ኦምሃጅር ከተማ ቀን እየወጣላት ነው

በደቡባዊ ምእራብ ኤርትራ የምትገኘውና ሱዳንና ኢትዮጵያን የምትዋሰነው ኦምሃጅር ከተማ ቀን እየወጣላት ነው ተባለ፡፡
የኤርትራ መንግስታዊው የዜና አውታር እንደዘገበው ይህች ከተማ ወደ9500 ያህል ነዋሪዎች ያሏት ስትሆን በአሁኑ ወቅት በሰቲት ድልድይ አማካኝነት ኢትዮጵያና ኤርትራን እያገናኘች ነው፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎችም በአዲሱ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ከማንም በላይ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተስፋ መሰነቃቸው ተዘግቧል፡፡ ለአካባቢው ነዋሪዎች መስኖ እርሻ እንዲያገለግል ታስቦ ከ8 አመት በፊት ባደሚት የተባለ ግድብ የተሰራላት ኦምጁሃር እስካሁን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ባትሆንም መንግስት አሁን ካላት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር በጣም በቅርቡ መብራት እንደሚያስገባለትም ተነግሯል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=cKOwRaexXZ4&t=4s

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ አካሄደ የወቅቱን ሁኔታ ገምግሞ የጋራ ትግሉንለማጠናከር ተጨማሪ መመሪያ ሰጠ
Share