May 19, 2011
7 mins read

የታክሲዎች ስራ ማቆም እንድምታ – በእስክንድር ነጋ

አስኮ፣ ላፍቶ፣ ለቡ፣ አያት ፣ ሲ.ኤም.ሲ፣ ዓለም ባንክ፣ ቀራንዮ፣ ኮተቤ፣ ቃሊቲ… የማለዳ ታክሲ ለወትሮውም መከራ ነው። ግፊያው የድብድብ ያህል ነው። ትላንት ሰኖ ግምቦት 8/2003 ግን ፣ ተጋፍቶ የሚገባበት ታክሲ የጠፋው ገና ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነበር። የአንድ አዓቱን ግፊያ እየሸሸ ቀደም ብሎ ከቤቱ የሚወጣው የከተማው ነዋሪ ታክሲዎች ምር አድማ መተዋል ብሎ መጠርጠር የጀመረው የወትሮ ደምበኞቹ የውሃ ሽታ ሆነው ሲቀሩበት ነበር። የቻለ እንደ ሰርዲን በሞጠቀጠቁት አውቶቢሶች ላይ እንደምንም ተሰጉጦ አመለጠ። ከፊሉ በእግሩ አስነካው። እድለኛው የቤት መኪና እየተባበረው በምቾት ወደ መሀል ከተማ ዘለቀ። ብዙዎች ከስራና ከትምህርት ቀርተው ወደቤታቸው ተመለሱ።

የሚገርመው በተፈጠረው እንግልት ያዘነና የተቆታ እምብዛም መሆኑ ነበር። ለወትሮው፣ የአዲስ አበባ ነዋሪና ታክሲዎች ብዙም አይፋቀሩም። ህዝቡ ታክሲዎችን አማርራል። ታክሲዎች ህዝቡን ያማርራሉ። ተቻችለው የሚኖሩት የግድ ነው። በዚህች እለት ግን የታክሲዎቹ ህብረት የህዝቡን ልብ አሸንፏል።

ይሄ ህዝብ መተባበር የጠማው ህዝብ ነው። ከቀይ ሽብር በኋላ በምርቻ 97 ለአጭር ጊዜ ብልጭ ብሎ ድርግም ብሎበታል። መከዳዳት፣ መጠላለፍ፣ መሰባበቅ፣ መወነጃጀል፣ መራራቅ፣ እንደሬት የመረረው ህዝብ ነው። እንደቱኒዚያ፣ እንደ ግብጽ፣ እንደ ሶሪአ፣ እንደ የመን ሚሊዮኖች በአንድ ሳምባ ለመተንፈስ የጓጓ ህዝብ ነው። ከምንም በላይ ህዝቡ በታክሲዎች ህብረት ተደስቷል።

በዛ ላይ፣ ከታክሲዎቹ ጥአቄ በስተጀርባ አለውን እውነታ ሕዝቡ የሚጋራው ነው። ጣሪያ በነካው የዋጋ ግሽበት አልተደቆሰ ጠህብረተሰብ ክፍል የለም። ህዝቡ መኖር እአቃተው ነው። በሽሮ እንካን መኖር ከብዷል።

የታክሲ ገቢ ባለበት ከቆመ ሁለት አስር አመታት ተቆትረዋል። ኢህአዴግ በ1983 ስልጣን ሲይዝ የታክሲዎች የእለት ገቢ ከ100 እስከ 120 ብር ነበር። ከሃያ አመታት በኋላ ዛሬም ያው ነው። የቤንዚን ዋጋ ግን በሌትር ከሁለት ብር ወደ ሃያ ብር ተሰቅሏል። የሾፌሮቹም ገቢ ባለበት የቆመ ነው።

