January 24, 2019
4 mins read

መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ

93808

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት በዛሬው እለት በአምቦ ከተማ ባዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርአት ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና ኦነግ ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ማቆም ውሳኔ አሳልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኦነግ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ውስጥ ካለበት ጫካ ወጥቶ ወደ ካምፕ እንዲገባም ውሳኔ አሳልፈዋል።

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

ሁለቱ አካላት ከስምምነት የደረሱባቸውን ዝርዝር የውሳኔ ነጥቦችንም ይፋ አድርገዋል፡፡

የስምምነቱን ዝርዝር ነጥቦች አቶ ጃዋር መሀመድ ሲዘረዝሩ ከዛሬ ጀምሮ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ጦርነት መቆሙን፣ ወደ ግጭት የሚያስገቡ ትንኮሳዎችን ሙሉ በሙሉ መከልከሉን እንዲሁም አንዱ በሌላው ላይ ከዚህ በኋላ መግለጫ ማውጣት ሙሉ በሙሉ መከልከሉንም ገልፀዋል። የኦነግ ሰራዊት ካለበት ቦታ በሙሉ ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ መወሱን እና ይህም ከበቂ ጥበቃ ጋር በክብር አቀባበል ወደ ካምፕ እንዲገቡ እንዲደረግ መወሰኑንም ገልፀዋል። ‹‹ሰራዊቱን ወደ ካምፕ የማስገባት ስራም በ20 ቀን ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለበት ተወስኗል›› ያሉት አቶ ጃዋር፥ ከእዚህም ውስጥ 10 ቀናት ዝግጅት የሚደረግበት፤ ቀሪው 10 ቀናት ደግሞ ሰራዊቱ ወደ ካምፕ የሚገባበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት የኦነግ ሰራዊትን ወደ ካምፕ የማስገባት ሂደቱ በሶስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ የሚካሄድ፥ በዚህ መሰረት በመጀመሪያ ወደ ወረዳ ከተሞች እንዲሰባሰቡ፣ በመቀጠል ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እንዲገቡ ማድረግ በመጨረሻም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት አቀባበል የሚደረግ ይሆናል፡፡ በዚህ ወቅት ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል ላይ መንግስት ህግን የማስከበር ስራ እንዲሰራ ተፈቅዶለታል ተብሏል። የኦነግ ሰራዊት ካምፕ ከገባ በኋላም አጠቃላይ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጎ የመንግስት የፀጥታ አካላት መቀላቀል ለሚፈልጉ እንደሚያሟሉት መስፈርት እንዲቀላቀሉ መወሰኑንም የፖለቲካ ተንታኝ እና አክቲቪስት አቶ ጀዋር መሃመድ አስታውቀዋል። ከዚህ ውጭ ያሉት ደግሞ እንደየፍላጎታቸው በፈለጉት ዘርፍ ስልጠና ወስደው እንዲሰማሩ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን ወደ ካምፕ የገባው ሰራዊትን አያያዝም በየጊዜው የሚጎበኝ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አቶ ጃዋር የኦነግ አባላት እስካሁን ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተናግረው የተዘረዘሩትን ስምምነቶች ጥሶ የተገኘ ማንኛውም አካል ግን ላጠፋው ጥፋት ተጠያቂ እንደሚደረግም አስጠንቅቀዋል፡፡ እንዲሁም የኦነግን የታጠቀ ሰራዊት ትጥቅ ለማስፈታት እና ሰራዊቱን ወደ ካምፕ ለማስገባት እንዲሁም ሌሎች ስምምነት ላይ የተደረሱ ጉዳዮችን ለማስፈፀም 71 አባላት ያለው የቴክኒክ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፥ የቴክኒክ ኮሚቴውም ከምሁራን 11፣ ከአባ ገዳዎች 54፣ ከኦዲፒ 3 እንዲሁም ከኦነግ 3 አባላት ያለው ነው።

93805
Previous Story

ድሬዳዋ ዛሬ በጎማ ጭስ ስትታጠን ዋለች

93811
Next Story

አዴፓ ከዳተኝነት፣ ከለዘብተኝነትና  ከይሉኝታ ፖለቲካ ወጥቼ በቁርጠኝነት የህዝባችንን ጥቅም ለማረጋገጥ እየተንቀሳቀስኩ መሆኑ ይታወቅልኝ አለ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop