የኔዘርላንድ የውጭ ንግድና የልማት (እርዳታ) ሚኒስቴር የርሃብተኛ አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ኤኮኖሚዋ አድጎ ከተረጅነት ወደ አቅራቢነት ተሻግራለች አሉ
በኔዘርላንድ በየእለቱ የሚታተመው ፎልክስ ክራንት (VOLKS KRANT) የተባለው ጋዜጣ በማርች 02-2013 ባወጣው እትሙ ጎላ ባለ እርዕስ ስር የርሃብ አገር የሆነችው ኢትዮጵያ የእድገት ምልክት ሆነች በማለት ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። ለዘገባው መነሻና ዋቢ ያደረገው የኔዘርላንድ መንግሥት የውጭ ንግድና ግንኙነት ሚኒስትር የሠራተኛው ፓርቲ
(Partij van de Arbeid) አባል የሆነችው ወ/ሮ. ፑልማን በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረገችውን ጉብኝትና የሰነዘረችውኝ አስተያየት መነሻ በማድረግ ነው።ከዓመታት ወዲህ ከግራ ክንፍ ፓርቲነት ወደ ቀኝ እያዘመመ ይባስ ብሎም በአሁኑ ጊዜ ከቀኙ የሊበራል ፓርቲ ፌፌዴ ከተባለው ጋር ጥምር መንግሥት በማቋቋም ቁሜለታለሁ የሚለው የሠራተኛ መደብ ሳይቀር ለችግርና ለሥራ መፈናቀል በር የሚከፍት ፖሊሲ በማውጣት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ደጋፊው ቊጥር ከቀን ወደቀን እየቀነሰ በመሄድ ላይ ነው።እንደሚባለው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ምርጫ ቢደረግ በስልጣን ላይ ለመውጣት ከበቃበት ከስድስት ወራት ምርጫ ጋር ሲወዳደር ከሩብ በላይ የሚሆን ድምጽ እንሚያጣ በተደረገው አሰሳ የተረጋገጠ ሲሆን ይህ አሃዝ ወደፊት እያደገ እንጂ እየቀነሰ እንደማይመጣ ማረጋገጫ ምልክቶች በመታየት ላይ ናቸው።የመንግሥቱም ዕድሜ አጠራጣሪ እየሆነ መጥቷል።ይህን በዚህ አቁሜ ወደተነሳሁበት ያገራችን ጉዳይ እመለሳለሁ።
ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ በኤኮኖሚ እድገት ከሚያሳዩት የአፍሪካ አገሮች ግንባር ቀደምነቱን ትይዛለች በማለት በመጀመር እርዳታ ከመቀበል ወደ ንግድ አጋርነት ተሻግራለች ለዚህም ያበቃት እርዳታ ሳይሆን በንግዱ ዘርፍ በኩል የውጭ አምራቾች በተከፈተላቸው ዕድል ነው በማለት ከእርዳታ ይበልጥ የንግዱ ዘርፍ እንደሚጠቅም በአንክሮ
ተናግራለች።ይህ አባባሏ ግን በአገሯ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ተንታኞች ተቀባይነት አላገኘም። የተጓዘቸበት ዋና ዓላማ የኔዘርላንድን የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ ለማጠናከር ሲሆን የተለያዩ የንግድና አምራች ዘርፍ ተወካዮችን አስከትላ ነው።በውጭ አገር ኩባንያዎች የሚያደርጉት መስፋፋትና እንቅስቃሴ 50% የሚደጎመው ደሃ
አገሮችን ለመርዳት በሚለው ሽፋን ከግብር ከፋዩ ሕዝብ ከሚሰበሰበው ግብር ነው።በኢትዮጵያም በመንግሥት ፈቃድና ትእዛዝ ለኩባንያዎች ማቋቋሚያና መነሻ ከ70% በላይ በድጎማ ወይም ከወለድ ነጻ የሆነ ብድር እስከተወሰነ ዓመትም አምርተው በሚሸጡት ላይ ቀረጥ እንዳይከፍሉ የሚረዳ መመሪያ ወጥቷል።ይህንን ዕድል የሚያገኘው የአገር ተወላጁ ጥቂቱ ሲሆን ለዚያውም በስውር ከባለሥልጣኑ ጋር በተዘዋዋሪ መንገድ በሽርክና አለዚያም ወፈር ያለ ጉቦ ከከፈለ ነው።ይህ የውጭ አገር ኩባንያዎች መስፋፋትና ዘመቻ ደሃ አገሮችን መርዳትና ማሳደግ በሚል ሽፋን የተጠቀለለ በግሎባላይዜሽን መርሆ የዘረፋ ሰንሰለት የሚዘረጋበት፣በኤኮኖሚ ዘርፍ ምክንያት ጠልቆ በመግባት የከባቢ የፖለቲካ ጥቅምን ለማስጠበቅ ከሚደረገው የእጅ አዙር ቅኚ ስትራተጂክና የረጅም ጊዜ እቅድ ተነጥሎ አይታይም።
ይህ እንቅስቃሴ ከውጭ መልኩ ሲታይ ለደሃው ሕዝብ የሥራ ዕድል ይከፍታል ቢባልም፣የሠራተኛው ጤናና ደህንነት፣ዋስትና፣የከባቢ ንጽህናና የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ የተጠበቀ አለመሆኑ በተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን እያጠኑ መረዳት ይቻላል። በአበባ ምርት ዙሪያ የሚጠቀሙበት ኬሚካል ከመሬትና ከከባቢ ብከላው ባሻገር ሠራተኛው መደበኛ የመከላከያ ትጥቅና መሳሪያ ሳይኖረው ላልነበረበት በሽታ ተጋልጧል።ከጧት እስከ ማታ ደፋ ቀና ሲል ለዋለበት አድካሚ ሥራ የሚከፈለው ደመወዝ ወይም የቀን አበል ከእጅ ወደአፍ ነው።ከነጭራሹም በቀን ለሚያስፈልገው ወጭ አይሸፍንለትም።የአንድ ሠራተኛ የቀን አበል ቢሰላ በአውሮፓ ገበያ አንዲት ዘለላ ጽጌረዳ የምትሸጥበትን ሁለት ኤሮ ወይም ከዚያ በላይ አይሆንም።ለአንድ ሠራተኛ በቀን 20 የኢትዮጵያ ብር ቢከፈለው 25 ብር ከፍሎ አንድ እንጀራ በሽሮ ገዝቶ ለመብላት አይችልም ማለት ነው።ሌላ ሌላ ወጩ፣የቤት ኪራይ፣ቢያመው የመታከሚያ ወይም የመለስተኛ መድሃኒት መግዣ፣የልጆቹ ፣የራሱ ልብስ፣የትምህርት ቤት ወጭ… ዘተከየትናእንዴትእንደሚያገኘውሲያስቡትይዘገንናል።አንደውአይጣል ! ያሰኛል።ይህን በሚመለከት ከሰባት ዓመት በፊት “ትዝብት” በሚለውወቅታዊጽሁፌሰፊትንተናአቅርቤነበር፤በከባቢየምካለውየሶሻሊስትፓርቲጋርተወያይቸበትድርጅቱቢዘጋናሠራተኛውቢባረርምንአማራጭአለው?በሚል ስጋት ጊዜ እስኪመቻች ድረስ ሁኔታውን መከታተሉና ቀስ በቀስ እንዲሻሻል ውስጥ ለውስጥ ጥረት ማድረጉ እንደሚሻል አምነንበት ቢበዛም ቢያንስም አንዳንድ ለውጦች እንዲከሰቱ ሆነ።
ሚኒስትሯ ለኢትዮጵያ እድገትና ልማት በማሰብ ያደረገችው ጎዞ በሚመስለው እንቅስቃሴዋ የትላልቅ አበባ እርሻዎችን የጎበኘች ሲሆን የአገሪቱን ባለሥልጣናትና ጠ/ሚኒስትሩን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጭምር አነጋግራለች።በዋናነት ግን የጉዞዋ ዓላማ የሃይነከንን ቢራ ፋብሪካ መሰረት ለመጣል ነበር።