ለገሠ ወ/ሃና
ታህሳስ 26/2011 ዓም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጎራ ብየ የእስር ቤት ሀላፊዎችንና የሜቴክ ሀላፊዎች ጉዳይ በከፊል ተከታትየ ነበር እኔ ተከሳሽ ሆኜ ከ20 ጊዜ በላይ የቀረብኩበት 4ኛ ችሎት ፍትህ ፈልጌ ሳይሆን ሁኔታዎች አስገድደውኝ በተከሳሽነት ቦታ የተቀመጥኩት ወንበር ላይ የቅሊንጦ አለቆች ተቀምጠው ሳይ አይ ጊዜ አልኩኝ እያንዳንዳችን የጊዜ ባሪያዎች ነን ትላንትና ጊዜ ጌታ አድርጓቸው እኔንና ብዙዎች በካቴና ጠፍረው ያስቀመጡበት ወንበር ላይ ዛሬ እነሱ ተቀመጡበት አቀማመጣችን ግን ይለያያል እኛ ህዝብ ነፃ ለማውጣት ታግለን እነሱ የሀገር ሀብት መዝብረው እና ሰብዓዊ መብት ጥሰው ነው ።
እነሱም ጊዜ ባሪያ አድርጓቸው እኛን ባስቀመጡት ደረቅ ወንበር ላይ ጊዜ አስቀመጣቸው ጊዜ ብዙ ያሳያል ።
እኛና እነሱ ተጠርጣሪ ተብለን ስንታሰርና ፍርድ ቤት ስንቀርብ ልዩነታችን የሰማይና የምድር ያክል ነው ልዩነታችንን ከዚህ በታች እንዳለው ነው ።
እኛ
* በማዕከላዊ እና በሌሎች ማሰቃያ እስር ቤቶች አካላችን እስኪጎድል ተደብድበናል
*እጃችን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስከ እከተፈታንበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት ፣ ህክምና ፣ ወዘተ ከእጃችን ካቴና ወጥቶ አያውቅም
* በእነሱ ቁጥጥር ስር ወድቀን ከእነሱ እጅ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ሽፍን ጫማ አድርገን አናውቅም
* የኛ ቤተሰቦች እስር ቤት ወይም ፍርድ ቤት በሚመጡት ጊዜ ወከባ ግልምጫ ማስፈራሪያ ወዘተ ይደርስባቸዋል ከኛም ጋር ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ በቃልም ሆነ በምልክት መነጋገር አይፈቀድም
* ፓሊስና አቃቤ ህግ ያልሰጠነውን ቃል እንደሰጠን ተደርጎ ወይም በግዳጅ ቃል ተወስዶ ያላደረግነውን እንዳደረግን ተደርጎ ክስ ይቀርብብናል
* ከእስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት ስንቀርብ የእስር ቤቱ ማህተም ያላረፈበት ወረቀት ይዘን መውጣት አንችልም
* መድሃኒት ለመውሰጃ የሚሆን የታሸገ ውሃ /ሃይላንድ / ውሃ ፍርድ ቤት ይዘን መሄድ አንችልም
* ለእኛ የዳኛ የአቃቤ ህግ የመርማሪ ስም አይገለጽልንም
*አቤቱታ ስናቀርብ ዝም በል እንባላለን
* ለእኛ የሚቆምልን ጠበቃ አጥተን እራሳችን እንከራከራለን ወዘተ
እነሱ
* ምንም አይነት አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው በክብር ተይዘዋል
እጃቸው ሳይታሰር ዘና ብለው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ
* እነሱ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ
* ዝንጥ ብለው ለምሳሌ ኮፍያ ፣ ሽፍን ጫማ ወዘተ አድርገው ቀርበዋል
* ከቤተሰቦቻቸው ጋር ፍርድ ቤት ግቢ ችሎት ውስጥ ሳይቀር እንደፈለጉ ያወራሉ
* ፓሊስ ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም ብሎ ለችሎት አቤቱታ ሲያቀርብ እነሱም ቃል ያለመስጠት ህገመንግስታዊ መብታችን ነው ብለው ችሎት ላይ ይናገራሉ
* ከእስር ቤት ወረቀት እስኪርብቶ ወዘተ ይዘው ሲመጡ አይጠየቁም
*የታሸገ ውሃቸውን ይዘው ችሎት ውስጥ እየጠጡ ያወራሉ *
* ችሎት ሲሰየም ዳኛ አቃቤ ህግ ይገለጽላቸዋል መርማሪ ፓሊስም ስሙን ይናገራል
* አቤቱታ ሲያቀርቡ ተከብረው ሀሳብዎትን ይቀጥሉ ይባላሉ በፍጹም ነፃነት የፈለጉትን ያክል ያወራሉ
* እነሱ አንድ ተጠርጣሪ አንድ የመንግስት ወይም ተከላካይ ጠበቃ አቁሞ በግሉ ሁለት ወይም ሶስት ጠበቃ ይዞ ይቀርባል ወዘተ
እኛና እነሱ ልዩነታችን ብዙ ነው ቀሪውን በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ ።