ትግራይ ጡረተኛ የጦር መኮንኖች በነጻ የመታከም መብታቸው ተነጠቀ

አቶ አሰገደ ገብረሥላሴ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ መሠረት የሀገር መከላከያና የፖሊሥ ሠራዊት የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሠው ጡረታ ከወጡ እሥከ ህልፈታቸው ከዝቅተኛ አሥከ ከፍተኛ ህክምና በነጻ እንደሚታከሙ ህገመንገሥት ያሥቀመጠላቸው መብት እያለ ሥለ ህገመንግሥት.. ሥለ የዜጎች መብት ይከበር ኣይከበር ደንታ የሌለው የኢህኣደግ መንግሥት ወታደራዊ ጡረቶኞች በነጻ መታከም የሚባል የለም በማለት ለህክምና የሚሆን እንደ ኡንሹራንስ የሚታሠብ 1% ከጡሮታ አበላቸው ይቆረጥ ብሎ ድንገት  ትእዛዝ ተላልፉዋል።

በተጨማሪም ጡረተኛ መኮንኖቹ ለወደፊት እንዴት እንደሚታከሙ የታወቀ ነገር የለም::

የህክምና ኢንሹራንሥ ያለውድ በግድ መቋረጡ በፖሊሥና በሀገር መከላከያ ሠራዊት ጡረቶኞች ብቻ ያቆመ ኣይደለም ያለው የአቶ አሰገደ ዘገባ ለሲቭል የመንግሥት ሠራተኛ ጡረቶኞች 2% ከጡሮታ ኣበላቸው ይከፍላሉ:: እንዲሁም በሥራ ላይ ያለው የመንግሥት ሠራተኛ 3% ከደሞዙ ለህክምምና ኢንሹራንስ ያለፍላጎታቸው በግድ በመቆረጡ በ መንግሥት ሠራተኛና በጡረቶኞች ተቃውሞ እያሥነሣ ይገኛል ::

ይህ የኡንሹራንሥ ገንዘብ ሢቆረጥ ከማን እንሹራንሥ ሥምምነት እንደተደረገ ; የህክምና ደረጃ ከየት እሥከየት የህክምና እድል ኣለ? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም::
ሌሎች ወታደር ጡሮቶኞችም እንዲሁ እየተነሳ ያለው ጥያቄ በጃንሆይና በደርግ ሥርዓቶች የነበረን የመታከም መብት ለምን እንነጠቃለን? የሚሉ ናቸው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሙሽሮቹ በሰርግ ቀናቸው ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በማምራት እስረኞችን ጠየቁ
Share