ይህ ስርዓት በፍጹም አይድንም

መስቀሉ አየለ

በጌታቸው አሰፋ እና በሳሞራ የኑስ መካከል ያለው ፍጥጫ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል። በሁለቱ አሽቃባጮች ማለትም በኃይሌ ገብራስላሴና በፕሮፌሰር ይሳሃቅ ኤፍሬም በኩል ተጀምሮ የነበረው የማስታረቅ ጥረት ሚስጥሩ  ሾልኮ ከውቀጣ በኋላ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን እንደገና በሁለቱም በኩል የተሻለ ተሰሚነት ሊኖራቸው ይችላል ተብለው በሚገመቱ ሙሉ ለሙሉ ከትግራይ በሆኑ የስርአቱ ሰዎች ሌላ የሽምግልና ጥረት እንደቀጠለ ነው።

ጸረ ሙስና በሚል ሽፋን ሰዎችን የማሰሩ ሂደት በሁለቱም ክንፍ በኩል ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ነገር ግን ጌታቸው አሰፋ ጉምቱ የሚባሉ ወታደራዊ ጀነራሎችን በማሰሩ በኩል ያልተሳካለት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ሂደቱ ቅርቃር ውስጥ ገብቷል። በአዋጅ ተቋቁሞ የነበረው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያለ አዋጅ ከፈረሰ ጥቂት ወራት ያስቆጠረ ሲሆን ለግዜው ከወታደራዊ ደህንነቱም ሆነ በጌታቸው አሰፋ ከሚመራው ብሄራዊ ደህንነት የሚላኩትን የሙሰኛ ስም ዝርዝሮች እየተቀበሉ ማሰሩ በጌታቸው አምባዬ በሚመራው አቃቢ ህግ ጽቤት ላይ የወደቀ እዳ ሆኖት አርፏል። በዚህ ሰአት ለሁሉም ግልጽ ሆኖ የወጣው አንድ ነገር ቢኖር ይህ ስርዓት የገባበትን አደገኛ ቀውስ ለመፍታት ምን ያህል አቅም እንዳነሰው; ይበልጡንም ቀኑ እየገፋ በመጣ ቁጥር አደጋው ከቁጥጥር እየወጣ መሄዱንና እስከዛሬ ያልተፈታ ችግር ቀን አልፎ ቀን በተተካ ቁጥር የበለጠ ውስብስብ እየሆነ መሄዱ ነው።ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ጨለማውን ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት አዋቂነት ነው። “ጠላትህን ወንዝ ሲወስደው ካየህ አንድ ጠብታ ምራቅም ቢሆን እንትፍ” በል የሚለውን ያባቶች ይትበሃል ገንዘብ እናድርግ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፈተናን መስረቅ ለስብሃት ነጋ ትግል ለሌላው ወንጀል ያደረገው ማነው?

