ፍሬ-አልባ ጩኸት – ከፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

አንሰ እቤ አምግዕዝየ ኵሉ ሰብእ ሐሳዊ ውእቱ!

(የዳዊት መዝሙር 115)

መስፍን ወልደ ማርያም (ፕ/ር)

የካቲት 2005
አቶ ዳንኤልን አላውቀውም፤ ለካ ብዙ ጭፍሮች ያሉት ሰው ነው፤ በጣም ተንጫጩለት፤ የሎሌ ነገር ሆነና ጩኸታቸው አንድ ነው፤ ጉዳዩን ጭራሽ አያውቁትም፤ ያንገበገባቸው መሪያቸው መነካቱ ነው፤ ለሎሌዎቹ መልስ መስጠት ባልተገባ ነበር፤ ነገር ግን ያደረጉት ትክክል መስሎአቸው እንዳይኩራሩና በያዙት የመክሸፍ መንገድ አንዳይቀጥሉ አንዳንድ ነጥቦችን ላብራራላቸው ፈለግሁ፤ ውጤት ይኖረዋል ብዬ ሳይሆን ለኔው ለራሴና ለማኅበረሰባችን ጤንነት ነው፤ ራሴን ከአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ለመከላከል ፈልጌ እንዳይመስል፤ አትኩሮት በጉዳዩ ላይ እንዲሆን ለመሞከር ነው።

አንዳንዶቹ ዲያቆን የሚል ቅጽል ባለመጨመሬ ሆን ብዬ መስሎአቸዋል፤ ባለማወቅ ነው፤ ራሴን ተጠራጥሬ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከፈትሁና የማውቀውን ነገረኝ፤ — የተካነ፣ ምሥጢር ያየ፤ ቀዳሽ — የሚል፤ በዚህ መስፈርት እኔም ዱሮ ዲያቆን ነበርሁ፤ ዛሬም ይህንን የሚያሙዋሉ ወጣቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚልዮን ባይሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ይኖራሉ፤ በዚያ ላይ እኔ እንደማውቀው ዲያቆን ሦስት ደረጃዎች ሲኖሩት የዲያቆኖች አለቃ ሊቀ ዲያቆናት ይባላል፤ አቶ ዳንኤል ሊቀ ዲያቆናትም አልሆነም፤ የአቶ ዳንኤል ዲያቆንነት የቱ ዘንድ እንደሚወድቅና ምን ማለትም እንደሆነ አላውቅም፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም እንዲህ ያለ ማዕርግ መስጠት ጀምራ እንደሆነና ለነማን እንደምትሰጥ አላውቅም፤ እኔ ዱሮ የማውቀው ዲያቆን የቅስና ሥልጣን (በምድር ያሰራችሁት በሰማይም የታሰረ ይሆናል፤) ሲያገኝ መምሬ መባሉን ነው።

ወደተነሣሁበት ጉዳይ ልግባ — አንድ መጽሐፍ አሳተምሁ፤ አውቃለሁ የሚለው አቶ ዳንኤል ተነሥቶ ስለመጽሐፉም ስለሌላ ሌላም የማያውቀውን ጻፈ፤ ስድስት የግድፈት ነጥቦችን ለቅሜ በማስረጃ እያስደገፍሁ የማያዳግም መልስ ሰጠሁት፤ ይህንን ያደረግሁበት ምክንያት ጭፍሮቹ እንዳሉት ሥራዬን አትንቀፉት በማለት በመታበይ አይደለም፤ ማናቸውም ሥራ አደባባይ ሲወጣ መነቀፉ አይቀርም፤ ስሕተትም አይጠፋም፤ አንድ ሰው በአንድ የአገር ወይም የማኅበረሰብ ጉዳይ ላይ ሲጽፍ ወይም በአደባባይ ሲናገር ራሱን ማጋለጡ ነው፤ የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ይህንን የማያውቁትን ጉዳይ ለእኔ ለማስተማር መከጀላቸው ጨቅላነታቸውን ያሳያል፤ በእኔ ላይ ባወረዱት ውርጅብኝ እንኳን ጉድጓድ ቆፍረው ራሳቸውን ቀብረው ነው፤ እውነተኛ ማንነታቸውን ደብቀው ነው፤ እነዚህ ጭፍሮች ስለመጋለጥ የሚያውቁት የለም፤ ስለዚህም ጉርጓድ ውስጥ ተቀብረው ስለማያውቁት ነገር መጮሁ የመጀመሪያው ስሕተታቸው ነው፤ ለነገሩ ስሕተት አይደለም፤ ወኔ-ቢስነት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አካላዊና መንፈሳዊ ጎኗ ክፉኛ የተጎዳውን ኢትዮጵያን ለመጠገን የሚታገለውን ፋኖ የማይደግፍ ኢትዮጵያዊ በምን ቀን የተፈጠረ ነው?

እነዚህ ሁሉ ጭፍሮች ለጩኸት ከመጠራራታቸው በፊት መጽሐፉን ለማንበብና የክርክሩ መነሻ የሆኑትን ነጥቦች ለመጨበጥ አልሞከሩም፤ ወደው አይመስለኝም፤ ንዴታቸውን ለመግለጽና ግዳይ ለመጣል ስለቸኮሉ ለእነሱ ችሎታ የሚቀልለውን

‹‹የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፣

ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!

በማለት በአደባባይ አቅራሩ፤ የችሎታ ማነስና ችኮላ ተለውሶ ያንን ጫጫታ አስከተለ፤ ገና ይቀጥላል፤ ባገኙን ቦታ ሁሉ ይህንን ጀብዱአቸውን ሊገልጹልኝ የሞከሩም አሉ፤ ከመሀከላቸው አንድም አንኳን ጉዳዩን ለመገንዘብና በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሞከረ አለመኖሩ የአስተሳሰብ ደረጃቸውን በግልጽ ያመለክታል፤ የሁሉም ዘገባ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው።
■ከመሀከላቸው ስለመጽሐፉ የተናገረ አንድም የለም፤
■ከመሀከላቸው አንድም ሰው አቶ ዳንኤል ስለጻፈው የተናገረ የለም፤ ■መጽሐፉን ሳያነቡና የአቶ ዳንኤልን ጽሑፍ ሳያነቡ እንዴት ብለው እኔ በጻፍሁት ብቻ እንደዚያ ያለ የንዴት ጫጫታ ማሰማት ቻሉ?

ለጭፍራዎቹ በመጽሐፉና በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ መሀከል ምንም ግንኙነት እንዳላዩበት ግልጽ ነው፤ ሊያዩበትም አይችሉም፤ ስለዚህ የእውቀት ጉድለታቸውን በንዴት ተኩት፤ እነሱው ራሳቸው የተገነዘቡትን የእውቀት ጉድለታቸውን እያጋለጡ ስለመጽሐፉ ለመናገር ወኔ አላገኙም፤ የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ማምለጫና መብለጫ በሆነው የብልጣብልጥ ዘዴ ተጠቅመው በእነሱ ግምት እነሱን ከፍ እኔን ዝቅ አድርገው ለማሳየት ሞከሩ፤ ጭፍሮቹ በሙሉ እውቀቱ ስለሌላቸው መጽሐፉን ረሱት፤ ስለዚህም ራሳቸውን የሥነ ምግባር ሊቃውንት አደረጉና ትንሽነታቸውን ወደበላይነት ለመለወጥ ጣሩ፤ ይህ ብልጣብልጥነት እንደማያዋጣ ስለገባቸውና የእውቀታቸውንም ጎዶሎነት ስለተገነዘቡ ማንነታቸውን ሳይገልጹ ስማቸውን ደብቀው በአደባባይ ደነፉ፤ ደስ አላቸው፤ አስደሰቱ፤ ‹‹ያንን ፕሮፌሰር ነኝ ብሎ የሚኮፈስ ሰውዬ ልክ ልኩን ነገርነው! ልኩን እንዲያውቅና ከእኛ የማይሻል መሆኑንም ነገርነው!›› አንዳንዶቹ የእውቀት ደረጃቸውን አዘቅት ሲያወርዱ ከመስፍን ጋር ፕሮፌሰርነትንም አብረው ይኮንናሉ! አይ ፕሮፌሰርነት! እንዲህ ከሆነ ይቅርብን! እያሉ ዘላበዱ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ክልል ነበርን፣ ክልል እንሆናለን! የአዲስ አበባ ክልላዊ መንግስት! - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ተመካክረው የተነሡት በእነሱ ሚዛን ስለመስፍን ወልደ ማርያም ምግባረ-ብልሹነት ለዓለም ለመንገር ነው፤ አዋጃቸውን እንቀበለው፤ ስለመስፍን ወልደ ማርያም አንድ እውቀት ያስጨብጠናል፤ ዋናው ጉዳይ ግን መስፍን ወልደ ማርያም አይደለም፤ ዋናው ጉዳይ መጽሐፉ ነው፤ እንግዲህ ስለመጽሐፉ ምንም የማያውቅ ሰው ስለመስፍን ወልደ ማርያም መናገር የሚችለው ስንት ገደሎችን ዘልሎ ነው? ሁሉም ያሉት መስፍን ወልደ ማርያም ለአቶ ዳንኤል የሰጠው መልስ ስድብ ነበር የሚል ነው፤ ነገር ግን ከመሀከላቸው አንድም ሰው ስድቡ ምን እንደነበረ አልተናገረም፤ አንዴም ደህና አድርጎ ያላነበበውን ደጋግሜ አንቤዋለሁ ብሎ ሐሰት የተናገረን ሰው ሐሰት ተናግረሃል ማለት፣ የማያውቀውን አውቃለሁ ብሎ የተናገረ ሰውን አታውቅም ማለት፣ የማያውቀውንና ያልሆነውን ነገር ሲለጥፍብኝና የተናገረውን መልሶ ምሥጢር በማድረጉ የደብተራ ተንኮል ማለት፣ ለእኔ ስድብ አይደለም፤ እውነትን መናገር፣ ወይም ፈረንጆች እንደሚሉት አካፋን አካፋ ብሎ መጥራት ነው፤ ማሰብ የሚችል ሰው ለተናገርሁት ማስረጃ እንዳይጠይቀኝ ማስረጃዎቼን ሁሉ ቁልጭ አድርጌ አቅርቤአለሁ፤ እንዲያውም ትልልቅ ግድፈት የምላቸውን ነገሮች አልገባሁባቸውም፤ እዚያ ብገባ የበለጠ አንጫጫ ነበር፤

ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን መጽሐፉን ያነበበ አይመስለኝም፤ ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ ውስጥ ምንም እንከን አላዩም፤ ሊያዩም አይችሉም፤ ከስድብም አልፎ ወንጀል ሊለጥፍብኝ ሲከጅለውም አልታያቸውም፤ ወንጀልን በሰው ላይ መለጠፍ አላዋቂነት፣ ተንኮል፣ ውሸት ቢባል ስሕተቱ ምኑ ላይ ነው? እውነት ከማይከበርበት ቤት የወጡ ጭፍሮች እውነትን አላዩም ብሎ መውቀስ ባይቻልም አለማየታቸውን መናገር ግን ተገቢ ነው።

የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች የመጽሐፉን ቁም-ነገር መጨበጥ ስላቃታቸው የሥነ-ምግባር ጉድለት የመሰላቸውን የመመጻደቅ ስብከት አወረዱት፤ ነገራቸው ሁሉ እንደአህያ መልክ አንድ ዓይነት ነው፤ ራሳቸውን አፋፍ ላይ እኔን ደግሞ ገደል ውስጥ ጨምረው እንደናዳ ሊያወርዱብኝ ሞከሩ፤ ከጭፍሮቹ መሀል አንድም እንኳን እሱም ራሱ ሆነ ጓደኞቹ የጻፉት የምግባረ ብልሹነት መግለጫና ማረጋገጫ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ ያለው አልተገኘም፤ በነዚህ ጭፍሮች የማሰብ ችሎታ እውነት መናገርን እንደስድብ ከመውሰዳቸው በላይ እነሱ ግን ለመሳደብ ልዩ ፈቃድ ያላቸውና የሥነ ምግባር ደረጃቸውም የተለየ ነው፤ እነሱ ሲሳደቡ የሥነ ምግባር ብልሽት አይታያቸውም! እውነትን በደረቅ ቋንቋ ከመስማት ይልቅ ውሸትንና ተንኮልን በለስላሳ ቋንቋ መስማት የሚበልጥባቸው ጭፍሮች አቶ ዳንኤል ለተናገረው ዓይኖቻቸውን ሸፍነው እኔ በሰጠሁት መልስ ላይ ማተኮራቸው ያጋደለ የሆዳምነት ሚዛናቸውን በገሀድ ያሳያል፤ ውሸት የተናገረን ውሸታም ማለት፣ ተንኮልን የሸረበን ተንኮለኛ ማለት ትክክል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእውነት የተራበ፣ ለእውቀት የተራበ ሆኖ ለብዙ ሺህ ዓመታት ባለህበት ሂድ ሲል የኖረው በእንደነዚህ ያሉ የእውነትና የእውቀት ጸር የሆኑ ጭፍሮች እየታገተ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባ - አጫጭር መረጃዎች | ኣስገደ ገብረስላሴ (መቀለ)

ሳያውቁት የመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ ዋናውን መልእክት በተግባር አሳዩ፤ እውነትንና እውቀትን (ሁለቱን መለየት አይቻልም፤ እውነትን የማይቀበል እውቀትን አያገኝም፤ እውቀትን የማይቀበል እውነትን አያገኝም፤) አርክሰው እነሱ ጨዋነት የሚሉትን አወጁ፤ አንዱ በማያሻማ መንገድ ገልጦታል፤ መስፍን ኃይለ ማርያም ነኝ የሚል እንዲህ አለ፤‹‹ከእርስዎ ምሁራዊ ስድብ የዳንኤል ክብረት ጨዋዊ መሃይምነት በእጅጉ ይሻላል፡፡›› ይህ ሰው እሱና ጓደኞቹ በያዙት ሚዛን ‹‹ስድብ›› ያሉትን ተቀብሎ ከመታረምና ወደእውነትና ወደእውቀት መንገድ ከመግባት ይልቅ ‹‹ጨዋዊ መሃይምነትን›› መርጦ ለመኖር መወሰኑ ያሳዝናል፤ የዳንኤል ክብረትን አስመሳይነት፣ ደፋርነት፣ አላዋቂነትና ተንኮል በማያሻማ ቋንቋ ለመግለጥ የወሰንሁት በእንደዚህ ያሉ ምስኪን ‹‹ጨዋዊ መሃይሞች›› ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ገምቼ ልከላከልላቸው ብዬ ነበር፤ ተመችቶናል ስላሉ እግዚአብሔር ያውጣቸው፤ ሌሎች ሕመሙ እንዳይጋባባቸው ይጠንቀቁ!

በመጨረሻ በእውቀት ጉዞ ይሉኝታ፣ መግደርደር፣ መሸፋፈን፣ ማድበስበስ፣ መቀላመድ፣ የተጠሉና የእውቀት ጸር በመሆን የሚፈረጁ ዝንባሌዎች ናቸው፤ ሀ ማለት ሁለት ነው፤ ለ ማለት ሦስት ነው፤ ከተባለ ሀ+ለ አራት ነው ሲል የተጻፈውን አላነበብህም፤ ወይም አልገባህም፤ ስለዚህም መልስህ ልክ አይደለህም ማለት መማር ለፈለገ ነውር አይደለም፤ እውነትንና እውቀትን ለማራመድ መንገዱ ይህ ነው፤ የተገነዘበው ይራመዳል፤ እውነትን የሚፈራው ወደኋላ ይቀራል፤ መክሸፍ ማለት እንዲህ ነው።

16 Comments

  1. min enide arogey wisha talazinale atimitim enidey ye enichet shibet 3 menigist belak min felek ahun demo

    • Yoyo man- balege neh betam, lemn ehen temegnehlachew?… misedbunm esachew slehonu new….echi hager shimagle ena mekari atita balechibet se’at ehen memegnetih yasaznal!! Egna Ethiopiawian yehone ye mentality chigr alebn meselegn…I think

    • yoyo man,be ewnet ante etyopia west kedehena betseb yetewledk be ethiopia bahel temkerh tarmeh yadk ethiopiawe lemhonh betam etrateralhu manem menged lay yadege beteseb yelelew mekari yata endant aynet astyafi qale lemeder lesemay lekebedu azawent mehure sew yehne qal menager betam asafarina manenthen yemiyasgemt naw.betam yasazenal temeker,tarem.

    • Balege, lafih lik yunereh! you can write comment but don’t insult respected man like this. Balage yasadegew yemibalew endante ayinetun new! This man could be a father for you so how do you dare to write those trash words to him. Bilginam lik alew.

