የውሃና መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴሩ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትን ወቅታዊ የግንባታ ደረጃ ይፋ አደረጉ

January 3, 2019
2 mins read
93510

የውሃና መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴሩ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትን ወቅታዊ የግንባታ ደረጃ ይፋ አደረጉ።

https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY

በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት ዋናው ግድብ የሲቪል ስራ 80 በመቶ መጠናቀቁንና የኃይል ማመንጫዎች የሲቪል ስራ በአማካይ 66 በመቶ ተማለቁን አስረድተዋል፡፡ የጎርፍ ማስተንፈሻ የሲቪል ስራዎች ደግሞ 99 በመቶ፣የኮርቻው ግድብ ስራዎች 93 በመቶ፣ የስዊችያርድ የሲቪል ስራዎች 33 በመቶ መጠናቀቁን ገልፀው በአጠቃላይ የሲቪል ስራው 82 በመቶ ያህሉ መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡

በሜቴክ ተይዞ የነበረውን የኤሌክትሮሜካኒካል ስራዎችን በተመለከተ ሲያስረዱ ደግሞ ‹‹የዘጠኝ ተርባይን እና ጄኔሬተር በአብዛኛው የተከናወነ ቢሆንም የተወሰኑት የተርባይንና ጄኔሬተር አካላት በሀገር ውስጥ ይመረታሉ ተብለው የታሰቡት አልተመረቱም›› ብለዋል፡፡ አጠቃላይ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎች አፈጻጸም 25 በመቶ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ የሃይድሮሊክስ ስቲል እስትራክቸር ስራዎች አፈጻጸም 13 በመቶ ብቻ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በሜቴክ የተሰራው ስራ 23 በመቶ ብቻ ሲሆን ፕሮጀክቱ አሁን የደረሰበት የግንባታ ደረጃም 65 በመቶ መሆኑን ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ አብራርተዋል።

93507
Previous Story

ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው  መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ

93513
Next Story

ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በታጣቂዎች ተዘግቶ የነበረው የካማሸ ዞን መንገድ መከፈቱን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop