Hiber Radio: ግርማ ብሩ ለሕወሓት ደጋፊዎች በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ክሰሱ ያሉበት ምስጢራዊ ድምጽ ወጣ | ሳዲቅ አህመድ በምስራቅ ሐረርጌ 2 መስጊዶች ላይ ስለደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ተናገረ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 22 ቀን 2008 ፕሮግራም

< ... ሕወሓት ትላንትም የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ነበር ዛሬም ተስፋ ሲቆርጡ በያንን እያደረጉ ነው። በምዕራብ ሐረርጌ በመስጊድ ላይ ያፈነዱት ነገ ተነገ ወዲያ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ሊያደርጉት ይችላሉ ተስፋ የቆረጠ ድርጅት ... ተቃውሞው በጋራ ማስተባበር ያስፈልጋል መናበብ ያስፈልጋል ብሄራዊ የስንብት ቀን ይባል ሌላ አገር አቀፍ ሁሉንም ያሳተፈ ተቃውሞ ለማካሄድ የሁሉም የለውጥ ሀይሎች በጋራ መቆም ወሳኝ ነው። ስርዓቱን ወደ መቃብር ለመሸኘት ፤ቅንጅት፣ ህብረት የጋራ ትብብር ያስፈልጋል። ምዕራባውያኑ ግን... > ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድ በምዕራብ ሐረርጌ በሁለት መስጊዶች ላይ ፍንዳታ ተፈጽሞ ንጹሃን ሰለባ ስለሆኑበት ሂደት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብሁሃን ስለ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ያቀረቡት ዘገባ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ በተደረገ ተቃውሞ ላይ የሀይማኖት አባቶችን ቸምሮ የተለያዩ ቡድኖች ያስተላለፉት መልዕክት

ዜናዎቻችን

አምባሳደር ግርማ ብሩ ከአገዛዙ ደጋፊዎች ጋር በምስጢር ባደረጉት ውይይት በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ክሰሱ ሲሉ ተደመጡ

የምስጢር ስብሰባው ድምጽ ማስረጃ ደርሶናል

የአማራ ሕዝብ ተጋድሎና ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አትሌት ኢብሳ እጅጉ የታላቁን አትሌት ፈይሳ ለሊሳን የሪዮ ተቃውሞ በካናዳ ማራቶን አሸንፎ ደገመው

የሕዳሴውን ግድብ ለመጎብኘት የሔዱ ባለስልጣናት ተቃውሞ ላይ ባሉ የጎጃም አማሮች ተገደው ጉብኝታቸውን ሰርዘው መመለሳቸውን ገለጹ

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ጸረ ሕወሓት/ኢህአዲግ ጥምረት ለአገዛዙ ታላቅ ፈተና መሆኑን ታዋቂው አፍሪካን ኮንፊደንሻል መፅሔት አጋለጠ

* 6 ሜሊዮን የአገዛዙ ካድሬዎች ድርጅቱን ገዝግዘው እየጣሉት ነው ተባለ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖ አጣየና ሰከላ ከተሞችን ተቆጣጠረ | ጎንደር ታላቁ ጦርነት ተጀመረ | ፋኖ ደሴን ለመቆጣጠር ደርሷል | ፋኖ ባ/ዳር ላይ እጅግ አሳፋሪ ጥቃት አከናንቦናል"

የብአዴን እና የኦህዴድ ባለስልጣናት ህዝባቸውን ለችግር አጋልጠዋል ተባሉ

ኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሊፈራረሙ መሆኑን የካርቱም ባለስልጣን ተናገሩ

በሳውዲ አረቢያ ህንጻ ተደርምሶ ኢትዮጵያዊ እና ግብጻዊያኖች ህይወታቸው አለፈ

ግብጽ ዜጎቾን ለመታደግ ልኡካን ወደ ስፍራው ልካለች

*የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ግን ዝምታን የመረጡ ይመስላሉ

*በኩዊት አንዲት ኢትዮጵያዊት ከባህር ውስጥ ሰጥማ ህይወቷ አለፈ

የአሜሪካው እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ በምርቻው ካሸነፉ የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተቃጠለባቸውና ቪዛቸው ያለቀባቸውን ጭምር ከአገር አባርራለሁ ሲሉ ዛቱ

የሞህ ፋራህን ወንድም እንግሊዝ ከአገሬ አባርራለሁ አለች

በምርጫ 97 እንዳደረገው ሕወሃት በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆችን ብቻ ለይቶ ስብሰባ ጠራ

ሌሎችም

Share