February 19, 2018
5 mins read

አገራዊ ቀውስና  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሪዎች ሚና በታሪክ                                                                                                                                                                                                  

መንግሥቱ ጎበዜ
ሉንድ ዩንቨርሲቲ፣ ስዊድን                                                          

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሪዎች በአገር ግንባታ፣ የሕዝብ ትሥሥርና አንድነት በመፍጠር፣ አገርን ከጠላት በመከላከል፣ የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ  በመሆን፣ እንዲህ እንደዛሬው አገራዊ ቀውስ ሲፈጠር ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች የነበራቸውን ከፍ ያለ ሚና ከታሪክ እንገነዘባለን። በቀደመው ጊዜ የቤተክርስቲያን አባቶች በአገራዊ ጉዳዮች ከእውነት ጋር የሚቆሙ፣ ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ፣ ተናግረውም የሚደመጡ ነበሩ። መሪ እንጅ ተከታይ ፤ ሽማግሌ እንጅ ታራቂ፣ ችግር ፈች አንጅ ችግር ፈጣሪ አልነበሩም። በተለይ ልክ እንደዛሬው ጊዜ የከፋ አገራዊ ቀውስ ሲከሰት የቤተክርስቲያን አባቶች ከፊት በመቆም ነገሮች ፈር እንዳይለቁ፣ አቅጣጫ እንዳይስቱና አገር ችግር ላይ እንዳትወድቅ የከፈሉትን መስዋዕዋትነት የሚመሰክሩ በርካታ ማሳያዎች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።

ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት በዛጉዬ ሥርወ መንግሥት ማብቂያ አካባቢ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች ምክኒያት በተከስተው አለመግባባትና ግጭት  አገርን ከባድ ቀውስ ውስጥ የሚያስገባ አደጋ ተፈጥሮ ነበር። በመሆኑም የደብረ ሀይቁ ገዳም መስራች አባ ኢየሱስ ሞዓ እና የደብረ ሊባኖሱ አባት አቡነ ተክለ ሐይማኖት ባደረጉት ከፍተኛ መንፈሳዊ ተጋድሎና አባታዊ ጥረት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ በመደረጉ ሊመጣ ይችል የነበረው አደጋ ከስማል።

በጎንደር ዘመነ መንግሥት በካቶሊክ ሚስዮናውያን ሰርጎ ገብነትና በአጼ ሱስንዮስ አዋጅ ምክኒያት የተፈጠረው ከፍተኛ ደም መፋሰስና ትርምስ ሊቆም የቻለው የቤተክርስቲያን  አባቶች ባደረጉት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ነበር። በተለይም ደግሞ ከታላቁ የማኅበረ ስላሴ አንድነት ገዳም የመጡ አበው  ከአጼ ሱስንዮስ ወደ አጼ ፋሲለደስ የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ ተጽእኖ በማሳደር በአገር ላይ አንዣቦ የነበረውን አደጋ በአጭሩ ቀጭተውታል።

የቤተክርስቲያን አባቶች በአድዋ ጦርነት ወቅት ከመነሻው እስከመጨረሻው፣ ከዘመቻው እስከ ድሉ፣ ከዋዜማው እስከጦርነቱ በመሪነትና በተሳታፊነት ነበሩ፡፡ ለአድዋ ድል መገኘትም የነበራቸው ሚና እጅግ የላቀ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ከጾም፣  ከጸሎትና ከመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት ባሻገር እነዚህ አባቶች ሕዝቡን በመቀስቀስ፣ አመራር በመስጠት፣ አብረው በመዝመት፣ የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖር በማድረግ፣ በጦርነቱ በመሳተፍ፣ መረጃ በመስጠትና በማስቀመጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል፡፡

በ1953  ዓ. ም የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከትሎ ሊከሰት ይችል የነበረውን አገራዊ ትርምስ በማስቆም በኩል ፓትርያርክ አባ ባስሊዎስ የነበራቸው የላቀ አስተዋጽኦ የሚታወስ ነው።ውጤቱ በፖለቲከኞች ሚዛን በምንም መንገድ ይታይ የቅዱስነታቸው ሚና ግን ጎልቶ የታየበት ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ሁለተኛው ፓትርያርክ ታላቁ አባት አቡነ ቴዎፍሎስ  የስልሳ ስድስቱን አብዮት ተከትሎ የመጣው የደርግ መንግስት ሰለባ የሆኑት ከእውነት፣ ከሕዝብና ከአገር ጋር በመቆማቸው ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዛሬስ

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop