የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል

ጥር 19 ቀን 2011 ዓ/ም የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል። በውይይቱ ኮሚቴው የሄደባቸውን ርቀቶችና ያጋጠሙትን ፈተናዎች ያቀርባል። ምሁራን ስለወልቃይት ከጥንት እስከ ዛሬ ያለውን እውነታ ያስረዳሉ ተብሏል። ስብሰባውን ለማካሄድ እንዲቻልም የባለሃብቶችን ድጋፍ ኮሚቴው ጠይቋል፡፡ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፊርማ የተፃፈው ድጋፍ መጠየቂያ ጥሪ የሚከተለው ነው፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

ኮሚቴው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የህዝብ መድረኮችን በመክፈት ተጨቁኖ የነበረውን ህዝባችን ነፃ ለማውጣት እየሰራ ያለ ኮሚቴ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአዲ አበባ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራምና የውይይት መድረክ ለጥር 19 ቀን 2011 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ስላዘጋጀን ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን የተለያዩ ወጪዎችን መሸፈን እንዲቻል ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡ እርስዎም የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ትህትናና አክብሮት ጋር እንጠይቃለን፡፡ 

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አየለ የኮሚቴው ሊቀመንበር

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ለአሸባሪው ህወሓት ፍፃሜ

1 Comment

  1. ጊዝያዊ ንዴት ማብረጃ ሊሆን ይችላል :: ሆኖም ንዴት የሚበርደው ጄኖሳይድ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሰሩ በሰሩት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ስናይ ነው:: ገንዘብ በማባከን ብቻ ሳይሆን ጄኖሳይድ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከስ ይገባዋል::

    https://qz.com/africa/1311288/ethiopia-amhara-persecution-stands-in-way-of-abiy-ahmed-reform-agenda/

    http://moreshinfo.com/archives/3224

    https://welkait.com/?p=13395

Comments are closed.

Share