January 3, 2019
2 mins read

በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ አንዲት እናት አራት ሴት ልጆችን መገላገሏ ተሰማ፡፡ 

93502

በትላንትናው እለት በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ አንዲት እናት አራት ሴት ልጆችን መገላገሏ ተሰማ፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY

ወ/ሮ ላቀች መዋህኝ የተባለችው የእነማይ ወረዳ ፈለገ ሰላም ነዋሪ ትላንት ታህሳስ 24 ከሌሊቱ 11፡30 ወደ የትመን ጤና ጣቢያ በመሄድ እስከ ጥዋቱ 12፡30 ድረስ 4 ሴት ህጻናትን በሰላም መገላገሏን አብመድ ዘግቧል፡፡

ወ/ሮ ላቀች መዋህኝ ከዚህ በፊት 4 ልጆችን እንደወለደችም ዘገባው አስረድቷል፡፡ እንደዘገባው ህጻናቱ በቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲሆኑ እናትዬዋ ሙሉ ጤነኛ ብትሆንም እስካሁን አይነት ክስተት በተቋሙ ተከስቶ የማያውቅ በመሆኑ በከፍተኛ ባለሙያ እንድትታይ ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ተልካለች፡፡ ያዋለዷት የህክምና ባለሙያ አቶ አባይነህ ሙላት ሲናገሩ ‹‹በህክምና ስራየ አንዲት እናት አራት ልጆችን ስትወልድ የመጀመሪያዬ ነዉ፡፡ ነገር ግን ቀድሞ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት በማድረጌ ያለምንም ችግር አንዲት እናት አራት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡ እንደዚህ አይነቱ ክስተት የመፈጠር ሁኔታዉ 0 ነጥብ 01 ከመቶ በመሆኑ ብዙም የተለመደ አይደለም›› ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ ሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ በተመሳሳይ አንዲት እናት አራት ልጆችን ተገላግላለች፡፡

93499
Previous Story

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደለሳ ቡልቻ በታጠቁ ሀይሎች ተጠልፈው መወሰዳቸው ተሰማ::

93507
Next Story

ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው  መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop