አርቲስት በኃይሉ መንገሻ አረፈ

/

ለበርካታ ዓመታት በሃላፊነት በብሄራዊ ትያትር ፣ በሃገር ፍቅር ቲያትር ፣ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እንዲሁም በአዘጋጅነትና በተዋናይነት በርካታ ቲያትሮችን ፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በመስራት ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከተው አርቲስት በኃይሉ መንገሻ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ፍትሃተ ፀሎቱ Thursday march 7,2013 9:00AM ጀምሮ በ DEBRE MIHERERT ST MICHAIL ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH 3010 Earl Place NE Washington DC ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ከተማ የካቲት 8 1948 ዓ.ም ነው እንደተወለደ የሕይወት ታሪኩ የሚያሳየው አርቲስት በኃይሉ ውልደቱ 6 ኪሎ ቢሆንም እድገቱ ሙሉ በሙሉ ጉለሌ ሩፋኤል አካባቢ ነበር። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም ት/ቤት ነው አጠናቆ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ አርቲስት አለም ፀሐይ ወዳጆ ጓደኛው ስለነበረች ወደ ሃገር ፍቅር ቲያትር ወስዳ ከነ ተስፋዬ አበበና መላኩ አሻግሬ ጋር አስተዋውቃው የቲያትር ሙያ ላይ በቲያትር ሙያ ላይ ማተኮር ጀመረ። በኋላም ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን 22ሺ ብር መድቦ አማተር ተዋንያን መልምሎ ሲያሰለጥን ከነ አለምፀሃይ ወዳጆ ፣ አለሙ ገብረአብ ፣ አስራት አንለይ ፣ ሲራክ ታደሰ ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ትሩፋት ገ/ኢየሱስ ፣ አልማዝ ሰይፉ ፣ ተዘራ ውብሽትና መሰለች ከበደ የስልጠና ጀመረው በሃይሉ መንገሻ ባገኘው ዕድል ለሁለት ዓመት ወደ ታንዛንያ ዳሬሰላም ሄዶ ወታደራዊ ሳይንስና ማኔጀርነት ይማራል። በኋላም ሃገሩ ተመልሶ ቲያትር ቤትም እየሰራ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቢጀምርም በወቅቱ ” ትግል ይቅደም ትምህርት ይቅደም” የሚባል የፖለቲካ ትግል ስለ ነበር አቋርጦ ወደ ራሺያ ይሄድና በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ዓመት ቀጥሎም በሞስኮ የቲያትር ኪነ ጥበብ አካዳሚ አምስት አመት ተኩል ትምህርቱን ተከታትሎ በቴአትር አዘጋጅነት “ዳሬክተር የማስተር ኦፍ አርት” ማስትሬት ዲግሪውን እንዳገኘ በዋሽንግተን ዲሲ በይሁኔ በላይ አማካኝነት ከሚታተመው ባውዛ ጋዜጣ ላይ ባደረገው ቃለ ምልልስ ተናግሮ ነበር።
አርቲስት በሃይሉ መንገሻ እዚህ ሃገር ከመጣ በኋላ የመስማት ችግር አጋጥሞት ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢሕአዴግ ምንም መራጭ ባልተመዘገበበት የቦረና ዞን ለምርጫ ሊወዳደር ነው

ከኢሳት ቲቪ ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ብዙ ግንዛቤን ያስጨብጣችኋል መልካም እይታ። ዘ-ሐበሻ በዚህ ታላቅ አርቲስት ሕልፈት የተሰማትን ሐዘን እየገለጸች ለቤተሰቡና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ትመኛለች።

1 Comment

  1. I never know this guy but I watch all 2 hours his interview. My god I love him, i was so mooved thanks and Rest In Peace. What a man.

Comments are closed.

Share