የመከላከያ ሰራዊት በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር  የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ…

የመከላከያ ሰራዊት በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር  የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብ መደረጉን የከተማይቱ አስተዳደር አስታወቀ። 200 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል። 

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ድሬዳዋ እንዲገባ የተደረገው ባለፉት ቀናት በከተማይቱ የነበረው ሁኔታ ከአስተዳደሩ እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ ስለነበር ነው። የመከላከያ ሰራዊት ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ኮማንድ ፖስቶች በተለያዩ አካባቢዎች ማቋቁሙንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአዲስ አበባ መግቢያ በሮች ገዳይ ቡድን ተሰማራ - ኮምሽነሩ ጉድ አፈሉ “በበህርዳር በፋኖ ተከበናል” | ቀጥታ ቪዲዮ ከግንባር | “አላማ አለን! ሕዝቡ ከጎናችን ነው” | “ከተረኝነት ነፃ የሆነች ሀገር እንሰራለን“
Share