የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

የጠ/ሚር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በብራስልስ የሚያደርጉትን ስብሰባ በመቀጥል ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጆን-ክላውድ የንከር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ:: ሁለቱ ወገኖች ሶስት የፋይናንስ ስምምነቶች ሲፈረምም ተገኝተዋል:: እነዚህም የ 130 ሚሊዮን ዮሮ ስምምነቶች ዘላቂ ሀይል ማመንጨት: አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ስራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ይውላል::

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

ሌላ በኩል ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ስብሰባ አካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀው በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ እየተንፀባረቀ ያለውን የመደመር አዲስ የፍልስፍና መሰረት አካፍለዋል። በሀገሪቱ የሚታየውን ለውጥ በተለይም ዲሞክራሲያዊ ምርጫን ለማመቻቸት እና አዲስ ዲሞክራሳዊ ባህልን ለማሰደግ በማገዝ ረገድ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነጥቦችንም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኮሚሽን መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነትና የወደፊት ትብብርን ያስታወሱት ኃላፊዋ መንግስት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ አውሮፓ እንደተገነዘበች እና ህብረቱ ሙሉ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ፈቃደኝነት አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መከላከያ ሙሉ መረጃውን አብሮ (በሚስጥር) ተከታትሏል

1 Comment

Comments are closed.

Share