February 17, 2019
4 mins read

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል

94121

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል፡፡ ሙሽራው አንተነህ አፖሎ የሚባል ሲሆን ለ14 አመታት በእስር ቤቱ የቆየ ታራሚ ነው፡፡ ሙሽሪት መስከረም ደገፉ ከዛሬው ባለቤቷ ጋር የተዋወቀችው እዚያው እስር ቤት የዛሬ ስምንት አመት ሰው ልትጠይቅ በሄደችበት ወቅት ነበር፡፡ ስምንት አመት ሙሉ በአይን ፍቅር የቆየው ግንኙነት ዛሬ ለየት ባለ ሰርግ ወደትዳር አምርቷል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=Fu1uIyUHtps&t=186s

በሰርጉ ስነስርአት ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አርቲስቶች እንዲሁም ታራሚዎች ተገኝተው እንደነበር በስፍራው የነበረው የዘሀበሻ ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ኮሜዲያን ፍልፍሉ ከሚዜዎቹ አንዱ የነበረ ሲህን ለሰርጉ ትልቅ ድምቀት ሰጥቶታል፡፡ በሰርጉ ላይ አንድ ግለሰብ ለሙሽሮቹ አንድ መኪና፣ መኖሪያ ቤትና 500 ሺህ ብር አበርክተውላቸዋል፡፡ እንዲሁም ሙሉ የሰርጉን ወጪ የሸፈነው ይኸው ግለሰብ ነው፡፡ ግለሰቡ ከ10 አመት በፊት በካሚላት አህመድ ላይ አሲድ በመድፋት ወንጀል ተፈርዶበት እዚያው እስር ቤት የሚገኘው ደምሰው ዘሪሁን መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ‹‹ለፍቅር ስል በሰራሁት ጥፋት ታርሜያለሁ›› ሲል ለዘሃበሻ ዘጋቢ የተናገረው ደምሰው ዘሪሁን ‹‹ይህንን የሰርግ ስነስርአት ሙሉ ወጪውን የሸፈንኩትና ለወደፊት መተዳደሪያቸው የሚሆን ስጦታ ያበረከትኩት ፍቅርን ለማሳየት ነው›› ብሏል፡፡ ሙሽሪትና ሙሽራው የተዋወቁትም ሙሽራዋ ደምሰው ዘሪሁንን ልትጠይቅታ በሄደችበት ወቅት ነበር፡፡ ሙሽራው አንተነህ ደገፉ ለዘሃበሻ በሰጠው መግለጫ በሚቀጥለው አመት ቅጣቱን ጨርሶ እንደሚፈታ አስረድቷል፡፡

በሌላ በኩል በ2005 ላይ በቃሊቲ ተመሳሳይ ጋብቻ ተፈጽሞ ነበር::  በሙስሊሞች የመብት ጥያቄ የተነሳ ታስረው የነበሩት ሙባረክ አደምና እና ኻሊድ መሀመድ የተባሉ የ18 አመት ፍርደኛ የነበሩ እስረኞች እስር ቤት ውስጥ ጋብቻቸውን ፈጽመው እንደነበር ይታወሳል::

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተፈጸመውን የሰርግ ስነ ስርዓት በማስመልከት ባስተላለፉት መል ዕክት “ይህ ለሀገራችን በታሪክም የመጀመሪያው ልንለው እንችላለን። አንተነህ አፖሎ እና ሙሽሪት መስከረም ደገፋ ይባላሉ። በቃሊት  በማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘውን የ8 ዓመት ፍቅረኛዋን በዛሬው ዕለት የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈጽመዋል።” ብለዋል::

94106
Previous Story

ኤርሚያስ አመልጋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በላኩት ደብዳቤ ዘመን ባንክን ቦይኮት አድርጉ ብለዋል (በቪዲዮ የቀረበ)

94125
Next Story

በጎንደር ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ | መከላከያ ገባ 

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop