እየተደረገ በነበረው ትግል በሙያቸው የወገናቸውን ድምጽ በማሰማት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው:: ይህን ተከትሎም ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ በወዳጅ ጓደኞቻቸው አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል::
ይሁኔ እና መሐሪ ታህሳስ 27 2011 በጎንደር በአፄ ፉሲል ስታዲየም የመጀምሪያ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከዚያም በተለያዩ ከተሞች እየተዟዟሩ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል::
መሐሪ “እግዚአብሔር ይመስገን ከጀግና ህዝብ መሀል ልንገኝ ነው ነው እኔና ይሁኔ:: በDMV የምትገኙ እንዲህ ያማረ ሽኝት ስላረጋችሁልን ውለታችሁን እግዚአብሔር ይክፈልልኝ” ብሏል::
https://www.youtube.com/watch?v=HxjVbnkoygk