በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት “የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲሰፍን እየሰራሁ ነው; የሕዝቡ ድጋፍ ያስፈልገኛል” አለ

በአቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት “የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲሰፍን እየሰራሁ ነው; የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲረጋገጥ የህዝቡ ተሳትፎ መጠናከር አለበት” ሲል በክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫው አስታወቀ::
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
“የመልካም አስተዳደር ችግርን መነሻ በማድረግ በተደረገ ትግል ከፍተኛ መሰዋዕትነት ተከፍሎ የኦሮሞ ህዝብ መብት መረጋገጥ ጀምሯል:: በአሁኑ ወቅትም የህዝቡ ተስፋ እየለመለመ መጥቷል” ያለው የክልሉ መንግስት፥ “ይሁን እንጂ ስልጣን ከእጃቸው የወጣ አካላት በየስፍራው ሴራ በመሸረብ አሁን የተጀመረው ለውጥ እንዲደናቀፍ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው:: የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር የደረሰው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩም የኦሮሚያ ክልል ሰላም እየደፈረሰ ነው” ብሏል::

“በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በምእራብ ጉጂ ዞን ውስጥ በየእለቱ የሰው ህይወት እያለፈና ንብረት እየወደመ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፥ መንገዶች በመዘጋታቸውና የንግድ እንቅስቃሴ በመቆሙ ህዝቡ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጠ ነው በማለት አስረድቷል::

“ወቅቱ ስልጣንን ማእከል በማድረግ እርስ በእርስ ድንጋይ የምንወራወርበት አይደለም ያለው የክልሉ መንግስት፥ ከሁሉም በፊት የህዝቡን ሰላም በማስቀደም ችግሮቻችንን የምንቀርፍበት ጊዜ ላይ ነን:: ለአንድነት እና ለሰላም ያለው አማራጭ ህግን ማክበር እና ማስከበር ነው፤ ለዚህ ደግሞ መንግስት ግዳጅ ስላለበት የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲሰፍን እየሰራ ነው::ችለዚህም ህዝቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብሏል;;

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በነቀምቴ፣ ጊምቢና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሰዎች በኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ ቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ቤተሰቦች እንደሚሉት ከሆነ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከኦነግ ጋር ተያያዥነት አላቸው ተብሎ በመጠርጠሩ ነው፡፡
የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ ከአባ ቶርቤ ውጭ ማንንም አልያዝንም ብሏል፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወታደሩ ራሱን፣ ሕዝቡን እና ሀገሩን ይታደግ

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ምክር ቤት እና የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባላት በደብረዘይት ቢሾፍቱ ከተማ ባደረጉት የልምድ ልውውጥ ስብሰባ የሁለቱን ክልሎች ሕዝብለሕዝብ ግንኝኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰሩ መናገራቸውን በኦሮሞ ብሮድካስት ኔትወርክ ላይ ተዘግቦ አይተናል::

Share