March 8, 2013
1 min read

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ላለባት ጨዋታ ተጫዋቾች ተመረጡ

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቦስትዋና ጋር ላለባት ጨዋታ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተጫዋቾቻቸውን ይፋ አደረጉ።

በዚህም መሰረት፦

 ግብ ጠባቂዎች 

ሲሳይ ባንጫ ፣ ጀማል ጣሰው እና ደረጀ አለሙ

ተከላካዮች

ደጉ ደበበ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ አበባው ቡጣቆ ፣ አሉላ ግርማ ፣ ብርሃኑ ቦጋለ ፣ ስዩም ተስፋየ ፣አክሊሉ አየነው እና አይናለም ሃይሉ

አማካዮች 

ሽመልስ በቀለ ፣ያሬድ ዝናቡ ፣ አዲስ ህንጻ ፣ በሃይሉ አሰፋ ፣ ምንያህል ተሾመ ፣ ኤፍሬም አሻሞ ፣ ፍጹም ተፈሪ እና አስራት መገርሳ

አጥቂዎች

አዳነ ግርማ ፣ ዮናታን ብርሃኑ እና ጌታነህ ከበደ ናቸው።

ለብሄራዊ ቡድኑ የተጠሩት ተጫዋቾች ከፊታችን ቅዳሜ የካቲት 30 ጀምሮ ሆቴል በመግባት ልምምዳቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።

 

ብሔራዊ ቡድናችንን ብራዚል ላይ ለዓለም ዋንጫ ሲጫወት ለማየት ያብቃን

Go toTop