February 26, 2013
7 mins read

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም! በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

       ትላንት የተናገሩትን  ዛሬ፤ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡

እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop