ኤርሚያስ አመልጋ በመጨረሻም “ለጊዜው” ተፈታ

(ዘ-ሐበሻ) በአንዱ ክስ በዋስ ሲፈታ እንደገና በሌላው ሲታሰር የቆየው ነጋዴ ኤርሚያስ አመልጋ 3ኛው ክስ ከተመሰረተበት በሗላ ትናንት መፈታቱ ተሰማ::

ኤርሚያስ አመልጋ ለጊዜውም ቢሆን ትናንት ተፈቶ ቤተሰቡን የተቀላቀለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛው ችሎት የቀረበበትን 3ኛ ክስ ውድቅ ካደረገው ከ11 ቀናት በኋላ ነው:: ፖሊስ አቶ ኤርሚያስን ፍርድ ቤት ከለቀቃቸው በኋላ ለምርመራ አቆይቷቸው እንደነበር መዘገቡ አይዘነጋም””

በአጠቃላይ በቀረቡበት ክሶች 1.1 ሚሊዮን ብር በዋስትና ያስያዘው ኤርሚያስ አመልጋ አሁንም እንደማይታሰር ምንም ማረጋገጫ የለም:: እንደ አስተያየት ሰጪዎች ገለጻ ከአንድም 3 ጊዜ ሲፈታ ፖሊስ አዳዲስ ክሶችን እየፈለገ ሲያስረው ቆይቷል::

ከቤት መስራት ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወስዶ ቤቶችን አላስረከበም በሚል የሚሰሰው ይኸው ነጋዴ ገንዘቡን በኮንስትራሽን ሰበብ የተቀብሉት የሕወሓት ሰዎች እንደሆኑ ይነገራል::

የ59 ዓመቱ ኤርሚያስ በአሜሪካ የተሳካለት የንግድ ሰው የነበረ ቢሆንም በሃገሬ ላይ ሰርቼ እኖራለሁ ብሎ ገብቶ በሕወሓት ነጋዴዎች የሚሰቃይ ሰው ሆኗል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርካታ ናቸው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  Ethiopia to buy more than 200 T-72 tanks from Ukraine for $100 million
Share