March 5, 2013
4 mins read

በደቡብ አፍሪካ በአቡነ ያዕቆብ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መዘጋጀታቸውን ምዕመናኑ ገለጹ

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ሊቀጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ም ዕመናኑ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በስፍራው ለሚገኘው የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ዘጋቢ ገለጹ። አዲስ አበባ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ የሄዱት አቡነ ያዕቆብ ወደ ጽረ አርያም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ሲመለሱ ተቃውሞውን ለማድረግ እንደተዘጋጁ የገለጹት ምእመናኑ ሊቀጳጳሱ የቤተክርስቲያን አንድነትን ካሰናከሉት የወያኔ ጳጳሳት ጎን በመቆማቸው እንደሚያወግዟቸው ነው የገለጹት።
በ1997 ዓ.ም የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ በነበሩበት ወቅት ተማሪዎቹ የአድማ በመቱበት ወቅት ለመንግስት በመሰለል የተማሪዎቹ ተቃውሞ እንዲረግብ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እንዳደረጉ የሚገነገርላቸው አቡነ ያዕቆብ በደርግ ስርዓት የባሀር ሃይል መቶ አለቃ እንደበሩ የሚያውቋቸው ወገኖች ይናገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ አይ መቶ አለቃ ሳይሆኑ በደርግ የወጣቶች ብሔራዊ ውትድርና ጢዮ የሚባል ቦታ በውትድርና አገልግለው አሰብ ድረስ ሄደዋል ይላሉ። እነዚሁ የሚያውቋቸው ሰዎችም የምንኩስና ስማቸው አባ ገብርኤል ወልደሚካኤል እንደሚባልና በደርግ ወታደርነት ጊዜ ውስጥ እንደመነኮሱ ይናገራሉ። በሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተነሳውን ተቃውሞ በማርገብ ለመንግስት ያላቸውን ታማኝነት በማሳየታቸው በ1998 ዓ.ም ሃምሌ ስምንት በደቡብ አፍሪካ ሊቀጳጳስ ሆነው የተሾሙት አቡነ ያዕቆብ በተለይ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተመላልሰው ሲታከሙ ለዋሉት ውለታ ሕይወታቸው ከማለፉ በፊት የአፍሪካ አህጉር ሊቀጳጳስ ተብለው በሱዳን፣ በጅቡቲ እና በኬንያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲቆጣጠሩና እንዲሾሙ ተደርጓል ያሉት የዘ-ሐበሻ ውስጥ አዋቂዎች የአቡነ ያዕቆብ ዓለማዊ ሥምም መቶ አለቃ አስማማው እንደሚባል ነግረውናል።
የደቡብ አፍሪካው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንዳለው የወያኔን ሥርዓት ጥለው በተሰደዱ የደቡብ አፍሪካ ምእመናን ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የቤተከርስቲያን አንድነት እንዳይሳካ ካደረጉት የሃገር ቤቱ የወያኔ ደጋፊዎች ጋር አብረው መወገናቸው በተለይ በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው የጽረ አረአያም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን በማስከተሉ ሕዝቡ በአንድ ላይ ተቃውሞውን ለማሰማት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አማኞች በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ሊደረግ የነበረው እርቀ ሰላም የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ተልከው አሜሪካ የሄዱት ተደራዳሪ አባቶች ሳይመለሱና የ እርቁን ውጤት ሳይሰሙ የመንግስትን ፍላጎት ለማሟላት 6ኛ ፓትርያርክ መምረጣቸው እንዳስቆጣቸው በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

ይህን ጉዳይ ተከታትለን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop