Hiber Radio: ኢህአዴግ የሾማቸው ዳኛ በጉቦ ክስ ፍ/ቤት ቀረቡ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ የካቲት 17ቀን 2005 ፕሮግራም
<<…ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ ትግስት ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ነው ታፍነው ተሽጠው ዛሬ ሲና የሚገኙት። አጋቾቻቸው የጠየቁትን ገንዘብ ካልተሰጠ ገድለው ኩላሊታቸውን፣ልባቸውንና ሌላ የፈለጉት አካላቸውን ይሸጡታል። ሰሞኑን የአንዲት ሌላ ኢትዮጵያዊ ሞት መርዶ መጥቷል።የወይዘሮዋን ነፍስ አድነን ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር እናቀላቅላቸው። ሕይወት እናትርፍ ጊዜ የለንም ..>>
ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ የሚኒሶታ ነዋሪ ሲና በረሀ በአጋቾቻች እጅ የሚገኜትን ኢትዮጵያዊ አስመልክተው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
<<…ባለቤቴ አሁንም በሲና በረሃ አጋቾቿ እያሰቃዩዋት ነው።እባካችሁ ከነወ/ሮ ሰብለ ጋር ተባበሩ…እኔ እዚህ ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ጥላ የሔደቻቸውን ልጆች ይዤ ተቀምጫለሁ። እዚያ ይደበድቧቸዋል፣ዘቅዝቀው ያሳድሯቸዋል…>> አቶ መልካሙ ባዬ (ከሱዳን ስደተኞች ጣቢያ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተ ክርስቲያኑዋን የሚመራት መንግስ መሆኑን አውቋል።ቤተ ክርስቲያን መመራት ያለባት በመንፈስ ቅዱስ ነው። ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ውስጥ ናት።አባቶች.ምዕመናን ከህጋዊው 4ተኛ ፓትርያርኩ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ጎን በአንድነት መሰለፍ አለባቸው። መለያየት ያበቃ ይመስላል።ሁሉም ዕውነቱን አውቋል። …>>
ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ የኔዛዳ፣
የአሪዞናና ዬዩታ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ም/ዋና ጸሐፊ(ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ)
ዜናዎቻችን
አንድ የነዳጅ አሳሽ ድርጅት ከኦጋዴን አካባቢ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
በሳዑዲ 53 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በቤት ውስጥ ባደረጉት ሀይማኖታዊ ስርዓት ሳቢያ ታሰሩ
አቡነ ሳሙኤል ለጵጵስና ሹመት የቡድን ትግልና መንግስ የፈለገውን እንደሚሾም አረጋገጡ
ሜትሮ ፖሊስ በቬጋስ ራፐሩን ተኩሶ ገድሏል ያለውን ተጠርጣሪ ማንነት ይፋ አደረገ
በግድያው ጦስ በተረሰተው አደጋ ታክሲ ተቃጥሎ ሹፌሩና ተሳፋሪዋ ሞተዋል
ኢህአዴግ የሸማቸው ዳኛ በጉቦ ክስ ፍ/ቤት ቀረቡ
በኢትዮጵያ ሰሞኑን ሶስት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ተጨማሪ ያንብቡ:  የክህደት ጥግ ሲጋለጥ....!
Share