በበዓላት በሚኖረዉ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት የተነሳ ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ለማስቀረት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

በበዓላት በሚኖረዉ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት የተነሳ ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ለማስቀረት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
አገልግሎቱ በፕሬስ መግለጫው እንዳስታወቀው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር በመተባበር ለሚፈጠረው የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሰጥ የጋራ ተጠባባቂ ኮሚቴ አቋቁሜያለሁ ብሏል።

ፋብሪካዎችና ሌሎች የከፍተኛና የመካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ከታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ንጋት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ንጋት 12፡00 ሰዓት ድረስ ኃይል ቀንሰው እንዲጠቀሙ ትብብር ጠይቋል።

በኅብረተሰቡ በኩልም ኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ሰዓትን በምሽት እና ሌሊት በማድረግ የሃይል እጥረትን ለመከላከል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በደቡብ ክልል ዘጠኝ ሰዎች በድንጋይና በዱላ ተወግረው ተገደሉ
Share