ደሴ የብሐራዊ መረጃዉ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ ተኩስ ተከፈተ

ልዑል ዓለሜ እንደዘገበው

ደሴ በብሄራዊ መረጃ በሚስጥር ተጠርቶ በመካሄድ ላይ የሚገኘዉ ዉይይትን በመንተራስ የወልዲያዉን ብጥብጥ ያባባሱና ሆን ብለዉ ነገሩን ወደ ህዝባዊ አመጽ እንዲሄድ በማድረግ የተሳተፉ ወጣቶችን በተመለከተ ስብሰባ እየተደረገ ባለበት ወቅት ትዉልደ ወልዲያ የሆነ የመረጃዉ ሰራተኛ እስኳድ ወይም አልሞ ተኳሽ ስምሪት ባልደረባ በድንገት በከፈተዉ ተኩስ ለግዘዉ ማንነቱ ያልታወቀ የጸጥታ ዘርፍ ሐላፊ ወዲያዉኑ ህይወቱ አልፋለች።

” እኛ ከዚህ ህዝብ አብራክ ወጥተናል ይህ ህዝብ አንፈልጋችሁም እያለ ጮኽ እንጂ ምን አደረገ ይህ ህዝብ አልፈልግም ስላለ ብቻ ተገደለ አሁን ደግሞ ተመንጥሮ ይታሰር ትላለህ” ብሎ የጠየቀዉ አልሞ ተኳሽ ከጸጥታ ዘርፍ ሐላፊው የንቀትና የስድብ ቃላት በማግኘቱ የታጠቀዉን መሳሪያ አዉጥቶ በአራት ጥይት ገላግሎት መሰዋቱን ታማኝ ምንቻችን ጠቅሰዋል።

ምንጩ አክለዉ አሁን ትግሉ ተፋፍሞ ግሏል በዉስጥም በዉጭም እረመጡ ወያኔን መብላት ጀምሯልና ሁሉም ክልል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወንጭፉን መወርወር እንዲጀምር ጥሪ አስተላልፈዋል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግስት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ሁለት ተቀጣጣይ ሲሊንደሮች አገኘሁ አለ
Share