ዶክተር አብይ 3700 መምህራንን ሊያነጋግሩ ነው

ሀገር አቀፍ የመምህራን ጉባኤን በማስመልከት ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ከ3700 በላይ መምህራንን በፅህፈት ቤታቸው ሊያነጋግሩ ነው፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በውይይቱ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡ የውይይቱ ዓላማም
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
ሀገሪቷ በምትፈልገው መንገድ ተማሪዎችን ለማብቃት መምህራን ትልቅ ድርሻ ስላላቸው በዚህ ዙሪያ ለመመካከርና ሀሳብ ለመለዋወጥ ነው፡፡ እንዲሁም የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በማስቀጠል ሂደት መምህራን የድርሻቸውን እንዲወጡና የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥና ብቁና ሀገር ተረካቢ ዜጎችን በማፍራት ረገድ ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡

በሌላ ዜና ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በጠቅላይ አቃቤ ህግና በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች ድንገቴ ጉብኝት አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የመሰሉ ድንገቴ ጉብኝቶች በሌሎች መስሪያ ቤቶችም እንደሚቀጥሉና ይኸውም መስሪያ ቤቶቹ በእቅዳችው መሰረት በአስፈላጊው ፍጥነት እየፈፀሙ መሆኑን ለማየት ነው::
ጉብኝቱ ሁለቱም መስሪያ ቤቶች የመስሪያ ቦታን በማስተካከል ውጤታማነትንና አፈፃፀምን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም ያለመ ነው::
እንደ አገር ለረጅም ጊዜ በግጭት ውስጥ ቆይተናል ያሉት ጠ/ሚሩ አሁን ጊዜው እይታችንን የማስተካከልና የኢኮኖሚ ልማታችን ላይ ነዉ ማተኮር ያለብን ሲሉ አጠንክረው ተናግረዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ -ከአበበ ገላው
Share