(ዘ-ሐበሻ) ፎርብስ የተባለው ታዋቂ የቢዝነስ መጽሔት የዓለማችንን 10 ሃብታም ክለቦች ዝርዝር አውጥቷል:: የስፔኖቹ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ ማን.ዩናይትድ እና ባየር ሙኒክ 3ኛ እና 4ኛ ሆነዋል:: እንደ መረጃው ከሆነ ባለፉት 3 ዓመታት ምንም ድል ያላጣጣመውና ደጋፊዎቹንም እያስከፋ የሚገኘው ማን.ዩናይትድ እስካሁን በ3ኛነት መቀመጡ የሚያስደንቅ ነው::
ደረጃውን ከነሃብታቸው መጠን ያንብቡት:
1. ሪያል ማድሪድ 2.52 ቢልየን ፓውንድ
2. ባርሴሎና 2.46 ቢልየን ፓውንድ
3. ማንችስተር ዩናይትድ 2.3 ቢልየን ፓውንድ
4. ባየርን ሙኒክ 1.85 ቢልየን ፓውንድ
5. አርሰናል 1.4 ቢልየን ፓውንድ
6. ማን.ሲቲ 1.33 ቢልየን ፓውንድ
7. ቼልሲ 1.15 ቢልየን ፓውንድ
8. ሊቨርፑል 1.07 ቢልየን ፓውንድ
9. ጁቬንቱስ 900 ሚልየን ፓውንድ
10. ቶተንሀም 704 ሚልየን ፓውንድ