  2. ዘሃበሻ የሚጻፉ ጽሁፎች ሁሉ አነባልሁ ይጠቀመኝም አይጥቀመኝም። እንደ እኔ እንደ እኔ ከሆነ በአሁን ስሃት የሚጻፉ መጽሃፎች ሁሉ ለ ኢትዮጽያ ህዝቦች ይጠቅማልሁ ሳይሆን የምለው መነሻ ብቻ ነው ሊሆኑት የሚቸልሁት ምክንያቱም እውነትን የሚያጣምሙ ብቻ ስለሆኑ ጽሃፌዎችሁ የ ኢትዮጽያ ቅርስ ሊሆኑ አይችሉም ።የ ኢትዮጽያ ቅርስ ነው ብዬ የማምነው ከህትመቱ በፊት ሁሉም ሙሁር ህዝብ ተስብስቦ ሲያጸድቀው ብቻ ነው።የፕሮፌስርን መጽሃፍ ለመገምገም የተስበስቡ ስዎች ሃሳባቸውን ለመግለጽ ያልቻልሁ በታክቲክ የታጀበ ሽወዳ አዳራሽ ወስጥ እንደነበረ እሪፖርተር ላይ አንብቤያልሁ።አዳራሽ ወስጥ መልስ ያልተስጠበት መጽሃፍ እኔ ጋር መጥቶ እንዴት እውነት ይሆናል።ዘሃበሻ አንድ ትክከለኛ ጋዜጠኛ መጠየቅ ካለበት ለፕሮፌስር ይህን ነው።ስሃት አልበቃም ብሎ ማለፍ አይሰራም ምክንያቱም ታሪክ ነው።ለወደፌቱ በ እኔ እምነት ትክክለኛው የ ኢትዮጽያ ታሪክ ነው ብዬ የማስቀምጠው መጽሃፍ አሁን የለም ብዬ አምናልሁ።ስለዚህ የመጭው ትውልድ እንዳይጭበረበር /እውነቱን ማውቅ ስላለበት።በአሁን ስሃት ብዙ የሚጻፉ መጽሃፎች ስላሉ እውነትም የሚጽፉ ካሉ/ውሽትም የሚጽፉ ካሉ ጥሩ ነው።አንድ ቀን እነዚህ መጽሃፎች ተስብስበው ህዝብና ምሁራኖች ተስብስበው ይገመገሙና አንድ መጽሃፍ ይሆናልሁ እስከዛ ግን እውነት የለም እናነበዋለን እንጂ ።እስከዛው ለፕሮፈስር የምትጠይቅልኝ ዘአበሻ ይገኛልሁ የተባልሁት ለምን አለተገኙም? አርተስት ደበበ ለምን ይስጠው አይስጠው አለ?ይህን እንደ ጋዜጠኝነትህ ጠይቃቸው። አመስግናልሁ

  3. you are quite right professor. some one covered themselves by so called religious scholars always told us what they don’t do things.

  4. Tanks prof. We always respect and love u. We understand that u r doing ur part perfectly. And tanks a lot again and again.

  5. እባካችሁ እባካችሁ! አሁንስ ከመውረድም አልፋችሁ ወደቃችሁ ‘”ከሸፋችሁ” (በእናንተው ዘዬ)! ስንት ያልሰራነው ነገር እያለ በዚህ ጉዳይ ስትነታረኩ ማየት እንዴት ወኔን ይፈታተናል? ልቦና ይስጣችሁ!

  6. zehabesha,

    Thank you. I am so sad by our so called intellectuals now a days. They are stubbornly stand for their ego while the country is in fire whether political, economical, social especially religious interference. Weyane appointed his cadre patriarch just today. But the egoist professor want to belittle our church as a whole by attacking one individual, Daniel, which I am not a fan of his too.
    Prof. Mesfin repeatedly attack in every opportunity radio, books, guest speaker etc.. Ethiopia’s hero Atse Teodros done many things to bring back a united Ethiopia after 70 years fiefdoms. In nation building almost all nations passed through what Ethiopians did; but our so called intellectuals like prof. Mesfin try to show their intelligence by belittle their own hard working leaders. Other countries intellectuals even try to hide their crimes as we know it. It is ironic what a scope of knowledge some have!!! I wonder if that is an ideology of regionalism!! Just like weyane!! Just about a month ago another prof. Getachew poisonous article also makes me wonder is Ethiopia cursed by her children especially whom she taught them dealy?

    wey gud.

