያሸለቡ ወያኔዎች ይጯወቱባችሁ? በተለይ የሚያቃጥለው የዖሮሞ ምሁራን ተብዬዎች ዬትኛውን ምሁር አክብረው ያውቃሉና ነው መቀሌ ኮንፈረንስ እየሄዳችሁ ስንት አስርተአመታት በህዝባችን የቀለዱትን ሰዎች በስመ ሳይንሳዊ ኮንፈረንስ ስታሽቃብጡ የሰነበታችሁ? ምን ደህና ነገር ከነዚህ ሰዎች ጠብቃችሁ ነው? የራሳቸውን ሰዎች መተንፈሻ ኦክሲጂን ከልክለው ህዝቡ እንዳይሰበሰብ እያገዱ፣ ጀግና የትግራይ ወጣት ተቀናቃኞች ብቅ እንዳይሉ እየኮረኮሙ እያያችሁ ዬትኛውን የሰላምና የዴሞክራሲ ኮንፈረንስ ነው የምትካፈሉት? ደግነቱ የተካፈሉት ጥቂት መሆናችሁ መልካም ነው።
በመጨረሻ የምለው አንድ ነገር ነው። ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም በላይ ነው። 28 ,አመታት ከራሳችን ጎሳ አልፈን ለሌላው እንዳናስብ ተደርጎ የትም አልደረሰንም። እስቲ እኒህን ቅን ሰውዬ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ሀሜቱንም ሁሉ ሰምተናል። በጭራሽ አለመሆኑን የምታውቁት ከውስጥ የውስጥ ባላጋራ እንኳ ታኮ ሆኖባቸው ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በዝምታ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው ዶር አቢይ። ሌላው ሳላደንቀው የማላልፈው የአቶ ደመቀ መኮንን ጽናትና ብቃት ነው። በጣም አስገራሚ ጽኑ መንፈስ ያላቸው ትልቅ ሰውዬ ናቸው። እንደኔ ምኞት ቢሆን ዶር ብርሀኑ ነጋ፣ ዶር ኦባንግ ሜቶ ከብልጽግናው ፓርቲ ቢቀላቀሉ አገራችን ታላቅ እርምጃ ትሄዳለች ብዬ አስባለሁ። እናንተ የህዝበ ቁጥራችሁን ከፍታ አይታችሁ ልባችሁ በእብሪት ለተወጠረ አክራርያን የአዲሱ አመት ምኞቴ ወደስልጣን መንበሩ እንዳትደርሱ ከልብ እመኛለሁ። ይልቅ የሚያምርባችሁ የምታከሩበትን የተነደፈ ፖሊሲ ይዛችሁ፣ ሰው ሰው የሚሸት ተጻራሪ ፓርቲ በግንባር ፈጥራችሁ አዲሱን ብልጽግና ወይም ሌሎችን በሀሳብ ሞግቱ። ለሀሳብ ሙገታው ደግሞ ካልሆነላችሁ ከላይ እንዳልኩት እርስ በርስ እየተመራረጣችሁ ተጫረሱ። ከህዝቡ ጫንቃ ላይ ግን ውረዱ። አላማረባችሁም። ይህው ነው። ድከም ቢለኝ እንጂ ትሰሙኛላችሁ እንኳ ብዬ እራሴን አላጃጅልም። የበአል ምኞቴ ስለሆነ በአክብሮት ይድረሳችሁ።
መልካም ገናና የፈረንጆች አዲስ አመት!