March 3, 2013
15 mins read

የአቡነ ማትያስ በዓለ ሢመት ተከናወነ

ሐገር ቤት በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት ብጹእ አቡነ ማትያስ ዛሬ በዓለ ሢመታቸው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከናወነ።
የአቡነ ማትያስ በዓለ ሢመት ከሀገር ውስጥና ከውጭ የተጋበዙ አባቶች ፣ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የተለያየ የሃይማኖቶች መሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንበት ተማሪዎች በተገኙበት ሲከበር የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሬዎችና ወረቦች ከልዩ ልዩ አቢያተ ክርስቲን በተውጣጡ ካህናትና የሰንበት ተማሪዎች ያቀረቡ ሲሆን አቡነ ማትያስም ለምእመኑ ቡራኬ መስጠታቸው ተዘግቧል።

የፓትሪያርኩ ቃለ መሃላ
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
1. እኔ አባ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005ዓ.ም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆኜ ተሾሜያለሁ:: ስለዚህ የተጣለብኝን ሃላፊነት ያለምንም አድሎና ተፅዕኖ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ካህናት፤ ምዕመናንና ምዕመናት የሁሉም አባት ሆኜ በቅንነትና በታማኝነት፤ በፍቅርና በትህትና አገለግላለሁ::

2.ሀ. በሚስጥረ ስላሴና በሚስጥረ ስጋዌ ትምህርትና ቀኖና መሰረት የቅድስት ስላሴን አንድነትና ሶስትነት አምኜ አስተምራለሁ፤

ለ. የመለኮትንና የትስብዕትን ፍጹም ተዋህዶና በዚህም የተገኘዉን የድህነተ ዓለም ትምህርተ ክርስትና በማስተማር የሚጠበቅብኝን ሁሉ እፈፅማለሁ፤ አስፀፈፅማለሁ፤

ሐ. በእግዚአብሔር ቸርነት፤ በቅድስ ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ በቅዱሳን መላዕክት፤ በቅዱሳን ነቢያት፤ በቅዱሳን ሐዋርያት፤ በቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታት ተራዳኢነት ሁሉንም ለመባረክ፤ ለመቀደስና ለማገልገል ቃል እገባለሁ፤

መ. በኒቅያ 325ዓ.ም በ318 ሊቃዉንት የተወሰነዉን፤ በኤፌሶን በ431 ዓ.ም በ200 ሊቃዉንት የተወሰነዉን ትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተክርስቲያን አከብራለሁ፤ አስከብራለሁ:: ለዚህም በአብ ወወልድ ቀመንፈስ ቅዱስ ስም ቃል እገባለሁ::

ጥቂት ስለ አቡነ ማትያስ –
– በትግራይ ክል ል በቀድሞው አጋሜ አውራጃ በሰቡሀ ወረዳ ጥር 15,1934 ዓ.ም ከአባታቸው ከአቶ ወልደጊዮርጊስ ወልደማርያምና እናታቸው ከወይዘሮ ከለላ ገብረመስቀል በትግራይ ክፍለሀገር አጋሜ አውራጃ ስቡሀ ወረዳ የተወለዱ ሲሆን ፥ አድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም ቀሲስ ወልደገሪማ ከሚባሉ አባት ፊደልና ንባብን ተምረዋል ።
– የኤርትራ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ማእረገ ድቁና እንደተቀበሉ በቀድሞው ትግራይ ክፍለ ሀገር ተንቤን አውራጃ ጮኸ በሚባል ገዳም በ1949 ዓመተ ምህረት በመግባት ለ10 ዓመት ገዳሙን በማገልገል በ1955 ዓመተ ምህረት ከገዳሙ አበምኔት ማዕረገ ምንኩስናን ተቀብለዋል ።
– አቡነ ማትያስ 13 ዓመታት በሊቀ ረዳኢነትና ለአንድ ዓመት የገዳሙ ቄስ ጎበዝ በመሆን አገልግሎታቸውን አበርክተዋል ።
– ወደ አዲስ አበባ በመምጣትም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ተመድበውም አገልግለዋል ።
– በአሁኑ ወቅት በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ናቸው ።
– አቡነ ማትያስ ከሀገር ውስጥ የተለያዩ ቋንቋዎች በተጨማሪ ኢንግሊዘኛ ፣ ዕብራይስጥኛ ፣ ግሪክኛና አረብኛን ይናገራሉ።

በሌላ በኩል 6ኛው ፓትርያርክ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ቃለምልልስ ሰጡ። አቡነ ማትያስ በቃለ ምልልሳቸው “የአሜሪካን ፓስፖርት ይዤ ነበር፡፡ አሁን ግን ተለውጧል፡፡ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2004 ዓ.ም አመለከትኹ፡፡ በግንቦት ወር እንደገና አመልክቼ ተሰጠኝ፡፡ ይኼ ከአሁኑ ምርጫ ጋራ አይያያዝም፡፡ ለምርጫው ተብሎ ፓስፖርት አልቀየርኹም፡፡ በመሠረቱ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ከኾንሁኝ በኋላ ሐሳቤ ወደ ኢትዮጵያዊነቱ ለመለወጥ ነበር፡፡ እንደዚህ ዐይነት ዕጩ እኾናለሁ ብዬ አላሰብኹም፡፡” አሉ።

ቃለ ምልልሱን እንደወረደ ያንብቡት፦
ብፁዕነትዎ ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ዕጩ መኾንዎን የሰሙት ከማን ነው?

ሰው ዝም ብሎ ያወራል፡፡ እገሌ ይኾናል ይባላል፡፡ ዕጩ ነኸና ና አሉኝ፤ አሁን ባለፈው የካቲት 13 ቀን ነው አዲስ አበባ የገባኹት፡፡ እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም ከኢየሩሳሌም ተነሥቼ ስገባ፡፡ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ተረቋል ተባለ፡፡ ያ ሕግ ታኅሣሥ 30 ለቅ/ሲኖዶስ ይቀርባልና ና ተባልኹ፤ ሥራ ይበዛ ስለነበር አልተመቸኝም፡፡ ጥር 6 ቀንም ና ተብዬ አልቻልኹም፡፡

ቀደም ሲል የአሜሪካ ዜግነት እንደነበረዎት ሰምቻለኹ፤ አሁንስ?

አዎ፣ በፈረንጅ አቆጣጠር በ1994 – 95 ችግር ነበረብኝ፡፡ የአሜሪካን ፓስፖርት ይዤ ነበር፡፡ አሁን ግን ተለውጧል፡፡ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2004 ዓ.ም አመለከትኹ፡፡ በግንቦት ወር እንደገና አመልክቼ ተሰጠኝ፡፡ ይኼ ከአሁኑ ምርጫ ጋራ አይያያዝም፡፡ ለምርጫው ተብሎ ፓስፖርት አልቀየርኹም፡፡ በመሠረቱ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ከኾንሁኝ በኋላ ሐሳቤ ወደ ኢትዮጵያዊነቱ ለመለወጥ ነበር፡፡ እንደዚህ ዐይነት ዕጩ እኾናለሁ ብዬ አላሰብኹም፡፡

ግን የአሜሪካ ዜግነት እንዴት ወሰዱ?

አይ÷ እርሱማ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በነርኹበት ጊዜ የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ተጽዕኖ ነበረብኝ፡፡ ከተሳላሚዎች ጋራ ደኅንነቶችን እየላኩ ብዙ ችግር አስከትለውብኝ ነበር፡፡ በዚያ ምክንያት ተሰደድኩ፡፡ አሜሪካ የነበሩትን ምእመናን ሳገለግል ቆየኹ፡፡ በኋላ ሲኖዶሱ ጠርቶ አጸደቀልኝ፡

በወቅቱ ፓትርያሪክ ተወግዘው ነበር?

መወገዙማ ደርግን አወገዝኹ እኔ፡፡ ደርግን ሳወግዝ የነበሩ ሰዎች እንዴት መንግሥትን ያወግዛል ብለው ፓትርያሪኩን አሳሳቱና አውግዘውኝ ነበር፡፡ በኋላ ስመጣ በስሕተት ነው ተብሎ አነሡት፡፡ የተወገዝኹት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ ነው፡፡ የተነሣው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስም ለቀው አቡነ ያዕቆብ ዐቃቤ መንበር በነበሩ ጊዜ ነው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው ጥቂት ጊዜ በፊት ነው ይኼ፡፡

ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ተወዳድረው ነበር ይባላል. . . . .

እኔ አወዳድሩኝ ብዬ አላውቅም፤ አሁንም ድሮም፡፡ ብቻ ከየክልሉ ሁለት ሁለት ተወዳዳሪዎች ሲባል ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ እኔ ሳላውቅ ተወዳድሬ እሳቸው ከአምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች ኾኑ፡፡ እኔ ቀረኹ፡፡ ጠርተውኝ የመጣኹት ግን የአቡነ መርቆሬዎስ ምክትል በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ጊዜ ነበር፡፡ መወገዜን እኔም አላውቅም ነበር፡፡ ምን ኾኜ? ስል እንዲህ ተላልፎብኽ ተባልኹኝ፡፡

ብፁዕነትዎ ሲወገዙ ሌላ አቡነ ማትያስ መሾማቸው ትክክል ነበር?

ደኅና፤ በቤተ ክርስቲያናችን ባህል ሁለት ጳጳሳት በአንድ ስም አይጠሩም፡፡ ግን ተደረገ ያን ጊዜ፡፡ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ ግፊት አድርገው ነው የተደረገው፡፡ ኾነ ብለው የእኔን ስም ለመውሰድ ያደረጉት ነው፡፡ ስመለስ ጸጸት ውስጥ ገቡ፡፡

ብፁዕነትዎ ፓትርያሪክ ቢኾኑ ዕርቀ ሰላሙ በምን መልክ ይቀጥላል?

ዕርቀ ሰላሙ እንደሚቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ተናግሯል፡፡ በዚያው መሠረት ይቀጥላል፡፡ ከሲኖዶስ የተለየ ሐሳብ ሊኖረኝ አይችልም፡፡

በፓትርያሪክነት ቢሾሙ በኢየሩሳሌም የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዞታ ለማስመለስ ምን ለመሥራት ዐቅደዋል?

ይህን በሰፊው እንገፋበታለን፡፡ ፓትርያሪክ የመኾን ጉዳይ ሳይኾን እኔም ኾንሁ ሌሎቹ እንዲገፉበት ቅዱስ ሲኖዶሱን እገፋፋለሁ፡፡ ከኾንሁ አለኹ ማለት ነው፡፡ ካልኾንሁ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሥራዬ ብሎ ከግብጽ ኦርቶዶክስ ጋራ ተነጋግሮ አንድ መፍትሔ እንዲገኝ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል፡፡ ወደ ሌላ ሀ/ስብከት ብቀየርም ይህ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት እርስዎ እንዲመረጡ ይፈልጋል መባሉ ከምን መነጨ?

እኔ ምንም የማውቀው ጉዳይ የለም ስለዚህ ጉዳይ፡፡

ፓትርያሪክ ቢኾኑ ከአምስተኛው ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ምን የተለየ ሥራ ይሠራሉ?

መቼም እግዚአብሔር የፈቀደውን የምንሠራው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትክክለኛውንና ቀጥተኛውን መንገድ እንድትይዝ፣ በውስጧ ያለው ሁሉ መንፈሳዊነትን የተጎናጸፈ፣ እውነትኝነትን የተከተለ መኾን አለበት ባይ ነኝ፡፡ እንደ ዓለማዊነት መደረግ የለበትም ባይ ነኝ፡፡ በተቻለ መጠን ይህን ወደ እውነተኛው መንገድ ለመመለስ ተስፋ ነው የማደርገው፡፡

ከአቡነ ጳውሎስ ሥራዎች በጣም የሚያደንቁት?

ቅዱስነታቸው ዓለም አቀፍ ሰው ነበሩ፡፡ በዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዋውቀዋል፡፡ በመንበረ ፓትርያሪክ ግቢ ለጳጳሳት ማረፊያ አሠርተዋል፡፡ ቤት አልነበረም፡፡ መሰብሰቢያ አዳራሽ አልነበረም፡፡ ቤተ መጻሕፍት አልነበረም፡፡ እነዚህ ሁለቱን አደንቅላቸዋለኹ፡፡

መሻሻል አለበት ብለውስ አቅርበው ያውቃሉ?

አንዳንድ ስሕተቶች ሳይ እነግራቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ÷ በስብከተ ወንጌል፣ በሃይማኖት አጠባበቅ በኩል የሃይማኖቱን ሥርዐት ያልጠበቁ ሰባኪዎች. . .በዘፈቀደ ሲኾን፡፡

ይቀበልዎት ነበር?

ይቀበሉኛል ግን ነገሩ ከባድ ይኾንና የተባለው መቶ በመቶ ላይሠራ ይችላል፡፡ መቻቻል ጥሩ ነገር ይመስለኛል፡፡ መቻቻል ከሌለ ሁከት ነው ያለው፡፡ የሕዝቡንና የሀገርን አንድነት ለመጠበቅ ተቻችሎ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ሌላ ምርጫ የለም፡፡ አንዱ የሌላውን ሳይቀማ መኖር መቻል አለበት፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop