Art: የዘመኑ ቀልብ ቀልባሽ ድምጻዊያኖች

በተስፋሁን ብርሃኑ

ዘመናዊ ሙዚቃ በኢትዮጵያ ከተጀመረ አራት አስርት ዓመታትን አሳልፏል፡፡ በነዚህ ዓመታት በርካታ ዘመን አይሽሬ ድምፃውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ነግሰውበታል ዘመን አይሽሬ ከሚባሉት ድምፃውያን በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ድምፃውያን መካከል ጥላሁን ገሠሠ፣ ሚኒሊክ ወስናቸው፣ መሀሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ አስቴር አወቀ፣ ኩኩ ሰብስቤ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
በቀደሙት ዓመታት የነዚህ ድምፃውያን ስራዎች በሰፊው ይደመጡ ነበር፡፡ ካሴቶቻቸውም በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን አግኝቶ ነበር ምክንያቱ ደግሞ የግጥሙ ይዘት ዜማውና ድምፃውያኑ የእውነት ዘፋኞች በመሆናቸው ሙዚቃቸው አሁን ድረስ ከመደመጡ ባሻገር ለአዳዲስ ድምፃውያን የድምጽ ማሟሻ እየሆናቸው ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ ድምፃውያን ለገንዘብና ለዝና ሲሉ ሳይሆን የእውነት ሙዚቃ ጠርታቸውና መርጣቸው በመሆኑም ጭምር ነው፡፡

አሁን አሁን ገና ለገና ገንዘቡንና አጋጣሚውን ያገኙ በርካታ ድምፃዎያን ነን ባዮች ግራ የገባው ግጥምና ዜማ ይዘው በመምጣታቸው በርካታ የሙዚቃ ወዳጆችን የኢትጵያ ሙዚቃ ወደየት እየሄደነው እንዲሉ እያስገደዳቸው ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአዳዲስ ድምፃውያን የሚወጡ ሙዚቃዎች አንድ ዓይነት ማለት ይቻላል ሴቶችን የሚያባብሉ፣ ብሶቶችና ‹‹የዛሬን ተደሰት የነገን ነገ ያወቃ›› የሚል መንፈስ በመያዛቸው አገር ተረካቢውን ወጣት ምንም እንዳይሰራና የጨለምተኛ አስተሳሰብ እንዲያዳብር እያደረጉት እንደሚሄዱ ምንም አያጠያይቅም፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ብዙ ሺህ ኮፒዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ የተሸጡለትና የቀደሙትን
ዘመን አይሽሬ ድምፃውያንን ይተካል የሚባልለት ቴዲ አፍሮ /ቴዎድሮስ ካሳሁን/ ከሰባት ዓመታት በኋላ በ2004ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ካወጣው ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም በፊት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ ቢያቀርቡም የበርካታ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ መግዛት ሳይችሉ ቀርተው ነበር፡፡ ይህ ጥቁር ሰው› አልበም በእውነትም እጅግ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አነቃቅቷል ማለት ይቻላል ምክንያቱ ደግሞ ካሴቱ ከወጣ ሰዓት ጀምሮ በሰልፍ ተሽጧል በሙሉ ማለት ይቻላል ዘፈኖቹ ታሪክን፣ አንድነትን ፍቅርን በመስበኩ በእጅጉ ተወዶ ነበር ብራቮ ቴዲ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Betoch | “አጥፍቶ ጠፊ”Comedy Ethiopian Series Drama Episode 309

