የሰላም በር ተዘግቶ የተደረገውን 6ኛ ፓትርያሪክ ምርጫ እንደማይቀበል የዲሲ ቅ/ገብርኤል ካቴድራል አስታወቀ

(ዘ-ሐበሻ) በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በአዲስ አበባ የተካሄደው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ የሰላምን በር ተዘግቶ የተደረገ በመሆኑ አልቀበልም አለ። ካቴድራሉ ለሚዲያዎች በላከው መግለጫ  “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ21 ዓመታት በፊት ፓትርያሪክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያእክ በመቺሙ ምክንያት የደረሰውን ጥፋት በመረዳት ስህተቱን ለማረም፣ ለማስተካከልና ሰላም ለማምጣት የሰላምና የአንድነት ጉባኤ ተቋቁሞ በውጭና በአገር ውስጥ በሚገኙት አባቶች መካከል ድርድር በማድረግ ችግሩን ለመፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን” ጠቅሶ ተጀምሮ የነበረው የሰላም ጉባኤ ተቋርቶ የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ በመካሄዱና ተጀምሮ የነበረው የሰላም ሂደት እንዲቋረጥ በመደረጉ ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማው በመግለጫው አስታውቋል።

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅንጡ ፕሮጀክቶችና የኢትዮጵያ የከፋ ድህነት

1 Comment

  1. This is not breaking news it’s broken news
    They are already ser ate alba people no respect the church
    And canon .

Comments are closed.

Share