የአቋም መግለጫ – ኢትዮጵያን የዘመናችን ጽንፈኞችና ጎሰኞች እንዲያፈርሷት አንፈቅድም!

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!

ኢትዮጵያ ፈሪሃ እግዚአብሔርን የተላበሰች፤ የሰውን የማትመኝ፤ የራሷን የማታስደፍር በመሆኗ ምቀኛና ጠላቷ በዝቷል። በክፋት የታበዩ ጠላቶቿ ውቅያኖስ ተሻግረው፤ ድንበሯን ጥሰው ሊቆጣጠሯት፤ እምነቷን ሊአስቀይሯት፤ ታርኳን ሊበርዙ፤ የባህል ትውፊቷን ሊአጠፉ ሲደግሱ ኖረዋል። የግራኝ መሐመድ ሃይማኖትን የማጥፋት ዘመቻ፤ የፋሽት ኢጣልያና የሶማሊያ ወረራ፤ የባድሜ ጦርነቶች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተደርጉ ሴራዎች ነበሩ። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ጠላቶቿ ታክቲክ ቀይረው ክሃዲ ልጆቿን ተጠቅመው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዘመቻ ጀምረዋል።

ኢትዮጵያን የምናውቃት ለተሰደዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች መጠጊያ የሰጠችና ለእምነቱ በር የከፈተች ሃገር መሆኗን እንጅ በሃይማኖት መካከል ጥላችን በመፍጠር ሰላምን በመንሳት አይደለም። የንብዩ መሐመድ ምስክርነት የሚአሳየን እስልምና ወደ ጦርነት ቢገባ ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ እንዳትነካ የሰበከውን ሐቅ ነው። ይህን ክብር ለኢትዮጵያ ያጎናጸፏት ሳይማሩ የተማሩ፤ የአዳምን ልጅ በሰውነቱ ተቀብለው ያስተዳደሯት ፊደል ያልቆጠሩት ወገኖችን ናቸው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሳና በሃይማኖት ሳይለያይ ወራሪን አሳፍሮ ሃገሩን አስጠብቋል።የተሸነፉ ጠላቶቹ ኢትዮጵያን የማተራመስ፤ የመበተንና የመቆጣጠር ሕልማቸው ግን አልቆመም። የዘር ፖለቲካን እያራገቡ፤ የእምነት ልዩነትን እያጦዙ፤ ጽንፈኞችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ማዳካምና  የማፈራረሱን ሴራ ተያይዘውታል።  አሁን በቅርቡ በዶዶላ፤ ናዝሬት፤ ባሌ ሮቤና ሐረርጌየተከሰተው ጎሳና ሃይማኖትን የማጽዳት ዘመቻ የውጪ ሃይሎች አጀንዳ አንዱ አካል እንደሆነ ይታመናል። ጭፍጨፋው አስከፊና አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ተረድተው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለሃገራቸው ዘብ መቆም ይጠበቅባቸዋል።

መንግሥትም የዚህን ዓለም አቀፍ ፀረ ኢትዮጵያ ዓጀንዳ አደገኛነት ተረድቶ አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት ይጠበቅበታል። ሁለት  ጎሳ ያላት ሩዋንዳ ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ቱትሲዎችን መጨፍጨፋቸው ትምህርት ሊሆነን ይገባል። ከሰማኒያ በላይ ማህበረሰብ ባለባት ኢትዮጵያ የዘርና የሃይማኖት ብጥብጥ ቢነሳ የእልቂቱ መጠን መገመት አዳጋች  አይሆንም። ጽንፈኞች ስራአጡን ወጣት በገንዘብና በቁሳቁስ እየደለሉ፤ ጎሳና ሃይማኖት ተኮር ቅስቀሳ ሲአደርጉ  ስናይ መጻዒው ችግር አስከፊ እንደሚሆን እንገምታለን። እኛ በካናዳ ርዕሰ ከተማ ኦታዋ የምንገኝ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ የተከሰተውን ጎሳና ሃይማኖት ተኮር ቅስቀሳና ፍጅት በሐዝንና በቁጭት ተወያይተንበታል። ስለሆነም የሚከተለውን የሃገር አድን ጥሪ ለኢትዮጵያ መንግስት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፤ ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን እናቀርባለን፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስርዓት በሰው ልጅ የሚፈጠር ወይስ ከሰማይ ዱብ የሚል ነገር? በምሁራን ፎረም በአንድ ተሳታፊ ለተሰነዘረ አስተያየት የሚሆን መልስ!

ለኢትዮጵያ መንግሥት፥  

  1. በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ የሰው ዘርን ሁሉ ያሳዘነና ያስቆጣ አረመኒያዊ ድርጊት ስለሆነ እናወገዘዋለን። በፍቅር፣ በባህልና በጋብቻ የተጋመደው ሕዝባችን በአብሮነት የመኖር ፍላጎቱ እንዲሟላ መንግሥት የሕዝብ አጋርነቱን በማያሻማ ሁኔታ ያሳይ፤ የሕግ የበላይነትን እንዲአስከብር እንጠይቃለን፤

 

  1. የጎሳና ሃይማኖት ጽንፈኞችን፣ አገር አፍራሾችን፣ የውጪ ዜግነት ይዘው ኢትይጵያን የሚአተራምሱትን በሕግ ፊት አቅርቦ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪአችንን እናቀርባለን።

 

  1. በሰሞኑ የኢትዮጵያ ቀውስ መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጂ ሕይወታቸውን ያጡ ሁሉም (ኢትዮጵያዊያንና ይተለያዬ እምነት ተክታዮች) ናቸው። በሃገራችን የተከሰተው የአንበጣ ወረርሽኝ ዘርና ክልል ለይቶ አልውረረም። በጎሳ ልዩነት የሚነሳ ሰደድ የሚአነደው ሁሉንም ስለሆነ የዘር  ፌድራሊዝም እንዲወገድ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

 

  1. ሃገር በመንጋ ፖለቲካ ሲታመስ ስርዓት አልበኝነትን ይነግሳል። ሰራዊት ወደ መንደርና ቀበሌ ወርዶ መንጋን መቆጣጠር ያስቸግራል። የመንጋን ፖለቲካ መቆጣጠር የሚቻለው ሕጋዊ እውቅና ባለው በአካባቢ ጥበቃ ሃይል ነው። ስለሆነም መንግስት ሕዝባዊ የአካባቢ ጥበቃ ሰራዊት መልምሎ፤ አሰልጥኖና በሕግ እንዲአሰማራ እንጠይቃለን።

 

  1. መንግሥት በተደራጁ የአጥቂ ሀይሎች ት በደረሰው አሰቃቂ የሰው ዕልቂት ሰለባ ለሆኑት፣ ንብረታቸው ለወደመባቸው ቤተሰቦችና ተቋማት አስፈላጊውን ካስ እንዲሰጥ፤ የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መልሶ እንዲአቋቁምና አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲአደርግ፣ አስቸኳይ የምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፤ አልባሳትና መጠለያ እንዲአቀርብ ጥሪ እናቀርባለን፤

 

  1. በየደረጀው የሚገኙት የአስተዳደርና የጸጥታ ጥበቃ አካላት በየጊዜው በሠላማዊ ወገኖቻችን ላይ የደረሱትን ጥቃቶች ለመከላከልና አጥቂዎችንም በፍጥነት አድኖ ለፍትሕ ለማቅረብ ያልቻሉበት ሀቅ ሕዝብ በመንግሥት ላይ የነበረው እምነት እንዲሸረሸር አድርጓል። መንግሥት እንዴትና ለምን ሕዝቡን መጠበቅና መከላከል እንደተሳነው ባይገባንም የፀጥታ አስከባሪ ኀይሉን አደረጃጀት እንዲገመግምና ተጠያቂነትን እንዲያሠፍን እንጠይቃለን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ታገል ሰይፉ፡ ኢሕአዴግ ካምፕ ውስጥ ያደገው አውሬ

ለካናዳ ሕዝብና መንግሥት፤

  1. የካናዳ ሕዝብና መንግሥት ለሰላም፤ ለሰበአዊ መብት መከበር በሚአደርገው ትግል ዓለም አቀፍ እውቅናና ከበሬታ አለው። በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትም ከበሬታ የተቸረው ሃገርና ሕዝብ ነው። ሮሚዎ ዳሌር በሩዋንዳ ስለደረሰው እልቂት የሰጡት የፀፀትና የቅድሚያ ማስጠንቀቅያ ደወል እንደትምህርት ሊወሰድ ይገባል። ስለሆነም ካናዳበኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ በዝምታ የማለፍ የሞራል ልእልና እንዲኖራት ስለማይገባ ከአጋር ሃገሮች ጋር በመሆን የጎሳ ፍጅት በኢትዮጵያ እንዳይደርስ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ጫና እንዲአደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን፤

  1. የሃገራቸው ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ልማት ያሳስባቸዋል። በወቅታዊ ሁኔታ ላይ አሉታዊና አውንታዊ ተጽዕኖ እንዳላቸው እሙን ነው። ማህበራዊ ድረገጽ ከፍተው ፖለቲካውን ያጋግላሉ፤ ዋልታ ረገጥ የጎሳና የሃማኖት ልዩነትን ያራግባሉ። ወደ ሃገር ተመልሰው እኩይ ተግባር የሚፈጽሙትን መንግሥት ሕግ ፊት እንዲአቀርብ፤ ካልቻለ ወደ መጡበት ይመልሳቸው።

 

  1. ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፖለቲካ አመለካከት ፤ በእምነትና በጎሳ ተከፋፍለን ስንቋሰል ሃምሳ ዓመት ሆኗል። በሃሳብና በእምነት መለያየት ያለና የነበረ ነው። በጎሳ ተለያይቶ መጣላት ምድራዊም ሰማያዊም አይደለም። ሃምሳ ዓመት ያቦካነው ፖለቲካ ሃገር ሊያሳጣን ጫፍ ላይ ደርሷል። መከፋፈሉን አቁመን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እድገትና ልማት እንሰራ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

 

  1. ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ የተጀመረውን የጎሳና ሃይማኖት ጭፍጨፋ አደገኛነትና ለዓለም ሰላም የሚአስከትለውን ጠንቅ ለካናዳ መንግሥትና ሕዝብ እንደራሴዎቻቸው እንዲያሳውቁ ጥሪ እናቀርባለን።

 

  1. ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ፊደል ያልቆጠሩ ወገኖቻችን አንድ አርገው ያስረከቡንን ኢትዮጵያ የጎሳና ሃይማኖት ጽንፈኛ ልሂቃን እንዲአፈርሷት አንፈቅድም። ኢትዮጵያዊያን፤ የፖለቲካ ድርጅቶችና ልሂቃን በጋር  ጽንፈኞችን እንታገል ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

 

ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ፤

 

  1. ዓለም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የጎሳና የሃይማኖት ጭፍጨፋ አደገኛነት ሊረዳው ይገባል። የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ህብረት ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን አቋቁሞ በናዝሬት፣ በደብረ ዘይት፣ በድሬ ዳዋ፤ ሀረር፣ በባሌ ሮቢ፣ ዶዶላ፤ በቤኒ ሻንጉል፤ በአማራና በሲዳማ ክልሎች የተፈጸሙ ጎሳና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋዎችን አጣርቶ ለዓለም ህብረተስብ እንዲአሳውቅጥሪ እናደርጋለን፤
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች - ግርማ ካሳ

 

ኢትዮጵያዊነት ዛሬ! ኢትዮጵያዊነት ነገ! ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም!

በኦታዋ ካናዳ የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን

ለተጨማሪ መረጃ አቶ ሰማነህ ጀመረን በ stjtamrat@hotmail.com ማግኘት ይቻላል።

ቀን፥ እሁድ፤ጥቅምት ፴ ቀን ፳፩፪

2 Comments

  1. This is a feke story and claim to restore monarchism, suppression of elites who claim they are religious and messenger of God.

    When it come to thier interest that want us to unite or merge with them. Funny!!

    If we claim independence, they will not get the tax coming from Axum, Kulibi Gabriel, and other monasteries based in Tigray, Oromia and others. This is a story devised and shared by Mahibrekidusan anti oromia and fan of fano and killers , amhara elites.

    Church is run by elites to numb the demo, people.

    We have many stories which is totally baseless and next to fairy tale .

    Ethiopian orthodox church priests and mahibrekidusan, MK, defame everyone who go against them and object thier moneyminded politics. They are snoopers .

    Priests poisoned , killed , raped many people. They separate many families using drugs.

    However, they call names other protestant church as heretics, satanic sects and etc as they were defaming artisans, musicians , weavers as evils and cursed group of people .
    Now,n they constantly defame all people who donot acknowledge thier outdated and supressive ideology. They poison many people who can be pride of that old country. Here in Nevada they are many amhara people who snoop against innocent fellow to destroy thier future and this happens in all western world as well.

    Megressa, Nevada, US

Comments are closed.

Share