ቅድመ ጥንቃቄ፤ በሶማሌ ክልል ለምትኖሩ የአማራ ተወላጆች (ሙሉቀን ተሰፋው)

ሕዝባችን ከትግሬው ጥቁር ፋሽስት ቡድን ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡ የ2009 ቀጣይ ወራት ለነጻነት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ብሎም ነጻነታችን የምንቀዳጅበት እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለም፡፡ ሆኖም ይህ ፋሽታዊ ሥርዓት መሸነፉን እየተረዳ በሔደ ቁጥር የሚወስዳቸው እርምጃዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ስለሚሆን ጉዳት ማስከተሉ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት ባለፈው ነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም. በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው የጅምላ ግድያ አዋጅ እስካሁን ያልተነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት በደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል ሲያከብሩ በነበሩ ወገኖቻችን ላይ የተከሰተው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ማውሳት ይቻላል፡፡
ሁሉም የአማራ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ አገዛዙን መፈናፈኛ ሲያሳጣው በሌላ አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱ የማይቀር ነው፡፡ በመቀሌ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ የአማራ ተወላጆች አደጋ ላይ መሆናቸውንም እየሰማን ነው፡፡ ሆኖም መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ አደጋ ከተጋረጠባቸው አማሮች ዋነኛዎቹ በሶማሌ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህ የትግሬ ፋሽስት ከሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ጋር በመተባበር በክልሉ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በተናጠልና በቡድን ለመጨረስ እንደሚንቀሳቀሱ ብዙ ማረጋገጫዎች እየመጡ ነው፡፡ የሶማሌ ክልል የሚተዳደረው ሐረር በተቀመጡ በትግራይ ጄኔራሎች አማካሪነት መሆኑም ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ጊዜያት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በአገሪቱ ተቋጦ መረጃ ለመለዋወጥ አስቸጋሪ ሁኔታ ስለሚፈጠር በሶማሌ ክልል የሚኖሩ አማሮች በቀጣይ ጊዜያት ከተደገሰላቸው እልቂት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልእክቱን አስቀድሞ በግልጽ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በዚህ መሠረት በሶማሌ ክልል በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ አማሮች ራሳችሁን ለመከላከል ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡
 ከሶማሌ መውጣት የምትችሉ ሰዎች ከአካባቢው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች ወይም ወደ መሀል አገር መሸሽ፤
 በቀጣይ ጊዜያት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ስለሚችል በሶማሊላንድና በኬንያ አካባቢ የጎረቤት አገሮችን ኔትወርክ በመጠቀም ሁኔታዎችን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቅ እንዲሁም፤
 ክልሉን ለቃችሁ መሔድ የማትችሉ ከሆነ ደግሞ በሕብረት በመተጋገዝ የሚሰነዘርባችሁን ጥቃት መመከት ይጠበቅባችኋል፡፡
የአማራ ተጋድሎ ያሸንፋል//

ተጨማሪ ያንብቡ:  20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ
Share