የታክሲ ስራ ሩጫ ነው። አድካሚ ነው። ነጻነትም የሚሳ ነው። ወደ አንድ አቅጣጫ ተሳፋሪ ይዞ ሄዶ ተመላሽ ከጠፋ፣ ኪሳራ ነው። የታክሲ ሾፌር ከመሬት ተነስቶ የሚወደውና የሚጠላው ሰፈር የለም። እንዲያዋጣው ሲሄድም ሲመለስም ተሳፋሪመሙላት አለበት። ከቤንዚኑ ውድነት አኳያ በከፊል እየሞላ መመላለስ አያዋጣም። ስለዚህም፣ የታክሲን አቅታጫ የሚወስነው ገበያው ነው፣ ሾፌሩ ወይም ባለቤቱ አይደለም። ኢህአድግ ግን አሁን እኔ ልወስን እያለ ነው፡፤ ገበያው ስላልሰራ መንግስት ጣልቃ መግባት አለበት ባይ ነው።

ኢህአዴግ ገበያው ችግር እንዳለበት ሲናገር የመጀመሪያው አይደለም። የሚዝ፣ የስኳር፣ የስጋ፣ የዘይት ዋጋዎችንም አስተካክላለሁ ብሎ ከተነሳ ሰነባብቷል። ውጤቱ ግን አልሰመረም። ሸቀጦቹ ከገበያ ጠፍተዋል። የስኳርና የዘይት ግዢ ሰልፎች የአዲስ አበባ መለያዎች እየሆኑ ነው። የዋጋ ግሽበቱ ደግሞ ጭራሽ ተባብሶ 30 ከመቶ ደርሷል። በሌላ አነጋገር፣ መንግስት ታች ድረስ ወርዶ ሲቆጣጠር ውጤቱ የተበላሸ ነው የሚሆነው። በሸቀጦቹ ዙሪያ የተፈጠረው ችግር ወደታክሲዎቹ ላለመሄድ ታኮ ሊሆን ይገባ ነበር።

ባለታክሲዎቹም ሆኑ የታክሲ ሾፌሮች የስምሪት ህጉ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት እንደማያዋጣቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አበክረው ተናግረዋል። ኢህአዴግ ግን የሚናገርበት እንጂ የሚያዳምጥበት ጆሮ የለውም። ሰሚ አላገኙም። ወደስራ ማቆም የሄዱት ተገደው ነው። ምርጫ አልነበራቸውም።

ኢህአዴግ ለስራ ማቆሙ ምላሽ የአዲሱ ዘመን ማብሰሪያ ሆናል። የወትሮው ፉከራ፣ ሽለላ፣ ማስፈራራት፣ ድብደባና እስር አልተተገበሩም። ድምጹን ማጥፋት ነው የመረጠው። ወደ ክፍለ ሀገር የሚወጡ ሚኒባሶችና አውቶቡሶች ክፍተቱን እንዲሞሉ ጥሯል። ደጋፊዎቹ ታክሲዎች ወጥረው ሰርተዋል። ከነበረው እጥረት አኳያ ግን፣ ክፍተቱ አልተሞላም።

ሰኞ ሰፋዱ ላይ ስምሪቱ እንዲቆምና ታክሲዎች እንደልብ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ የቃል መመሪያ ተሰቷቸዋል። በዚህ የተደሰቱ በርካታ ታክሲዎች አመሻሹ ላይ ወጥተዋል።

ዛሬ ማክሰኞ ታክሲዎች በብዛት አሉ። የሚሰሩት ግን በተሰጣቸው መስመር ብቻ አይደለም። አንዳንዶች እንደፈለጉ ይሰራሉ። የሚናገራቸው የለም። መጨረሻው አይታወቅም።

የስራ ማቆሙ አድማ ተሳካም አልተሳካም ግን፣ ቢያንስ ቢያንስ ህዝብ መተባበር እንደሚችል አሳይቶናል። ይህ ታላቅ ቁም ነገር ነው። በሁለተና ደረጃ ደግሞ፣ የኢህአዴግ እብሪት መተንፈሱ ታውቆበታል። ይህ ደግሞ፣ ለኢህአዴግም፣ ለህዝቡም፣ ለሀገርም የሚበጅ ነው

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop