የዛሬው የአዲስ አበባ ንፋስ መብራትና ውሃ አቋረጠ

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ነፋስ ሲነፍስ ውሏል፡፡ ሁኔታው በከተማው አብዛኛው አካባቢ ለረጅም ሰአታት መብራት እንዲቋረጥም አስገድዶ ነበር፡፡ የተከሰተው ንፋስ በመዲናዋ የሚገኙ 43 የውሃ መግፊያ ጣቢዎችን ሀይልም አቋርጧል። ይህን ተከትሎም
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
በበርካታ የመዲናዋ አካባቢዎች ውሃ መቋረጡ ታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት በየካ አባዶ፣ ቦሌ አራብሳ፣ አያት፣ በአቃቂ ጥልቅ ጉድጓዶች ከክፍል 1 እስከ ክፍል 4 የውሃ መግፊያ ጣቢያዎች ሃይል በመቋረጡ፥ ኮዬ ፈጨ፣ ሳሪስ ጎተራ፣ ላፍቶ፣ ጀሞ፣ ሳርቤት፣ ቤተል፣ ለቡ፣ ቄራ፣ ጎፋ፣ ስቴዲየም፣ ጦር ሃይሎች፣ ልደታ፣ መርካቶ በከፊል፣ ቦሌ አየር መንገድ አካባቢ ውሃ መቋረጡን ሰምተናል። በተጨማሪም በተፈሪ መኮንን፣ ሽሮ ሜዳ፣ አር 1 እና አር 2 የውሃ መግፊያ ጣቢያዎች ላይ ሃይል በመቋረጡ ምክንያት፥ በሽሮ ሜዳ፣ መነንና ስድስት ኪሎ አካባቢ ውሃ ሲቋረጥ በተመሳሳይ አዲሱ ገበያ በላይ ዘለቀ የውሀ መግፊያ ጣቢያ በተመሳሳይ መልኩ ሃይል መቋረጡን ተከትሎ ከፒያሳ እስከ ድል በር በግራና ቀኝ አካባቢ የውሃ ስርጭት ተቋርጧል፡፡ በራስ ሀይሉ የውሃ መግፊያ ጣቢያም በተከሰተው የሀይል መቋረጥ ሳቢያ በጳውሎስ፣ ሩፋኤልና ኮልፌ ጠሮ አካባቢ ውሃ ተቋርጦ ውሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የከንቲባ አዳነች አበቤ ... አደገኛ ሴራ እና የመፈንቅለ መንግስት ስጋት
Share