“የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነስቶ በወጣ ግዜ እነሆ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም ጌታዪ ሆይ ወዮ ምን እናደርጋለን? አለው። እርሱም ከእኛ ጋር ያሉት ከእርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው”። መጽሐፈ ነገስት ከልዕ 6፡ 15-16
ሀቁን እንነጋገር ከተባለ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት አገር አይደለችም። ይህ ማለት ግን ለጥቂቶች የወቅቱ አክራሪ ኦሮሞዎችና ለአክራሪ አስልምና ተከታዮች መንግስተ ሰማይ አልሆነችም ማለት አይደለም። በሌላ በኩል የስው ልጅ ውሎውና በቀኑ መጨረሻ ላይ በስላም ወደ ጎጆውና ቤተስቡ መመለሱ ዋስትና በሌለው ሁኔታ ውስጥ እራሳቸውን የሚያገኝበትና ባልታሰበ ቀንና ስዓት ደክመው ያፈሩትን ንብረታችውን በነዚሁ አክራሪ ቤሄርተኞችና አክራሪ ሙስሊሞች እንዳይወድምባቸው የሚሰጉበት ቀውጢ ሰዓት ላይ ይገኛሉ። ከሁሉም የከፋው ሕዝቡ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ለማድረግ የኦሮሞ አክራሪዎችና አክራሪ ሙስሊሞች ሰውን የመሰለ ክብር በየመንገዱ አሰቃቂ በሆነ መልኩ መግደልና ቤተ አምልኮዎችን ማቃጠል ስራዪ ብለው ተያይዘውታል።
በአሁን ሰዓት ዋናው ፍሬ ነገር ሥልጣን ለመያዝ የሚከጅሉት አክራሪ የእስልምና ተከታዮቸ እና አክራሪ የኦሮሞ ቤሄረቶኞች ሊያሳኩት የሚከጅሉት የግብጽንም ሆነ የሌሎች አረብ አገሮች ጥቅማ ጥቅም ለማስጠበቅ የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ጋር ለማጋጨትና ቀጥሎም አሁን ያለውን የጠቅላይ ሚንስትር አብይን መንግስ ለመጣል የሚሄደበት እርቀት ነው። እኛም ኢትዮጵያውያን ይህንን ተገንዝበን በሀገራችንና በህዝባችን ቀልድ የለም በማለት በኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደም የሚቀልደውንና የአረብ አገራት በተለይ የግብጽ ተላላኪ የሆነውን አቶ ጀዋርን በሄደበት አገርና ከተማ ሁሉ እየተከተልን ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ውሻ እያዋከብነው ይገኛል።
መታውቅ ያለበት አቶ ጀዋርም ሆነ ሌሎች አክራሪ ኦሮሞዎች እጅግ በሚያስከፋ መንገድ የስው ልጆችን መብቶትችና ነጻነቶች ለመግፈፍ እንዲያመቻቸው ከላው መንግስት ስልጣንን ለመውስድ እየተጎዙበት ያለው መንገድ ህወሀት ከሄደብት መስመር ጋር መመሳሰሉ ነው። ይህን አይነት መንገድ ደሞ ከህወሀት ጥፋቶችና ክፋቶች ያንሳል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። እንዲያውም ኢትዮጵያን የማዋረዱን ሥራ ህወሃቶች ጀመሩት እንጂ ገና አላጠናቀቀም ብለው የሚያስቡና ለማጠናቀቅ ከአክራሪ ሙስሊም አገሮች ጋር ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ።
የዚህም ማሳያ የሚሆነው በቤተክርስቲያኖችና በአማኞች ላይ የሚፈጸመው ባዕድ ደባ ይህንኑ አመላካች ነው ብል ማጋነን አይሆንም። ይህንን የጀዋርና የአክራሪ ሙስሊሞችን አካሄድ በግዜ ካልተገታ ህዝባችን አንደ ህዝብ አገራችንም እንደ አገር መውጫ ወደ ሌለው ችግር ወስጥ እንገባለን ማለት ነው ለምን ቢባል የጥፋቱ ተግባር የሚካሄደው በአዕምሮም ሆን በኅሊና ምንም ዐይነት ብቃት በሌላቸው ኅሊና ቢሶችና በስንኩሎች በመሆኑ፡ ጥፋቱ የክፋና የተፋጠነ ይሆናል።
አቶ ጀዋር እና ተከታዮቹ ኩሩውን የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊና ኩሩውን የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊ ለማጋጨት ባለፉት ሁለት ሦስት ወራቶች ብቻ ቡዙ ቤተክርስቲያኖች አስቃጠሉ፤ደፈሩም የሀይማኖት አባቶችንም ገደሉም፤ አሰደዱም የሚገርመው ነገር ዛሬም እኛም ካለንበት ሆነን በኢትዮጵያ ያለውም ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። ይህ በፈጣሪ የሚሳብበው የሽሽት ጸሎት ይመስለኛል፡፡
ይህ አባባላችን አንድ ወቅት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በጽሁፍ ያስነበቡንን ያስታውሰኛል – “የሀገራችን ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። መደብ ላይ ከመተኛት አሹቅ ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት በታች ወዴት ወደ ከፋ ይወረዳል?” ብለው ነበር።
በሌላ በኩል አንድ የቀድሞ የሕወሃት ባልሥልጣን የአማራና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግንኝነትን መምታት ለድርጅታችው ዓላማ መሳካት ዐይነተኛ መሣሪያ መሆኑን በገሃድ መናግራችው፡ የዘር ማጽዳቱ ዘመቻ ምን ያህል በዕቅድ የተያዘ መሆኑን አመላካች ነበር።
ሕወሃት በተወገደ በሁለት አመቱ አቶ ጀዋር በተራው ኢትዮጵያን ለማጥፋትና የሀይማኖት ጦርነት ለመጀመር ቤተክርስቲያን ማቃጠል የእለት ተለት ስራው አድርጎ ተያይዞታል። አቶ ጀዋር አልገባውም እንጂ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተጋቡና የተዋለዱ አንድ ያንዱን ክፉ ማየት የማይፈልጉ መሆናቸውን አልተገነዘበም። አቶ ጀዋር አልታየውም እንጂ በአሁኑም ሰዓት መላው ኢትዮጵያዊ ከውጪ ጠላት የመጣበት በሚመስል መልኩ አገራችንን ኢትዮጵያን ከአክራሪ ኦሮሞዎችና ከአክራሪ ሙስሊሞች ለመታደግ ሆ ብሎ ተንስቶል “ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል“ ይባል የለ። አቶ ጀዋርም ሆነ አክራሪው የኦሮሞ ቤሄረተኞችና አክራሬ አስላማዊ ክፍል ህወሀት ከወደቀ ጀምሮ እስከ ዛሬ የፈጻማቸው ወንጀሎች ከበቂ በላይ ማስረጃ ስላለ የፊደራል አቃቢ ህግ ከህግ ፊት አስቀርቦ እምነት ክህደቱን መጠየቅ ይጠበቅበታል ያ ሆኖ ካልተገኘ የፊደራል አቃቢ ህጉ እራሱ የወንጀሉ ተባባሪና ወንጀለኛ ነው ማለት ነው ይህ ከሆነ ደሞ ጥያቄችን የሚሆነው የፊደራል አቃቢ ህግ ለፍርድ ይቅረብ ማለት ነው።
እንደ እውነቱ ከሆነ አቶ ጀዋር የተጣላው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር አሊያም ከአንድ ጎሳ ጋር አይደለም በአሁኑ ሰዓት ጀዋር የተጣላው ከመላው ኢትዮጵያዊ ጋር ነው ይህ ደሞ “አይጥ ሞቷን ስትሻ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች” የሚሉትን የአባቶች አባባል ነው የሚያስታውሰኝ።
አሁን እንደሚታየው ክሆነ ለአቶ ጀዋርም ሆነ ለአክራሪ ኦሮሞዎችና ለአክራሪ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ማተራመስ ዐይነተኛ የገንዝብ ማግኛ ምንጭ ሆኖአል ብል ማጋነን አይመስለኝ። ይህንን ተገንዝበን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን የሀገር ጥፋት መዋጋት ይገባናል እንጂ ከመንግስት ብቻ የምንጠብቀው ሊሆን አይገባም። ዛሬ ይህንን ለማድረግ ከምንጊዜውም በበለጠ ተክኖሎጂ የፈጠራቸው አመቺ ሁኔታዎች ስላሉ፤ እንዚህን ተክኖሎጂዎች በመጠቀም፡ ሁኒታውን የዓለም ህዝብ እንዲያውቀው ማድረግ ይቻላል። ተገቢም ነው።
በሌላ በኩል ልንረሳው የማይገባው ቁም ነገር ታላላቅ የኦሮሞ አባቶቻችንና ታላላቅ የኦሮሞ እናቶቻችን እንዲሁም ታላላቅ የኦሮሞ እህቶችና ታላላቅ የኦሮሞ ወንድሞች የኢትዮጵያዊነት ህልም አላቸው ብል መሳሳት አይሆንም፡፡ ቀሪዎቹ አክራሪዎቹ በቅዠት የተሞሉ ናቸው ባይ ነኝ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሌሊትም ሆነ ቀን እንቅልፍ አልባ የሆነው ጀዋር ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም አክራሪ ኦሮሞዎችና አክራሪ ሙስሊሞች ተማርን የሚሉ ፕሮፊሰሮችና ዶ/ር ነን ባዮቹና ጭምር ናቸው፡፡ አቶ ጀዋርም ሆነ ሌሎቹ አክራሪ ኦሮሞዎችም ሆኑ አክራሪ ሙስሊሞች ማወቅ የሚገባቸው ከሏአላዊነት በፊት ስባዊነት ምቅደም እንዳለበት ነው።
ፕሮፌሰር አል ማርያም በአንድ ወቅት መጣጥፋቸው ስለሙስና ሲጽፉ ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ ስገልጹ። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። ‘’ In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. ’’(Al Mariam)
በአሁን ሰዓት በጣም የሚያሳዝነው በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ምሁራን፣ አካዳሚክስ፣ ፕሮፌሰሮች እና የተማረው ልሂቅ ትውልድ የአክራሪ ኦሮሞዎች እና የአክራሪ ሙስሊሞችን አምባገነንነት በተጨባጭ ተግባራት በምስክርነት እየተመለከተ እንደ ድንጋይ ሀውልት ተገትሮ ጸጥ ካለ በእያንዳንዷ ጉዳይ ላይ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የመሆነና የተቆርቆሪነት ስሜት ካላሳየ የአገራችን የኢትዮጵያና የዜጎች ኃላፊነት በጥቂቶች ላይ ብቻ የሚወድቅ በመሆን ሸክሙ የበዛ ይሆናል፡፡
አቶ ጀዋር በሄደባቸው አገሮች ሁሉ ይሀፍረት ሸማ ከመከናነቡ በተጨማሪ በሄደባቸው አገሮች ሁሉ ጥርስ ውስጥ መግባቱ ምንም ጥርጥር የለውም እንኮን እርሱ እሱን ለማጀብና ለማድነቅ በስብሰባው ውስጥ የገቡ ሳይቀር ማንነታቸውን ለማወቅ የየአገሮቹ የደህንነት ክፍሎች ክትትል እንደሚጀምሩና በተለያዩ አገራት ካሉ የደህንነት ጽህፈት ቤቶች ጋር ስለ አቶ ጀዋር ማንነትና ከማን ጋር ግንኙነትና ቀረቤታ እንዳለው የወደፊት ተልኮውስ ምን እንደሆነ በጥንቃቄ እንደሚከታተሉት ምንም ጥርጥር የለውም ይህንንም የሚያደርጉት ለኢትዮጵያና ለህዝቦቾ ብለው ሳይሆን ለያገራቸው ሲሉ ነው ምክንያቱም ኡሰማ ቢላዲን ከየት ተንስቶ የት እንደደረሰና በእያንዳንዳቸው አገር ላይ ያደረስውን ቀውስ የማይረሱትና በየዓመቱ ሴፕቴምበር 11 እያሉ እያከበሩት ነውና።
በማስከተልም ለክቡር ጠ/ሚ አብይ ያለኝ መለክት በኔ እምነት አቶ ጀዋር ይህንን ዓይነት አስከፊና ዘግናኝ እልቂት በአገራችንና በህዝባችን ላይ እንዲደርስና የሐይማኖት ጦርነት እንዲነሳ እየሰራ ያለው ከአንዳንድ አረብ አገሮች ጋር ሆኖ እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ነው። በሌላ በኩል ደሞ ድፍረቱን ያገኘው “ሁለት ጉድጎድ ያላት አይጥ አትሞትም” የሚለውን አባባል በመጠቀሙ ነው ይህውም በአንድ በኩል የርሶና የመንግስት አማካሪ ሲሆን በሌላ በኩል ደሞ የኔ የሚላቸው አክራሪ የኦሮሞ ሙህራኖች ነን ባዮችና አክራሪ ሙሲሊሞች ስለሚከተሉት በተጨማሪ አንዳንድ የአረብ አገራት በገንዘብ ስለሚዶጉሙት ነው።
በመጨረሻም በመግቢ ላይ ከመጽሐፈ ነገስት ከልዕ 6፡ 15-16 የተዋስኩት ጥቅስ ለእርሶ ለጠ/ሚ አብይ ትመጥናለች ብዪ አስባለው ምክንያቱም አቶ ጀዋር ጋ ከሉት አክራሪ ኦሮሞዎች ይልቅ እርሶ ጋ ያሉት ታላላቅ የኦሮሞ አባቶቻችንና ታላላቅ የኦሮሞ እናቶቻችን እንዲሁም ታላላቅ የኦሮሞ እህቶችና ታላላቅ የኦሮሞ ወንድሞች የኢትዮጵያዊነት ህልም ያላቸው እንዲሁም ጀዋር ጋ ካሉትና ለባእድ አገር ካደሩ አክራሪና ሙስሊሞች ይልቅ ከርሶ ጎን የሚቆሙት ታላላቅ የእስልምና ተከታይ አባቶቻችን እና ታላላቅ እናቶቻችን እንዲሁም ታላላቅ የእስልምና ተከታታዮች እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን። በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያዊ ከጎኖት ስለሆነ ጅዋርን አትፍሩት ምክንያቱም ከእርሶ ጋ ያሉት እርሱ ጋ ካሉት ይበልጣሉና።
አንድ አምላክ አገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቃት!