የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) አራተኛ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ

ነሃሴ ፲፬ ቀን ፪ ሺህ ፱ ዓ.   ምየኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ  ትግል  ሸንጎ  (ሸንጎ) አራተኛ  ጉባዔውን  ከነሃሴ  ፲፪  እስከ  ፲፬  ቀን  ፪ ሺህ ፱ ዓ. ም (August 18 – 20,  2017)  በአሜሪካን  አገር፣  በቨርጂኒያ  ግዛት፣ በአሌክሳንደሪያ ከተማ ውስጥ አካሂዷል።   ጉባዔው በሦስቱ ቀናት ውስጥ በበርካታ ጉዳዮች    ላይ  ሰፊና  ጥልቅ  ውይይቶችን  አካሂዶ  ውሳኔዎችን   አስተላልፏል።

የረጅም ዘመን ታሪክ ያላትና የሰው ልጅ መገኛ የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ ወራሪ የፋሽስት ሠራዊትን በጦርና በጎራዴ አይቀጡ ቅጣት ቀጥታና አዋርዳ ነፃነቷን ያስከበረችና ለአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረች ሀገር በአሁኑ ወቅት ከምን ጊዜውም  በላይ  ኅልውናዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያውያን በአኩሪ ታሪካችን ኮርተን በገዛ አገራችን በነፃነት የመኖር መብታችንን ተገፈን እንደ ዜጋ መኖር ያልቻልንበት  አስከፊ  ጊዜ  ላይም እንገኛለን።

ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብታችን ተረግጦ በአፈና፣  እስራት፣  ግድያና የሽብር ኑሮን እየገፋን እንገኛለን። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በሥራ አጥነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በረሃብና በበሽታ እየተሰቃዩ፣ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ኑሮን እንዲገፉ የተገደዱበት  ድረጃ  ላይ  ተደርሷል።  በመቶ  ሺዎች   የሚቆጠሩ   የወደፊቱ   የአገሪቱ  ተስፋዎች የሆኑ ወጣቶች እንደዜጋ በሀገር ውስጥ  መኖር  ካልቻሉበት  ደረጃ  ላይ  በመድረሳቸው፣ የተሳካላቸው የስደት ኑሮን ሲያያftት፣ በርካታዎቹ ግን በቀይ ባህርና በሜዲቴራኒያን ባህር ውስጥ እየሰጠሙ ሕይወታቸው  እንዲያልፍ  ሆኗል።  የተወሰኑትም  የሰሃራ በረሃን ሲያቋርጡ በአክራሪ ftድኖች በመስዋዕትነት ተሰይፈዋል። በተጨማሪም እራሳቸውን በማኖር ዘመዶቻቸውን ለመርዳት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ሴቶች እህቶቻችን  ስብዕናቸው  ተገፎ  የዘመናዊ  ባርነትና  የውርደት  ኑሮን  እንዲገፉ   ተዳርገዋል።

ሀገራችን አሁን ለምትገኝበት ውጥንቅጥ  ችግር  ዋናው  መንስዔ  በጠብ-መንጃ  ኃይል  የሥልጣን  ኮርቻ  ላይ  የተፈናጠጠው  ሽበርተኛና  አምባገነን  የህወሓት/ኢህአዴግ   አገዛዝ   ነው።    በመሆኑም  አገዛft  በስፋት  እያካሄደ  ያለው  አፈናና  ግድያ  ያስመረረው     ሕዝባችን፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወገኔ በል ስማኝ ሀገሬ - ESFNA

 

ከስቃይ ኑሮ ለመላቀቅ ለብft ወራት የዘለቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳያግደው በአራቱም ማዕዘናት መብቱን ለማስከበር ትግሉን እያftftፈ ይገኛል። ሕዝባችን የነፃነት አየር ለመተንፈስና ሀገራችንን በዕድገትና ብልጽግና ጎዳና ላይ እንድትጓዝ ለማድረግ ከፍተኛውን መስዋትነት በመክፍል እያካሄደ ያለውን የሞት የሽረት የሀገር አድን ትግል፣ ሸንጎ ከልብ ይደግፋል። ይህ ትግልም እንዲጠናከርና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እንዲቀጣጠል፣ ብሎም ጎሰኛውንና ጎጠኛውን የግፍ አገዛዝ በተባበረና በተቀናጀ መልኩ ታግሎ  ለማስወገድ እንዲቻል ሸንጎ አቅሙ በፈቀደ መጠን ድጋፉን ይሰጣል፣ ሁለንተናዊ የሆነ ጥረት ማድረጉንም ይቀጥላል።

ሸንጎ በሦስት ቀን ጉባዔው ካሳለፋቸው በርካታ ውሳኔዎች ውስጥ አንኳር እንኳሮቹ፦

 

  1. ጉባዔው የሸንጎውን የሁለት ዓመት ዘገባ አዳምጦና በዘገባው ላይ ውይይት አካሂዶ ዘገባውን አጽድቋል።
  2. ጉባዔው እስካሁን ድረስ በአገዛft እየደረሰባቸው ያለውን መጠነ ሰፊ አፈና ተቋቁመው ሥርዓቱን እየታገሉ ካሉ የተለያዩ ድርጅቶች ጋር ያለው  ግንኙነቶች የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የተቀነባበረ የጋራ ትግል እንዲካሄድ    ወስኗል።
  3. አራተኛው ጉባዔው ሦስተኛው ጉባዔ ያፀደቀውን የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ዕድልን ከጥፋት ለመታገድ የሚመረጠውና የተሻለውን የሰላምና ዕርቅ አማራጭ እንደገና መርምሮ አሸባሪውንና አምባገነኑን አገዛዝ የሚወጥሩ ሁኔታዎችን  በመፍጠር በማስገደድ ወይም በማስወገድ የሥርዓት ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ አጠናክሮ ሕዝብን  ያማከል  ትግል  መቀጠል  እንዳለበት   ተስማምቷል።
  4. ሸንጎ ትግሉን ይበልጥ ኣጠናክሮ ለመቀጥል፡-

ሀ)  የሸንጎን  አምስት  መሠረታዊ  መርሆዎች ማለትም

  1. በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነትና     ሉዓላዊነት፣    የሕዝft                       የሥልጣን ባለቤትነት የማያወላውል ዕምነት መኖር፤
  2. የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና  የሰብዓዊ  መብቶች ማክበር፤
  3. በሀገራችን የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን መታገል፤
  4. በኢትዮጵያ ሕዝብ መካክል በፖለቲካ፣ በኤኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፎች አድሏዊነት ሳይኖር ሁሉም በሕግ ፊት እኩል ዜጎች  መሆናቸውን ማመንና በተግባር  ማረጋገጥ፣
  5. የህወሓት/ኢህአዴግን ሥርዓት ማስወገድና                                                በዴሞክራሲያዊ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የተፈራው ደረሰ ታላቁ ባለስልጣን ተገደለ ክልሉ አሁን መግለጫ ተጨማሪ ባለስልጣን ተገድሏል የአብይ አስደንጋጭ መግለጫ ምሽት በጀት ተደበደበ

ሥርዓት  መተካት ናቸው።

 

ስለዚህም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን መሠረት ያደረገ የብሄር ይሁን ኅብረብሄር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጠንካራና ሰፊ መሠረት ያለው የብሄራዊ አማራጭ ለማስተባበር ሸንጎ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲያድርገው የነበረውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ጉባዔው ተስማምቷል።

ለ) የሸንጎ ዓላማና ግቦች በኅብረተሰft ዘንድ ሰርፀው እንዲገftና የሕዝft መሠረታዊ መታገያ ዘዴ ሆነው እንዲያገለግሉ ማናቸውንም የመገናኛ ብftሃን ዘዴዎችን በመጠቀም አጠናክሮ ትግሉን እንዲቀጥል  ተስማምቷል።

ሐ) የሸንጎ አባል ድርጅቶችና ደጋፊዎች ባሉባቸው ከተሞች ሁሉ በስፋት በመንቀሳቀስ ኅብረተሰftን በንቃት የሚያሳትፉ የድጋፍ አካላት እንዲቋቋሙ ወስኗል።

  1. በሸንጎ ውስጥ የወጣቶችንና የሴቶችን ተሳትፎ ማጎልበትን በተመለከተ፦

ሀ) በየከተሞቹ ውስጥ በሚቋቋሙት የድጋፍ አካሎች ውስጥ  ተሳትፎ  እንዲያደርጉ   ተግቶ  መሥራት፣

ለ) በተቋቋሙትና በሚቋቋሙት ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ የተለያዩ  የማኅረሰft ተቋማት፣ በየአካባቢው እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት መሳተፍ  የሚለውን  ውሳኔ   አስተላልፏል።፣

  1. በመጨረሻም በአራተኛው ጉባዔ ማጠናቀቂያ በሦስተኛው ቀን ጉባዔው ሸንጎን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚመሩትን የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላትን መርftል።

ሀገራችን ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ ለማዳን፣  ሕዝባችን  ከሚገኝበት  የኑሮ  አዘቅት ውስጥ ለማውጣት የተቃዋሚ የአንድነት ኃይሎች የተባበረ ትግል ከምን ጊዜውም በላይ እጅግ አስፈላጊ ከሆነበት ደረጃ ላይ የተደረሰበት ጊዜ ነው። በሀገራችን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን የምንታገል ድርጅቶች ሁሉ ዛሬ መተባበርና በጋራ መታገል ካልቻልን በታሪክ ተጠያቂ እንደምንሆን ጉባዔው አስምሮበታል። የሀገራችን  ኅልውና አደጋ ላይ መሆኗን በማመንና ወገኖቻችን ለመብት መከበርና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሥረታ የሚያደርጉትን ትግል አንድ እርከን ከፍ ለማድረግ  ይቻል  የሸንጎ አራተኛ ጉባዔ የሚከተለውን ጥሪ  ያቀርባል።

 

  1. ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የወደፊት የሀገሪቷ ተረካቢ የሆነው  ወጣቱ ትውልድ፣ የሸንጎን ዓላማ በመደግፍ አብሮት  እንዲቆምና  የጀመረውን  እልህ  አስጨራሽ  ትግል  እስከ  መጨረሻው  የድል  ምዕራፍ  ድረስ  አጠናክሮ እንዲቀጥል፣
  2. የተቃዋሚ ኃይሎች ሁሉ በታሪክ ተጠያቂ እንዳንሆን ትግላችንን አቀናብረን በጋራ እንድንታገል፣
  3. በሥርዓቱ ውስጥ ተሰልፈው አምባገነኑንና አሸባሪውን አገዛዝ  እያገለገሉ  ያሉትን ሁሉ በተለይም የሠራዊቱና የደህንነት አባላት ከሕዝft ጎን እንዲሰለፉና በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን ከአሁኑ እራሳቸውን ነፃ እንዲያወጡ፣
  4. ህወሓት ጎጠኛና አሸባሪ ftድን በመሆኑ የትግራይን ሕዝብ  ጥቅም  ሳይሆን  የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያስከብር ስለሆነ የትግራይ ሕዝብ  ይህንን  ተረድቶ  ከኢትዮጵያ  ሕዝብ ጎን በመሰለፍ በስሙ እየነገደ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ለማስወገድ ትግሉን እንዲያዲያፋፍም፣
  5. የዓለምአቀፉ ማኅብረተሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ሁለንተናዊ ጭቆናና የሰብዓዊ መብት ረገጣን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ እያካሄደ ያለውን ትግል ደግፎ  ከጎኑ  እንዲቆም  እናሳስባለን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለማይቀረው እና ለመጨረሻው ትግል ከዚህ ፍሽስት ከወያኔ አገዛዝ ጋር ለሚደረገው ትንቅንቅ እራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘጋጅ !!!
Share