January 4, 2019
3 mins read

በሀረሪ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ የወንጀል ድርጊት መባባስ በስጋት እንድንኖር አድርጎናል ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች ገለጹ

93544

በሀረሪ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ የወንጀል ድርጊት መባባስ በስጋት እንድንኖር አድርጎናል ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች ገለጹ። በሌላ በኩል በክልሉ እየተፈጸሙ የሚገኙ ወንጀሎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ፍትህና ጥታ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ የሱፍ ገልጸዋል።
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s

በክልሉ በህገ ወጥ መንገድ መኖርያ ቤትን ሰብሮ የመግባት፣ድብዳባ፣ ስርቆትና የጎዳና የነዳጅ ግብይት ድርጊት መባባስ ስጋት አሳድሮብናል፤ በከተማው ያለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ከታሪፍ በላይ ክፍያ መፈጸም፣የጎዳና ላይ ንግድ መባባስ ደግሞ ነዋሪውን ለምሬት እየዳረገ ይገኛል::
የከተማው ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ፎዚያ ከበደ እንደሚናገሩትበክልሉ ከቅርብወራትወዲህ ቤት ሰብሮ የመግባትወንጀልእየጨመረመጥቷል፤ ለዚህም ለ3 ዓመታት ክፍያ ፈጽሜበት የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤትን ግለሰቦችበጉልበት ሰብሮው ገብተውበት እየኖሩበት ነው።

የክልሉ መንግስትድርጊቱንየፈጸሙትን ግለሰቦች ለመያዝምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እያከናወነ አይደለም፤ ይህም ቅሬታ አሳድሮብናል የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጥልን ሲሉ ምሬታቸውን አቅርበዋል::

በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ የስርቆት፣ የህግ ጥሰት፣ስርዓት አልበኝነትና ሌሎችተግባራት እየተስፋፉ ይገኛሉ ያሉት የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ዩስፍ ህገወጥ ድርጊቶችንለመከላከልና የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎችን እየተከናወነ ይገኛል።

በተለይ በተሳሳተ መንገድ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ሰብረው የገቡ ግልሰቦችን የማስወጣት፣ አደጋን የሚስከትሉ ህግ ወጥ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን እና ሌሎችን ተግባራት ለመከላከልና ክልሉ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ ከወጣቶች፣ከአገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት አባቶችና ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዶ ከስምምነት ተደርሷል።

በአንዳንድ የፖሊስ አባላት የሚስተዋሉ ችግሮች መነሻው አመራሩ በፈጠረው የመልካም አስተዳደር ችግር ነው ያሉት አቶ አህመድ በአሁኑ ወቅት ግን የነበሩት ችግሮች እየተቀረፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

27
Previous Story

የሀይማኖት አባቶች ‹‹ለ27 ዓመት ያክል የተዘራ ዘር ለችግር ዳርጎናል›› አሉ

93548
Next Story

በበዓላት በሚኖረዉ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት የተነሳ ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ለማስቀረት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop