ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው  መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ

January 3, 2019

ከኤርትራ ድንበር ጓዙን ጠቅልሎ ሲሄድ ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው  በሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ቀጭን ትእዛዝ መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ:: ሰኞ ዕለት መንገድ ተዘግቶባቸው ሕዝቡ ማብራሪያ ጠይቆ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን መከላከያው ማክሰኞ ጠዋት መንገዱን አስከፍቶ ሲሄድ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ምንም ችግር እንዳልገጠመው ሰምተናል::

https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY

ከዛላምበሳ ግምባር የጦር መሳሪያ ጭነው ወደ መሀል ሀገር ሲንቀሳቀሱ የታገቱ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች ተለቀዋል  በሚል በሕወሓት ሰዎች በኩል የሚነዛው ወሬ የመከላከያ ሰራዊቱን አቅም ለማሳነስ መሆኑን የጠቆሙት እነዚሁ ምንጮች የመከላከያ ተሽከርካሪዎቹ መንገዱን አስከፍተው ነው የሄዱት ብለውናል::

93502
Previous Story

በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ አንዲት እናት አራት ሴት ልጆችን መገላገሏ ተሰማ፡፡ 

93510
Next Story

የውሃና መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴሩ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትን ወቅታዊ የግንባታ ደረጃ ይፋ አደረጉ

Go toTop