ሼህ መሃመድ አላሙዲ ከዓለም ሃብታሞች 65ኛው ሆኑ

(ዘ-ሐበሻ) የ8 ልጆች አባት የሆኑት ሼህ መሀመድ አላሙዲ ፎርብስ የተባለው መጽሔት በየዓመቱ ከሚያወጣው የሃበታሞች ደረጃ ከ2013 የዓለማችን ትላልቅ ቢሊየነሮች መካከል 65ኛው መሆናቸውን አስታወቀ። ከሳዑዲ አረቢያዊ አባታቸው እና ከኢትዮጵያዊ እናታቸው የተወለዱት አላሙዲ ገንዘባቸውን ኢንቨስት ማድረግ የጀምሩት በ1970ዎቹ እንደሆነ ያስታወቀው ፎርብስ ኒውስ በኢትዮጵያም ትላልቅ ገቢ በሚያስገኙት የወርቅ፣ የሲሚንቶ፣ የእርሻና የሆቴል ሥራዎች ላይ እንደተሰማሩ መጽሔቱ ገልጿል።

የ68 ዓመቱ ዕድሜ ባለሃብት አላሙዲ የ2013 የፎርብስ የዓለማችን 65ኛው ሃብታም ሲሆኑ በአንደኝነት የተቀመጡት ሜክሲኳዊው ካርሎስ ስሊም እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው።  73 ቢሊዮን ዶላር አላቸው።

2ኛ. ቢልጌትስ 67 ቢሊዮን ዶላር

3ኛ. አማናኮ ኦርቴጋ 57 ቢሊዮን ዶላር

4ኛ. ዋረን ብፌት 53 .5 ቢሊዮን ዶላር እንዳላቸው ፎርብስ ገልጿል።

በየዓመቱ ማርች ላይ የሃብታሞችን ዝርዝር የሚያወጣው ፎርብስ አላሙዲ ከዓለም 65ኛው ሃብታም ሲሆኑ ይህም በሳዑዲ አረብያ 2ኛው ሃብታም ያደርጋቸዋል። ያላቸውም ሃብት 13.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ መጽሔቱ አስፍሯል። አላሙዲ በ2012 ዓ.ም የነበራቸው ሃብት 12.5 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ዘንድሮ ዕድገት ማሳየቱ የፎርብስ የሁለት ዓመቱ ሪፖርትን በማየት ማወቅ ይቻላል። ሆንም ግን አምና አላሙዲ ከዓለም ሃብታሞች 61ኛው የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ 4 ደረጃ ዝቅ ብለው 65ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግሥት ልዩነቶችን በማጥበብ፣ በመቀራረብና በመመካር ሀገር የመምራት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ኢዜማ አሳሰበ

2 Comments

  1. ALAMOUDIN IS SAD THAT HE HAS LOST A FEW PLACES ON THE FORBES RICH LIST. IT IS so shameful that WHAT WORRIES THIS scrupulous so called investor is HIS POSITION IN THE forbes rich list. He is now exporing premium grade rice grown on Ethiopian soil by displacing 100s of 1000s of poor people to saudi arabia and other arab countries. the woyane and the arabs have a joint agenda to bleed Ethiopia while they benefit at the expense of the people. The fascist woyane is only accountable to arabs, chinese and indians and what ever they want or say is a first priority. they trample on the poor people of Ethiopia which they treat like shit.

  2. Dear editor
    You said Alamoudine has 13.5 bi dollars Best. Sir ,then please said to Alamoudine to give to Abay project 6 bi dollars, like this we finish Ethiopian respect dream “ABAY ” . Thank’s dear editor Habesha news

Comments are closed.

Share