ኤርሚያስ አመልጋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በላኩት ደብዳቤ ዘመን ባንክን ቦይኮት አድርጉ ብለዋል (በቪዲዮ የቀረበ)

የአክሰስ ሪል እስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አሜልጋ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የበላይ አመራሮች ጋር በጥቅም በመተሳሰር የቀድሞውን ኢምፔሪያል ሆቴል ያለምንም የጨረታ ሂደት በ75 ሚሊየን ብር ውል ስምምነት በማሰር ሽያጭ እንዲፈፀም በማድረእግ የድርጅቱ ወቅታዊ ዋጋ 51 ሚሊየን ብር መሆኑ እየታወቀ በተጋነነ ዋጋ እንዲሸጥ በማድረግ በመንግስት ሀብት ላይ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ተከሰው ቃሊቲ ይገኛሉ:: በአሁኑ ወቅት በቃሊቲ እስር ቤት ቢጫ የ እስረኞች ዩኒፎርማቸውን ለብሰው እስረኞችን ስለንግድ እያስተማሩ የሚገኙት አቶ ኤርሚያስ በ እስር ቤቱ ብዙ ሰዎችን እየለወጡ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ መረጃ ደርሷል:: እስረኞችም በአቶ ኤርሚያስ የሚሰጠውን ትምህርት በንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ሰምተናል::

https://www.youtube.com/watch?v=QHgOVBzpybE

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ ሚ/ር ዘነቡ ታደሰ ዩጋንዳ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣቷን ተቹ
Share