2 Comments

  1. ወያኔ 26 ዓመት በስልጣን ላይ መቆየቱ እይታውን አጨልሞታል። ማን አለብኝ፤ ማን ይነካኛል እንዲል አስችሎታል። በአንድ ዘር የተዋቀረ ወታደራዊና የሲቪል የስልጣን አሰራርን ድጋፍ በማድረግ ለመኖር እያሰረ፤ እየገደለ፤ በዘር፤ በጎሳ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈል ለአንድ እንካቹሁ እሳት ያን ሰፈር አቃጥሉት ለሌላው የኖራቹሁበት ሃገር ክልልላችሁ አይደለም ሂድ ውጡ በማለት ህዝባችን እያመሰ ይገኛል።
    አሁን በቅርቡ በተደረገ ስብሰባ ዶ/ር ደብረጽዮን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩን አቶ ደመቀን በጥፊ ያጮለበት ሁኔታ ምን ያህል ስርዓቱ የነቀዘና በአንድ ዘር የበላይነት የሚመራ እንደሆነ አመላካች ነው። በመሰረቱ የበላይ አካልን በጥፊ መምታት ለእስራት ይዳርጋል። በወያኔ ዓለም ግን ስልጣንና ህግ ሳይሆን የሚሰራው ዘር ነው። የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል እንዲሉ አቶ በረከትና ሌሎችም ገላጋይ መሆናቸው የወያኔን የአሰራር ብልሽነት ያሳያል። የወያኔው የስለላ ቁንጮ የጌታቸው አሰፋና የሳሞራ ግብግብ ሌባን ከመያዝ ጋር የተያያዘ እንጂ ሃገርን እናድን በሚል የሃሳብ ልዮነት የተፈጠረ ክስተት አይደለም፡፡ ሳሞራ በዙሪያው ያሉ ወታደራዊ መኮንኖችን፤ በስሙ ያለቅጥ ሃብት ያካበቱ ዘመዶችን ከጸረ ሙስና ኩነኔ ለማዳን ጠበንጃውን ተገን አርጎ ጌታቸው አሰፋን ማስፈራራት መጀመሩ ቆይቷል። ሳሞራ መዝባሪና የመዝባሪዎች ተባባሪ መሆኑ ገና ከበፊት ይታወቃል።
    ባጭሩ የአማራና የኦሮሞ ወይም የደቡብ ክልልሎች ተወካዮች ነን በማለት በየስፍራ የተለጠፉ የወያኔ ተለጣፊ ለሥጋ አዳሪ ድርጅቶች ወያኔን ለመጋፈጥ ልቡም የሞራል ብቃቱም የላቸውም፡፡ የወያኔ ትራፊ ለቃሚዎች ከሆኑ ዘመናት ተቆጥረዋል። ዛሬ ሃገሪቱን የሚያሽከረክራት ዶ/ር ደብረጽዮን ነው። ለዛም ነው ማንንም ሳይፈራ ምክትል ጠ/ሚ ደመቀን አንተ አታዘኝም ብለሃል አላልክም በማለት በስብሰባ ፊት አፋጦ አዎ በአሰራሩ መሰረት አንተ አታዘኝም ብያለሁ ሲለው በጥፊ የተማታው። የወያኔ ንቀት ይህን ያህል ነው። ቀዳሚው ጠ/ሚ አቶ ሃይለማሪያም በስም ብቻ በስልጣን ላይ የተጎለቱ ሰው ናቸው። ያ ባይሆን ኑሮ ዶ/ር ደብረጽዮን ላይ እርምጃ መውሰድ ይቻል ነበር።
    እኔን አንድ ነገር ይገርመኛል። ሳሞራንና ጌታቸው አሰፋን አስታራቂ ለምን አሰፈለጋቸው? ይህ የወያኔ የማማቻ ብልሃት ነው። የተጣሉት በሴት፤ በመሬት፤ ወይም የግል የቡና ቤት ገጠመኝ ጥል አይደለም። የአሰራር ልዮነት እንጂ! ይህ ግን አንድ ነገር ያመላክታል። ወያኔ በአጸደቀው የሃገሪቱ የወንጀልና የአስተዳደር ህግ ሳይሆን የሚመራው ከበረሃ ይዞት በመጣው የአስረሽ ሚቸው ዘይቤ ነው።
    በቅርቡ ወደ ዋሽንግተን ብቅ በማለት ላቀረቡት እርዳታ ነክ ጥያቄዎች የአሜሪካ መንግስት ልክ ግብጽን ክፉኛ በዘለፈበት አንደበት ወያኔን በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ልጆችን መብትን ጥሰት ካላስተካከለ ምንም አይነት ወታደራዊ እርዳታ አንሰጥም ሲሉት ነው ወያኔ ወደ ቻይና የተጓዘው። የስርዓቱ መውደቅ አይቀሬ ነው። ችግሩ ከስጦታና ከሽያጭ የተረፈችው ሃገር እድል ፈንታ ምን ይሆን? ቆይቶ ማየት ነው።

Comments are closed.

Share