“ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ መውጣት አለበት” – ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ

ሕወሃት ለሁለት በተከፋፈለበት ወቅት በአቶ መለስ ዜናዊ ከመከላከያው ኢታማዦር ሹመነታቸው የተባረሩት ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ “በአማራ ልሂቃን የሚነሳው የህገ መንግስት ተቃውሞ መሰረተ-ቢስ ነው ፤ ህገ-መንግስቱ ሲፀድቅ ህዝብ ተሳትፎበታል ፤ እንደውም በየጣብያው ምን ያህል ህዝብ እንደተወያየበት ሁሉ ስታቲክስ ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ነበር” ሲሉ ከዋልታ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናገሩ::
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
“አሁን እየሆነ ያለው በለውጥ ስም ጥላቻ ነው እየተንጸባረቀ ያለው ይህ መሆን አልነበረበትም ፤ ምክንያቱም አሁን እየገዛ ያለ ሃይል ግልጽ የሆነ የመዳረሻ ፍኖተ ካርታ የለውም ፤ ይህ ትልቁ ችግር ነው። በቅርብ ግልጽ የሆነ ሁሉኑም ያሳተፈ ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ መውጣት አለበት።” ያሉት ጀነራሉ “ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ከማንም በላይ የትግራይ ህዝብ ነበር ደስተኛ የሆነው ፤ “ባልበላሁት ባልጠጣሁት የምወቀስበት ምክንያት ከንግዲህ አይኖርም ፤ አሁን ነጻ ወጥቻለሁ” ነበር ያለው። ነገር ግን ቀስ በቀስ የትግራይን ህዝብ አንገት የሚያስደፉ ንግግሮች ተጀመሩ ፤ የትግራይ ህዝብ ብበአዴን ሰዎች አካኪ-ዘራፍ ሲባልበት ፌደራል መንግስት ዝም አለ፤ በትግሉ፣ በላቡ የተሰራ መንገድ ሲዘጋም ፌደራል መንግስት ዝም አለ ፤ የግሌ አቋም ይቅር፣ ህዝቡ ግን ትክክል አይደለም ብየ አላስብም።” ብለዋል::
በአማራና በትግራይ ክልሎች አዋሰኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች መንስዔ በ1984 ዓ.ም የተደረገው ህዝብን ያላማከለ አከላለል እንደሆነ የአዴፓ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ደሴ ጥላሁን ለጀርመን ድምጽ ሲናገሩ ሰምተናል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  Birtukan Mideksa urges compatriots to stand in unison

1 Comment

  1. Leper! Your hatred permeates your words. You have no moral or courage capabilities even to mention the name Amhara. Stop your diarrhoea or you will bite the dust!!!

Comments are closed.

Share