ከቢራ ፋብሪካው ዳሬክተር ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ቦታ ስትደርስ በመጀመሪያው ገጽ ላይ እንደሚታየው ቀይ ምንጣፍ /ስጋጃ/ተነጥፎላት የባህል ዘፋኞች በልልታና በጭፈራ የተቀበሏት ሲሆን በሚያማምሩ ሆቴሎችና መዝናኛ ቦታዎች በተደረገላት መስተንግዶ እንዲሁም ብቅ ብቅ ባሉ የህንፃ ስራዎች ቀልቧ ተስቦ የተሳሳተ አመለካከት እንዲያድርባት ተጽእኖ ሳያደርግባት እንዳልቀረ መገመት አያቅትም።ወያኔ የሚመራው የኢሕአዴግ መንግሥት ለመንግሥታት ተጠሪዎችና እንግዶች ልዩ ልዩ ገጸበረከትና መስተንግዶ በማድረግ ዓይናቸው እንዲጋረድ በማድረጉ ጥበብ የተካነ ነው። እርግጥ የቢራ ፋብሪካው መቋቋም ለተወሰኑ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥር ይሆናል፤ግን በአገር ውስጥ ባሉ የቢራ
ፋብሪካዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳትና ተጽእኖ ሲታሰብ ከጥቅም ጉዳቱ ያመዝናል።የቢራ ፋብሪካውና የምርቱ አይነት መብዛት በውድድር ለተጠቃሚው ጥሩ ነው የሚል ግምት ሊያሳድርብን ይችል ይሆናል።ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ የሚያሳስበውና የሚያስጨንቀው የሚታገልለትም ቢራ ለማማረጥ ሳይሆን መደበኛ ምግብ በልቶ ማደሩ፣ጤናው የሚጠበቅበት ተቋምና መድሃኒት መስፋፋቱና መገኘቱ፣የሰብአዊና የዜግነት መብቱ መጠበቁ፣የኔ ነው የሚለው መንግሥት ለሥልጣን መብቃቱ፣በአገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትነት ድርሻውን መወጣቱ፣መወሰኑ፣ያገሩ አንድነት ና ዳር ድንበር መከበሩና፣በፈለገው ቦታ ተዘዋውሮ ያሻውን ሠርቶ ማደሩ፣የፈለገውን እምነት የመከተሉ ወይም ያለመከተል መብቱ መረጋገጡ…ወዘተነው።በውጭአገርኩባንያዎችየሚቋቋመውተቋምናየምርትዘርፍበሕዝቡፍላጎት፣ጥቅምናአቅምላይየተመሰረተሳይሆንየውጭባለሃብቶችበርካሽዋጋአምርተውበውድዋጋወደውጭአገርአውጥተውለመሸጥበሚያስችላቸውናያንንበሚያመቻችበሙስናሰንሰለትየተሳሰረየባለሀብቶችናየባለሥልጣኖችውሳኔነው።ለምመሬትንበመቀራመትና የተፈጥሮ ሃብት ለመበዝበዝ የሚደረግ የከባቢው ድመትከእጅአዙርቅኝአገዛዝሂደትተነጥሎመታየትአይገባውም።ስለሆነምበውጭአገርየምንኖርየአገራችንነፃነት፣የወገናችንክብር፣ደህንነትናአንድነትየሚያሳስበንይህንንአይነቱንበማርየተጠቀለለመርዝማጋለጥናመታገልይኖርብናል። ገራችንንአቀባባይከበርቴዎችናባለሥልጣኖችለውጭአገርጥቅምአሳልፈውሲሰጡ፣ሲሸጡናሲለውጡበዝምታማየትወይምእንደእድገትናመሻሻልሂደትአድርጎመቁጠርስህተትከመሆኑምበላይበታሪክየሚያሶቅሰንጥቁርነጥብይሆናል። የቢራፋብሪካውየከባቢገበሬዎችከምግብምርትይልቅየቢራብቅልእንዲያመርቱሲያደርግምግብአምራችየነበረውሕዝብምግብሸማችያደርገዋልማለትነው።በ 2014 ይከፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ የሃይነከን ቢራ ፋብሪካ ለ 20.000 ሰዎች የገቢ ምንጭ ይሆናል በማለት የኩባንያው መሪ ዮሃን ዶየር ገልጿል፤ይህ ማለት 20.000 ምግብ
አምራች የነበረ ገበሬ ሕዝብ ለምግብ የሚሆን እርሻውን ትቶ በመቀጠር እራሱ ሸምቶ አዳሪ ይሆናል ማለት ነው።በሌላ ገጹ ለሰፊው ሕዝብ መቅረብ የሚገባው የእርሻ ምርት ይቀንሳል፤መሬቱም ጦም ያደራል ወይም ደግሞ ለቢራ የሚሆን ገብስ ይዘራበታል ማለት ነው።ይህ አይነቱ ሂደት በምግብ እጥረትና በዋጋ ግሽበት ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ ማጤን ያስፈልጋል።ለመሆኑ የቢራው ምርት ለየትኛው የህብረተሰብ ክፍል ጥቃሞት ይሰጣል ?እንኳንስ ተራው ደሃ ሕዝብ የመካከለኛ ገቢ ያለውም የህብረተሰብ ክፍል እንኳንስ ለሃይንከን ቢራ ለሎካል ጠላ ፣ጠጅና ድራፍት ቢራ መግዣም አቅም የለውም።በሌሎች አገሮች እንደታየው የሃይንከን ዓላማ በርካሽ አገሮች አምርቶ በማውጣት በውድ ሸጦ ትርፍ ማካበት ነው።በአበባውም ምርት ዙሪያ የሚታየው ይኸው ነው።
በቢራ ምርቱ ዘርፍ የተሰለፈው ሃይንከን ብቻ አይደለም ሌላውም ባቫሪያ በመባል የሚታወቀው የደች ቢራ ጠማቂ ድርጅት እንዲሁ በኢትዮጵያ ውስጥ እጁን አስገብቷል።ስታይን ስዊንክልስ የተባለው የፍብሪካው ተወካይ በሰጠው መግለጫ የቢራ ፋብሪካው ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል ሲፈጥር 8000ኢትዮጵያውያን የድርሻ /የሸር/ተካፋዮች ይሆናሉ ብሏል።የቢራ ፋብሪካውን ተፈላጊነት ሲገልጽ የግንባታ ሥራ በሰፊው እያደገ በመምጣቱ ቀን በግንባታ ሥራ ላይ የዋለው ሠራተኛ ከሥራ በዃላ የቢራ ፍላጎቱ ከፍተኛ ስለሆነ ያዋጣል ብሏል።የድርጅቱ ግንባታ ከአንድ ዓመት ተኩል በዃላ ተጠናቆ ፋብሪካው ሥራውን ይጀምራል ብሏል።
ሌላው የባሎን ጉዞ ድርጅት ባለቤት የሆነው ሆላንዳዊ /ደች/ ብራም ፋን ሎስብሩክ በአገሪቱ የኤኮኖሚ እድገት የሚታይ መሆኑን ገልጾ በ 2012 የጀመረው የንግድ ተቋም 8 ኢትዮጵያውያንና ሁለት ያገሩን ዜጎች እንዳቀፈ ገልጾ የዚህ አይነቱ የኔዘርላንድ እንቅስቃሴ ኔዘርላንድን ከገባችበት የኤኮኖሚ ቀውስና ማጥ እንደሚያሶጣት፣እቤቱ ለተቀመጠው ሥራአጥ ኔዘርላንዳዊ የሥራ ዕድል እንደሚከፍት በመግለጽ ወደ ኢትዮጵያ ፊታቸውን እንዲያዞሩ ጥሪ አድርጓል። የቢራ ፋብሪካዎቹ መቋቋም በሌሎቹ የአገር ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ላይ የሚያመጡትን ኪሳራና የሠራተኛ መባረር ማጤን ያስፈልጋል ፡፡የብዙ ገንዘብ ተቀማጭ ካላቸው መልቲ ናሽናል ኩባንያዎች ጋር ለመወዳደር አይችሉም፣ያላቸው እድል አዝግመው አዝግመው ተንገጫግጨው መቆም ነው።ይህ ሲሆን ደግሞ ተቀጥሮ የነበረው ዜጋ ለሥራ አጥነት ይጋለጣል።
የአበባ አምረች የሆነው ፍራንክ አመርላን የተባለው ደግሞ የበኩሉን እንዲህ ይላል። ከወንድሙ ጋር በ 2006 በኢትዮጵያ የጀመረው የአበባ ምርት አሁን ለ1200 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል እንደከፈተና ትርፋማ እንደሆነ አብራርቷል።በኔዘርላንድ ውስጥ ከነበሩት የአበባ አምራች ድርጅቶች ውስጥ 70% በኪሰራ እንደተዘጉ በማብራራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የሱ ቢጤዎች ግን በትንሽ ወጭ፣ በርካሽ የሰው ጉልበትና በመንግሥት ድጎማ የትርፍ ባለቤት መሆናቸውን፣ከሚያመርቱትም 99% ወደ ኔዘርላንድ የአበባ መሰናዶና ማከፋፈያ እንደሚላክ ሳይደብቅ ተናግሯል።እዚህ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ የአበባ ምርት ቢያመርት ለውጭ ገበያ የሚያወጣበትና የሚያደርስበት ዕድልና
በሩ የተዘጋ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።ሌላውም ምርት አምራች ቢሆን ምርቱን በውጭ አገር ገበያ በቀጥታ ለማቅረብ አይችልም።የግድ አስቸጋሪ ከሆነው ሰንሰለት ውስጥ መግባት አለበት ወይም ያለው ሰፊ ዕድል ለሰንሰለቱ ተዋንያንና ባለቤቶች ምርቱን በርካሽ መሸጥ ነው።የቡናን የገበያ አካሄድ ልብ ይሏል።
በዕቅድ ላይ በቅርቡም ተግባራዊ ለመሆን ጫፍ ላይ የደረሰው የደቾች አንዱ የዘረፋ መንገድ በአገሪቱ ላይ የዳቦ እጥረት ስላለ ያንን ማሟላት ያስፈልጋል በሚል ሰበብ ትልቅ የዳቦ ፋብሪካ የመክፈት ዓላማ ነው።እርግጥ ነው፤ከሕዝቡ ብዛት አንጻር ሲታይ የምግብ /የዳቦ/አቅርቦቱ በጣም አነስተኛ ነው።የኢትዮጵያን ሕዝብ አመጋገብ ሲመረመር ዳቦ ከሚመገበው የከተማ ተዋሪ ይልቅ ያገኛትን ቁራሽ እንጀራ ጠቅሎ የሚጎርሰው ይበልጣል።ያም ሆኖ ግን ዳቦ የለመደው ከተሜ ጦሙን ይደር አይባልም።ይህን አይነቱ የሥራ ዘርፍ ግን ለውጭ ባለሃብቶች አሳልፈው የሚሰጡት ሳይሆን በእርሻ መስክ ላይ የተሰማራው ኢትዮጵያዊ ከእህል ምርቱ ጋር አያይዞ መሥራት ያለበት ቢሆን ይበልጥ የአገርን ኤኮኖሚ እዛው በዛው ለማሳደግ ይረዳል።እራስንም ከመቻሉ ምኞትና ፍላጎት ጋር የተያያዘ ይሆናል።የደቾቹ ፍለጎት ዳቦ አምርቶ በኢትዮጵያ ቀጫጫ ብር ሸጦ ለመክሰር ሳይሆን የረጅም ጊዜ ዓላማቸው ለአውሮፓ ገበያ የዳቦ አቅርቦትን በማሟላት በኤሮ ወይም በዶላር ሸጦ ለማትረፍ ነው።አሁን ባለው ዘመናዊና ፈጣን፡የመጓጓዣ ዘዴ ሌሊት ደብረዘይት ሲጋገር ያደረው ዳቦ ከሰዓት በዃላ ወይም ቢዘገይ በማግስቱ ጧት በአውሮፓ የሱቅ መደርደሪያ ላይ ሊዘረጋ ይችላል።የፈሶሊያንና የፈረንጅ ቃሪያ /ስዊት ፔፐር/ ለምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።በአሁኑም ጊዜ የወያኔ ደጋፊዎችና ተባባሪዎች በውጭ አገር የሚያራምዱት የትኩስ ጤፍ እንጀራ ንግድ አንዱ ማረጋገጫ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች ከመሆን አያልፈም ማለት ነው።በዚህ ከቀጠለ ነገ ደግሞ ቻይናዎች የእንጀራ ፋብሪካ ይተክሉና ወደውጭ ገበያ በማውጣት በእህል መጠንና ዋጋ ላይ ግሽበት ከማምጣቱ በተጨማሪ በጋጋሪነት የተሰማራው ብዙ ደሃ ሕዝብ ሠርቶ እንዳይበላ ይሆናል ማለት ነው።
አንድ መንግሥት የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ሲነድፍና ተግባራዊ ሲያደረግ ቅደም ተከተሉን በመጠበቅ ትኩረትና ድጋፍ መስጠት የሚገባው በመጀመሪያ በአገር ምርት አምራችና ገበያ፣በሕዝቡ ጥቃሞትና አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉትን በአገር ውስጥ ባለሃብቶችና የመንግሥት ዘርፎች እንዲስፋፉ ማድረግ ነው።ለአገር ውስጥ ፍጆታ፣ለሕዝብ አገልገሎት የሚውሉ እንቅስቃሴዎች ሊበረታቱ ይገባል።በርካሽ አምርቶ በውጭ ገበያ ትርፍ ለማግበሰበስ የሚደረገው የውጭ አገር ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ግብግብና ዘመቻ መግቢያ ቀዳዳም ሊነፈገው ይገባል።ለሃገር የሚያስብ የሕዝብ መንግሥት የሚያወጣው ፖሊሲ ለሕዝቡ ኑሮና ጤና ጠቀሜታ የሚኖራቸውን ምርቶች እንዲስፋፉና እንዲያድጉ የሚረዳ እንጂ የሚያቀጭጭ፣ሕዝቡ ን ለአልኮል፣ለእጽና ለሌላ ጎጂ ልማዶች ለሚያጋልጥ ምርት መሆን ለበትም።በጫት ዙሪያ የሚታየው ስብራት አላፊነት የጎደለው መንግሥት የሚከተለው የፖሊሲ ውጤት ነው።
የሥራ ዕድል ይከፍታል ከሚለው ትንታኔ ጎን ለጎን የሚሰጠው ጥቅምና ጉዳት አብሮ መታየት አለበት።ለመሆኑ የሥራ ዕድል ይከፍታል ተብሎ የፈንጂ ፋብሪካ ወይም የኑክሌር ዝቃጭ ማጠራቀሚያ ማቋቋም ተገቢ ነውን ?አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ መሪዎች ግን ጥቅምና ድጋፍ ካገኙበት ይህን ከማድረግ አይመለሱም ፣ዐይናቸውን አያሹም። በአገራችን ደረጃ ቅድሚያ መሰጠት የሚገባው በምግብ ፣በእርሻና ከዚያም ጋር በተያያዘ ኢንዱስትሪ፣ከማምረት እስከ ማዘጋጀት ባለው ሂደት የሚሰማሩትን አገር በቀል የግልና የመንግሥት ድርጅቶች እንዲስፋፉ ዕድል መስጠት፣ በጤና ጥበቃ ከመድሃኒት ማምረት /የባህል መድሃኒቶችን በተጠና መልክ ማቅረብን ያካትታል፤ ምክንያቱም በከፍተኛ ወጭ ከውጭ አገር የማስገባቱንና በውጭ የመተማመኑን ልማድ ያሶግዳል።በተጨማሪም የሕክምና እርዳታ በሕዝቡ ፍላጎትና አቅም ላይ ባተኮረ አሠራርና ወጭ ማስተናገድ የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ነው።የጤና እርዳታ አንዱ ሰብአዊ መብት በመሆኑ ገንዘብ ያለው ሃብታም ብቻ የሚገለገልበትና አሁን ተስፋፍቶ እንደሚታየው በሙያው በዝባዦች የሚጠቀሙበት መሳሪያ እንዳይሆን ማድረግ፣ ንፁህ ውሃ የማግኘትና የመጠቀም ሌላው የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው።ንጽህናው ያልተጠበቀ በውስጥም በውጭም ለቁሻሻ የተጋለጠ ህብረተሰብ ጤነኛ አይሆንም።ጤነኛ ካልሆነም ምርታማ አይሆንም፤ምርታማ ካልሆነ ደግሞ ኑሮው አይሻሻልም፣የአገር ኤኮኖሚም አያድግም።በሌላ አነጋገር ተመጽዋች፣የሌሎችን እጅ ዐይቶ አዳሪ ይሆናል፤አገሩም፡የውጭ ጥገኛ ትሆናለች።
በትምህርት ዘርፍም እንዲሁ አንድ ሕዝብ የዕውቀት ጌታና ባለቤት ካልሆነ እድገቱ የተገታ ነው።ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያይበት ዓይኑ የታወረ ይሆናል።ትምህርት ማለት እውቀት ነው።ለሚሠራው ሁሉ ግንዛቤና እውቀት ሊኖረው የሚችለው ሲማር ነው።ስለሆነም አንድ ሕዝብ ማግኘት ያለበት አንዱ መብቱ የትምህርት ዕድል ማግኘቱ
ነው። ትምህርት፣ ውሃ፣ ጤና … የንግድሸቀጥከሆነጥቂቱባለገንዘብየሚቆጣጠረውናየሚጠቀምበት የግል ይዞታ ይሆንና ጥቂት አዋቂና ጤነኛ ዜጎች በአገሪቱየኤኮኖሚ፣የፖለቲካናየሶሻልእንቅስቃሴዎችባለቤቶችናወሳኞችእንዲሆኑያደርጋል። እርግጥ ነው አንድ አገር ከሌሎች አገሮች ጋር በእኩልነት ደረጃ ላይ በተመሰረተ የንግድም ሆነ የፖለቲካ ተግባራትንማካሄዱተገቢናአስፈላጊምነው።ችግሩየሚነሳውየጌታናየሎሌግንኙነትሲሆንነው።የውጭአገርከበርቴዎች፣ኩባንያዎችምሆኑየመንግሥትተቋማትባላቸውጠንካራጎንሌላውንደካማአገርናሕዝብለመርዳትናኑሮውንለማሻሻልፈቃደኛሆነውከመጡመቀበልብቻሳይሆንእንዲመጡምጥሪማድረግተገቢነው።የሚሰማሩበትመስክግንለአገሪቱአስፈላጊበሆነውበሃይልማመንጫ (ከጸሃይ፣ከውሀ፣ከንፋስ)፣በጤናዙሪያ፣በመድሃኒትፈጠራናዝግጅት፣በእርሻ፣በመሳሪያናማዳበሪያናዘርምርምርናማምረቻ፣በማመላለሻናበመጓጓዣ፣በመገናኛበስልክናበዜናአውታሮችዘርፍእርካሽናዘመናዊ፣ከሕዝቡአቅምጋርየሚመጣጠንአቅርቦትንማስፋፋትናመዘርጋትበሚያስችለው፣መንግሥትናሕዝብበሚጠይቀውናበሚቀበለውአንጻርመሆንአለበትእንጂባለሃብቱያዋጣኛልብሎበሚያስበውከንግድናትርፍአንጻርየሚዘረጋውመስክመሆንአይኖርበትም። እዚህላይእንደምሳሌለመጥቀስየምፈልገውነገርቢኖር፣ ጥቂት ዓመታት በፊት በተወሰኑ ኔዘርላንዳውያንና ኢትዮጵያውያን በመንግሥት ፈቃድና ትብብር በኢትዮጵያ ውስጥ የቤት መኪና አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ “ሆላንድካር” በሚል ስያሜ የመገጣጠሚያተቋምበደብረዘይትመንገድላይተከፍቶነበር።ሃሳቡንሲያዩትደስይላልምክንያቱምከውጭአገርአሮጌመኪናበውድዋጋገዝቶከመጠቀምናከባቢንከመበከልአዲስናበአገርውስጥየተመረተመኪናመግዛቱበብዙመልኩስለሚሻልነው።በጥቂትጊዜውስጥ“አባይ”በመባልየተሰየመመኪናአምርቶለገበያአቅርቦነበር።በአሁኑጊዜግንየመኪናመገጣጠሙሥራቆሞ፣ጋራጁምተዘግቶባለቤቶቹወደሆላንድእንደተመለሱጭምጭምታይሰማል።ለመክሰሩምክንያትየሆነውየሚጠየቅበትዋጋከሕዝቡአቅምበላይበመሆኑገዢበማጣቱነውተብሎይወራል።እርግጥነውበአሁኑጊዜበአውሮፓገበያአንድየኮሪያወይምየጃፓንመኪናከ10.000 ዶላርበታችእየተሸጠኢትዮጵያንበመሰለአገርከ12.000 ዶላርባላነሰዋጋተመሳሳይመኪናሸጬአተርፋለሁብሎማሰብስለንግድሕግጋትእውቀትናግንዛቤአለመኖርነው።እንግዲህእንዲህአይነቱአሰራርነውከወጩናከሸማቹአቅምጋርያልተጣጣመየሽያጭዋጋጠይቆመክሰርየሚመጣው።ለማምረትያወጡትንያህልለማትረፍመሞከርለአንድድርጅትዕድሜማጠርዋናምክንያትነው።ከ10%-15% የተጣራትርፍከተገኘከበቂበላይነው።እንደውምበመጀመሪያውአካባቢምርቱእስኪለመድድረስኪሳራውስጥሳይገቡወይምግፋቢልበ5% ትርፍመንቀሳቀስየአስተዋይነጋዴስልትነው።በኢትዮጵያውስጥልማትአለየለምበሚለውጉዳይላይብዙየተጻፉሳይንሳዊትንታኔዎችመኖራቸውአይካድም።እያነበቡናእየተከታተሉየሚያስፈልገውንእርምጃመውሰድየአገርወዳዱዜጋድርሻነው።በዕውቀትላይየተገነባክርክርለመርታትያለውዕድልከፍተኛነው።የውጭአገርመንግሥታትናሕዝብያገራችንንእውነተኛገጽእንዲረዳ፣በሥልጣንላይያለውንመንግሥትናስርዓትእንዲገነዘብያላሰለሰየዲፕሎማሲናየሎቢሥራመሠራትአለበት።የውጭመንግሥታትአቋማቸውበየጊዜውይለዋወጣል፤ምንጊዜምሚዛኑወደሚያደላውነው።ጊዜያዊጥኢማቸውንከሚያስጠብቅላቸው፣ያሉትንከሚቀበልናያዘዙትንከሚፈጽምላቸውጋርአብሮመዝለቅንይመርጣሉ።ያየማይቀጥልበትሁኔታሲከሰትግንገልበጥይላሉ።ያእንዲሆንየመጫወቻካርታውበእጃችንላይይገኛል።እሱምበሕብረትድምጻችንንማሰማትነው።እንኳንበድርጅትበግለሰብደረጃምአሰራራቸውንማስለወጥይቻላል።አንደምሳሌልጥቀስ፣የዛሬስምንትዓመትይሆናልኢትዮጵያበሄድኩበትወቅትለጉዳይወደሆላንድኤምባሲሄጄነበር።ከኤምባሲውአጥርውጭብዙኢትዮጵያውያንባለጉዳዮች፣መጠለያበሌለበትየጠራራፀሃይ፣ከሰውነትደረጃበወጣአቀባበልናመስተንግዶሲንገላቱለማየትችያለሁ።ሁኔታውንበወቅቱ“ትዝብት” በሚለውጽሁፍገልጫለሁ።እንደተመለስኩለሶሻሊስትፓርቲአባላትሁኔታውንአስረዳሁ።በሁኔታውአዝነውናተናደውወደሚመለከተውባለሥልጣንአቤቱታአቀረቡ።አቤቱታቸውሰሚአገኝቶከዚአወዲህለጉዳይወደኤምባሲውየሚሄዱሰዎችየሚያርፉበትመጠለያናመቀመጫተዘጋጀላቸው።በሌላጊዜስሄድለውጡንለማየትችያለሁ።እዚህላይለመግለጽየምወደውእኔይህንአደረኩ6
ለማለትሳይሆንበተገቢውመንገድናአጋጣሚበመጠቀምየውጭአገርመንግሥታትናተቋማትየሚያደርጉትንስህተትእንዲያርሙማድርግእንደሚቻልለማሳየትነው።በሌላውምወቅትበ
2005-በ2006 በኔዘርላንድፓርላማውስጥበኢትዮጵያውስጥስላለውየሰብአዊመብትጥሰት፣ስለተቃዋሚዎችመታሰርናመገደል፣ስለዲሞክራቲክመብትአለመከበርበማንሳትየዛሬውንአያድርገውናየአሁኑየኔዘርላንድመንግሥትአካልየሆነውየሠራተኛውፓርቲየሚመለከተውንባለሥልጣንየኤኮኖሚተአቅቦእንዲጣል፣የባለስልጣኖችየመንቀሳቀስነጻነትእንዲታገድበኔዘርላንድብቻሳይሆንበመላውአውሮፓተግባራዊእንዲሆንጠይቀውነበር።ይህንአቋምየያዙትበነበረውሁኔታናበተደረገውየሎቢሥራነበር።አሁንምቢሆንያንንአይነትእንቅስቃሴበማካሄድተመሳሳይአቋምእንዲይዙማድረግይቻላል።ይህንበሚመለከትእኔየምሳተፍበትየኢትዮጵያሕዝብየጋራትግልሸንጎ(ሸንጎ)የዲፕሎማሲናየውጭጉዳይዘርፍዘርግቶበስዊድን፣በጀርመን፣በሆላንድ፣በካናዳ፣በአሜሪካናበአውስትራሊያበመንቀሳቀስላይይገኛል።በእንቅስቃሴውውስጥሁሉምእንዲሳተፉበትሸንጎውበተደጋጋሚጥሪአድርጓል።በውጭየተመሰረተውይህግንባርማከናወንካለበትዋናውይኽንንበተግባርመግለጽነው።የሱየኔሳይባልሁሉምየእኛብሎመነሳትናበዘመቻውመሳተፍአለበት።ለግንዛቤናለማስረጃያህልከዚህጽሁፍጋርከሰባትዓመትበፊትየኔዘርላንድፓርላማየተወያየበትንበፓርላማውውስጣዊጋዜጣየሰፈረውንአባሪአድርጌአቅርቤአለሁ።ምንምእንኳንበደችቋንቋቢሆንምአንኳርነጥቡከላይባጭሩየገለጽኩትነው።በአንድነትለዴሞክራሲሥርዓት፣ለአገርአንድነትእንታገል!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አገሬአዲስ