በዚህ በያዝነው 2005 ዓ.ም በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአደማጭ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን በለስ ቀንቷቸው የአድማጮችን ቀልብ የገዙት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው በዚህ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት ዓመት ከተወዳጅ ድምፃውያን መካከል ጃሉድ፣ አቤል ሙሉጌታ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ጃኖ ባንድ፣ ፀጋዬ እሸቱ የቀደመውን ዜማዎቹ እንደ አዲስ ያቀረበበት እንዲሁም አሁን በሰፊው እየተደመጠ ያለው ‹‹ስጦታሽ›› የሸዋንዳኝ ሀይሉ ካሴት በእጅጉ የሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቷል፡፡ በዚህ በያዝነው ነሐሴ ወር ሌላ አዲስ አልበም ወጥቶ በሰፊው እየተደመጠ ይገኛል፡፡ ‹ሲያ ሲያ› ፣ ‹አልችልማ› በሚባል ክሊፓቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘው ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር /ተሙ/ አዲስ ካሴት አሳትሟል የመጀመሪያ ካሴቱን በራሱ ወጪ አሳትሟል፡፡ ይህ ካሴት በወጣ በአጭር ጊዜ የመጀመሪያው ህትመት በጥቂት ጊዜያት ተሽጠው በማለቃቸው በድጋሚ እንደታተመ ተነግሯል፡፡ በሌላ በኩል ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት በዚህ ዓመት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ አቅርበዋል፡፡ ካሴቶቻቸውን አውጥተው ብዙም ተደማጭነትን ካላገኙት ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል አስቴር ከበደ፣ ነፃነት መለሰ፣ አበባ ደሳለኝ፣ ይገኙበታል፡፡ ከዓስር ዓመት በፊት የህበረተሰቡ አዲስ ካሴት ሲወጣ የመግዛት ዝንባሌው በእጅጉ ከፍተኛ ነበር ለማለት ይቻላል አሁን አሁን ግን
አዳዲስ የሚወጡ ካሴቶችን በተለያዩ ሚዲያዎችና ድህረ ገጾች ካሴቶቹ በወጡ በጥቂት ቀናት በመለቀቃቸው ምክንያትና በዘፈኖቹ ጥራት አብዛኛው ህብረተሰብ አዲስ ካሴት ገዝቶ የማዳመጥ አዝማሚያ አይስተዋልም፡፡ የህብረተሰቡ ካሴት ገዝቶ የማድመጥ ባህሉም ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰና ነጠላ ዜማዎችን ብቻ የማየትና
የማድመጥ አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መሀልም አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን አንዳንዶቹ ስራዎቻቸውን ማቅረባቸው አልቀረም ከነዚህ ውስጥ ታዲያ በግጥሞቹ በሳልነትና በድምፁ እስከ አሁን እየተደመጠ ያለው አቤል ሙሉጌታ አንደኛውነው፡፡
ይህ ወጣት ድምፃዊ በቤተክርስቲያን አካባቢ በማደጉ ለግጥምና ለዜማ እንዲሁም ለድምፅ ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገለት ይመሠክራል አንጋፋው ፀጋዬ እሸቱም ከቀድመው ተወደውለት ከነበሩት ሙዚቃዎቹ መካከል መርጦ በሙሉ ባንድ ያወጣው ካሴትም እጅግ ተወዶለታል፡፡ ከሰባት ዓመት በኋላ ‹‹ ስጦታሽ›› በተሰኘው አዲስ
አልበም የመጣው ሸዋንዳኝ ሀይሉ አንጀት የሚያርስ ሙዚቃ እንደሰራ ብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያንና የሙዚቃ ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አልበም ውስጥ በርካታ ስመጥር ገጣሚያን የተሳተፉበት ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ የቴዲ አፍሮ ግጥም በአልበሙ ተካቷል፡፡ ወጣቱ ድምፃዊ ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር
ተሙ ሌላው 2005 ዓ.ምትን ካደመቁት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው ይህ ወጣት ድምፃዊ በሦስት ነጠላ ዜማዎቹ የብዙ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቶ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በአዲስ አልበም ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ካሴቱ በወጣ በጥቂት ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ የታተመለት ይህ ድምፃዊ ሙሉ የካሴቱን ወጪ በራሱ ማሳተሙ ለሙዚቃው የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን አስመስክሮለታል ይህን ካሴት በርካታ አቀናባሪዎች የሰሩት ሲሆን ማስተሩን ታዋቂው አበጋዝ ሺዌታ ሰርቶለታል፡፡ በ2005 ዓ.ም እጅግ ካሴቶቻቸው የተደመጠላቸው ጃሉድ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ፀጋዬ እሸቱ፣ ሸዋንዳኝ ሀይሉ እንዲሁም ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር ነበሩ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ጨርሰው ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) በሚኒሶታ የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ

3 Comments

  1. that is really a perfect commercial for those of them u r near.but z reallity looks different.
    yewededenewen lemerdat belen ke’ewenet anerak

  2. men aynet research serteh new endih bdefret y ekele tedemtual yeekele altedemetem yemetelew kechalk please send me research paperehen

Comments are closed.

Share