የሮማዉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ የሪፐብሊካኑን ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ በመቃኘት “ክርስታናዊ አይደለም!” ሲሉ ታላቅ የጥያቄ ምልክት አሳርፈዉበታል። መልስ ከመስጠት ያልታቀቡት ቱጃሩ ትራምፕ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሱን ንግግር “አሳፋሪ!” ሲሉ አጣጥለዉታል። የካቶሊክ እምነት መንፈሳዊ አባት የሆኑት አቡነ ፍራንሲስ ተዘልፈዉ 70 ሚሊዮን የሚሆኑ የአሜሪካ ካቶሊኮች ትራምፕን ይመርጣሉን? የካቶሊክን ድምጽ ሳይቀበሉ ትራምፕ የፓርቲያቸዉ እጩ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉን? የትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ወደ ማሽቆልቆል የተቃረበ ይመስላል። እየደበዘዘ ባለዉ የምርጫ ዘመቻቸዉ ዉስጥ ትራምፕ ምን ያህል በርተዉ መቆየት ይችላሉ? በቀናት ዉስጥ የሚወሰን አይመስልምን? ሳዲቅ አህመድ የሰራዉን ፕሮግራም ይከታተሉ።