ባለፈው ምርጫ የኦፌኮ እጩ ተወዳዳሪ የነበረው ኢንጅነር በዳዳ ጋልቻ በህወሃት አጋዚ አንጋቾች በጥይት ተደብድቦ ተገደለ

የደህሚት ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው በዳዳ ጋልቻ የጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወረዳ መጋደር ቀበሌ ነዋሪ የነበረና በምህንድስና ትምህርት ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ስራ ማግኘት ስለተሳነው ሥራ ፈጥሮ ለመስራት ያቀረበውን ጥያቄም የአካባቢው አስተዳደር በውል ባልተገለፀ ምክንያት ውድቅ ስላደረገበት ድግሪውንና የስራ እቅዱን ወደጎን በመተው ሙሉ በሙሉ በግብርና ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ ማሳው ላይ በደቦ ሲሰራ ውሎ ሲመለስ አጋዚዎች ደጋግመው በጥይት መደብደባቸውንና ወደ አዶላ ሆዬ ሆስፒታል ቢወሰድም እንኳን እንደደረሰ ከምሽቱ 2።30 አካባቢ ህይወቱ ማለፉን ያገኘነው መረጃ ገልጿል።

መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው ተኩስ ሰምቶ የተሰበሰበውን የአካባቢ ህብረተሰብ የአጋዚ አንጋቾች ደጋግመው በመተኮስ እንዲበተን ማድረጋቸውን በመግለፅ በዳዳ ከወር በፊት የሼክ መሐመድ ሁሴን አልሙዲን የአኮቴ የወርቅ ፕሮጀክትና የማስተር ፕላኑን በመቃወም ተካሂዶ የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ አስተባብሯል በሚል ይጠረጠርና ይፈለግ እንደነበር ዳንኤል ቦሩ እና ጋሪ ሶኒ የተባሉ የአይን ምስክሮች መናገራቸውን አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ
Share