የአማራ ክልል ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ነቅተው እንዲጠብቁ ጀነራል አሳምነው ጽጌ አሳሰቡ

የአማራ ክልል ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ነቅተው በመጠበቅ በሃገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል አሳምነው ጽጌ ትናንት ከወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ገለጹ::

https://youtu.be/J8BZqY2t65c

ባለፉት ዓመታት አማራው በክልሉ ውስጥም ሆነ በሌሎች ክልሎች ማንነቱን መሰረት ያደረጉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፀሙበት መቆየታቸውን የገለጹት ጀነራል አሳምነው ችአሁን ላይ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ሊያረጋግጥ የሚችል የለውጥ ብርሃን እየታየ ቢሆንም ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት ለውጡን ወደ ኋላ ለመመለስ እየተንቀሳሱ መሆኑን  ገልጸው መንግስት ችግሩን በሰከነና ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመፍታት ብርቱ ጥረት እያደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለቀናት ታግተው የተለቀቁት የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ‹‹እኔ ፖለቲካ አይመለከተኝም፣ ያገቱኝ ሰዎችም የተሳሳቱ ይመስለኛል›› አሉ
Share