  7. “አቶ ” ዳንኤል አቶ መስፍን ወልደ ማርያምን ነርቫቸውን የነካው ይመስላል። ሽማግሌው ግመኛ የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸው አጻጻፋቸው ይመሰክራል።ዳኒ በርታ ዘመናችን ስራ እንጅ ሽበት የሚያስከብርበት ዘመን አይደለም መከበር በሽበት ቢሆን ኖሮ ከመስፍን በላይ የሸበቱ እድሜ ጠገብ ደንጋዮች ታላቅ ክብር ያገኙ ነበር ስልዚህ ዳኒ እንደፈለጉ የሚለፋደዱ ለፍዳዳዎችን እሳት በሚተፋው እውነተኛ ብ ዕ ርህ አስደንግጣቸው፤ ልክ አበበ ገለው መለስን እንዳስደነገጠው!!ምስጋና ለዳኒ ፤ ልቦና ደግሞ ትናንት ዲያቆን ለነበርው ዛሬ ለከሰረው ለመስፍኔ ፤አሜን

    • The professor is a highly educated scholar. AAn emblem of erudition.
      Guys go to school to learn how to write and speak. Get off spoiling the name of those who have it. Lenegeruma Getachinins yetsefut ena yezebetubet mehayman
      Ayidelumn. Nebiy bageru ayikebirm yibalal yihew new. DenaKurt anhun.

  8. @Yoyo man:
    Ante geta yeker yebelih. You looks orphan who do not know the love of parent. Dear professor well said I totaly accepted. At this time dekunina be machine ye mimeret yemesilal.

  9. Thank you so much professor Mesfin Weldemariam, we love you!!
    we know you very well , you are knowledgeable man, ! we can’t forget your great contribution for Ethiopian Geography ,History study , Human right ,……etc

    Never listen this stupid BANDA !!!
    long live to professor

  10. የተከበሩ ፕሮፌሰር በመጀመርያ ትዕቢት የትም እንደማየደርስዎ ላሳውቅዎት ደስ ይለኛል ምክንያቱ በመጀመርያ መጽሓፍ ጽፈው ” አስተያየታችሁን ስጡልኝ ” ብለው
    ለሚያውቁትንና ለማያውቁትን ሰው ሁሉ የጋበዙ እርስዎ እራስዎ ሆነው ሳለ ሰው የመሰለውን ሓሳብ ቢሰጥ ለምን ያብዳሉ ለምንስ ከእርስዎ ለሚበልጠው እና በሚልዮኖች ተደናቂ እና ተወዳጅ ለሆነው ለዲያቆን ዳኒኤል ክብረትን ይሰድባሉ ድግሞ የሚገርሞው ድያቆን ነብርኩ ብሏል ታድያ ስድብ ብቻ ነው ከእርስዎ ውስጥ የቀረ እውነት ለመናገር ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ለ ሃይማኖቱ የተሰዋ ስለሆነ ነው እንጂ በፖሎቲካ ውስጥ ቢገባ ንሮ አንተ በፊቱ ቁንጫ ሆነህ ትቀር ነበር የሱ ነገር ፍሬ አልባ ጭሆት ብለህ ሳለህ ደግሞ እራስህ ጭሆቱ ፍሬ እንዳለው መስክራሃል እንዲህ በማለት “አቶ ዳኒኤልን አላውቀውም፡ ለካ ብዙ ጭፍሮች ያሉት ሰው ነው፡በጣም ተንጫጩለት………” አዎ ፍሬ ያለው ጭሆት ነው እኔ እራሴ የምናገረው ስለ እውነት
    ነው እንጂ ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት በአካል አግኚቸው አላውቅም ስራው ግን አውቀዋለሁ ከእርስዎ በላይ ም ታዋቂ እና በብዙ ሚድያዎች ቀርቦ አስትያየት የሚሰጥ እና በጣም ብዙ ቃለ መጠይቅ የተደረገለት ሰው ነው ስለዚ አቶ ፕሮፌሰር አስተያየት ለሚሰጥዎ ሰው መስደብ አቁመው አስተያየትን መቀበልን ይልመዱ።

Comments are closed.

Share