March 5, 2013
2 mins read

Hiber Radio: “በአሜሪካና በአውሮፓ ለሕወሓት እየሰለሉ፤ እያስፈራሩ የሚኖሩትን ምንም አያመጡም ብሎ መተው አደገኛ ነው” – አበበ ገላው

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ የካቲት 24ቀን 2005 ፕሮግራም
<…በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ያሉትን ለህወሃት የሚሰሩ እና ዲያስፖራውን እየሰለሉ፣እያስፈራሩ የሚኖሩትን ምንም አያመጡም ብለን መተው አደገኛ ነው። እነሱን የበለጠ ተደራጅተን ነህግ መታገል ያስፈልጋል።ሕግ ባለበት አገር ለመፋረድ የግድ የጠበቃ ድጋፍ ሊኖር ይገባል ለዚህ እያንዳንዱ መተባበር አለበት ይሔ የነጻነት ትግሉን ያግዛል..> ጋዜጠኛ አበበ ገላው የወቅቱን የሕግ ድጋፍ ጥሪ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
< ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለሺህ ዓመታት በአንድ ላይ አብረው የኖሩ የተዋለዱ ናቸው።የነሱ የዛሬ ቅስቀሳ የስልጣን እድሜን ለማራዘም እርስ በእርስ ለማጋጨት ነው። በአንድ ላይ ነጻነታችንን እስክናገኝ ልንታገል ይገባል …>> ኡስታዝ ኑር አህመድ በቬጋስ የተደረገውን የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ( ያዳምጡት)
<<…የቬጋስ የታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው።በኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መተባበር ኮርቻለሁ ። ከተባበር እናሸንፋለን..>> አቶ ቢኒያም ከቬጋስ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች አንድ ለህብር ሬዲዮ እንደተናገረው
አድዋ (ታሪካዊ ግጥም)
የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አንጻር (ትንታኔ)
ዜናዎቻችን
– በኢትዮጵያ አንድ ታጣቂ ሀይል ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ሰሞኑን በአካሄደው ውጊያ ድል መቀዳጀቱን ገለጸ
– የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የመሬት መቀራመት የቀኝ ግዛት ነው ተባለ
– በመንግስት ድጋፍ የተመረጡት ጳጳሱ አቡነ ማትያስ በዓለ ሲመታቸው ተደረገ
– የቬጋስ ታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
– የሳውዲው የመከላከያ ባለስልጣን ጸረ- ኢትዮጵያ አስተያየት አአ ላይ ቅሬታ አስከተለ
– በኢትዮጵያ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ በመላው አገሪቱ እየተስፋፋ ነው
– በቬጋስ የዕምነቱ ተከታዮች የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ክርስቲያኖች ድጋፍ ለመስጠት ተገኙ
– በስዊድን በሶስት የኤርትራዊን ጽቤቶች መቃጠል ሳቢያ ኤርትራዊያን ተወዛገቡ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Go toTop