የጄ/ል ክንፈ ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለቀረበባቸው ክስ መቃወሚያቸውን አሰሙ

የጄ/ል ክንፈ ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለቀረበባቸው ክስ መቃወሚያቸውን አሰሙ፡፡ ተጠርጣሪው የኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ዜድቲኢ ከተሰኘው የቻይና ኩባንያ ጋር በፈፀሙት ውል መከሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=14ql5rq_pMI

አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው በዚህ ክስ ከዜድቲኢ ጋር 44‚ 510‚ 971.00 (አርባ አራት ሚሊዩን አምስት መቶ አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ) የአሜሪካን ዶላር የግዥ ውል ለጊዜው ስማቸው በክሱ ውስጥ ካልተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር ቀጥታ ግዥ እንዲፈጸም ማድረጋቸው ተገልፆ ነበር፡፡ በግዢውም በስውር ጥቅም በመመሳጠር በመንግሥትና በኮርፖሬሽኑ የተሰጣቸውን ሹመት፣ ሥልጣን ወይም ኃላፊነት በግልጽ ተግባር ወይም በግድፈት ያላግባብ በመገልገል እንዲሁም ከተሰጣቸው ሥልጣን በላይ አልፎ በመስራት የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት እንዲሁም ለዜድ.ቲ.ኢ. ለማስገኘት በማሰብ በመንግሥትና በኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬሽን ጥቅም ላይ ጉዳት የማድረግ የማድረግ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ነበር፡፡ ጉዳዩን ሲመለከተው የነበረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ ያላቸውን የክስ መቃወሚያ ይዘው እንዲቀርቡ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆችም የክስ መቃወሚያቸውን ዛሬ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ችሎቱም ዐቃቤ ህግ ለቀረበው የክስ መቃወሚያው መልስ እንዲሰጥ ለማድረግ መጪው አርብ የካቲት 22 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: አርበኞች ግንቦት ሰባት በፊኒክስ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ እና የሕዝቡ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር) * "የኦህዴድ አመራር ሆነው ኦሮምኛ የማይናገሩ አሉ - ኤርሚያስ ለገሰ * * በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ... ሌሎችም
Share