By: Asress
ያውራምባው ታይምስ ድረ ገጽ ባለቤት ዳዊት ከበደ እንደብዙዎቹ ጋዜጠኞች በምርጫ 97 ታስሮ ከተፈታ በኋላ ትግሬ በመሆኑ ምክንያት ተመልሶ ጋዜጣ ከመጻፍ አልተከለከለም:: አዲስ አበባ እያለ አውራምባ ታይምስ በተባለ ጋዜጣው ላይ ብዙ የህውሃት ጉዶችን ሲዘግብ ብዙዎቻችችን እናስታውሰው አለን:: በቅርቡ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላም ለተዎሰነ ግዜ በኢሳት ቀርቦ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ እና ኢህአዴግን ሲቃዎም ሰምቸው ነበር::
ከቅርብ ግዜ ዎዲህ ግን በየግዜው በድረ ገጹ ላይ እየለጠፋቸው የነበሩትን የታማኝን የአበበ ገላውን እንዲሁም የሌሎቹን የዎያኔ ተቃዋሚዎች የጻፏቸውን ጽሁፎች በድረገጹ ማስተናገድ አቁሟል:: ይባስ ብሎም ትግሬ በመሆኔ አንዳንድ ዲያስፖራዎች አገለሉኝ በማለት በቀል በሚመስል መልኩ የተቃዋሚዎችን ጹሁፎች ለማጣጣል እና መሰረተ ቢስ ለማድረግ ቱር ቱር ማለቱን ጀምሮታል:: አሳቀኝ ገንፎ ከራቴ ተርፎ አሉ:: በጣም የሳበኝ ነገር ሰሞኑን በኤርሚያስ አመልጋ መታሰር ትንፍሽ ያላለው አውራምባ ታይምስ ኤርሚያስ ሲፈታ አብሳሪ ለመሆን መቸኮሉ ቁርጥ የኢትዮጵያ ቴሌቭዚንን መሰለኝ::
ዳዊት የማያውቅ ከሆነ ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ሃብት ማፍራት የሚችለው እና ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ንብረት ማፍራት የሚችለው ትግርኛ ተናጋሪ (ትግሬ) ብቻ ነው ብንል አንሳሳትም ምክንያታችንም እነሆ:: 1 በፓርቲ ደረጃ ህውሃት ከ66 በላይ ካምፓኒዎችን (ለምሳሌ ሱርኮንስትራክሽን መስፍን ኢንጅነሪንግ መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ኢዛና የወርቅ ማእድን ጣና ትሬዲንግ ትራንስ ኢትዮጵያ አፍርካ ኢንሹራንስ ወዘተ ወዘተ) የተቆጣጠረ ሲሆን ብአዴን ግን የህውሃትን አንድ ኩባንያ እንኳ የሚያክል ድርጂት የለውም::
አስታውሳለሁ ከጥቂትግዜ በፊት ብአዴን አንድ የባህል አዳራሽ ለመስራት ስንት ግዜ በሞባይል ህዝብን እየለመነ ሲያስቸግር:: 2 በግለሰብ ደረጃ እነ አንበሳ ባንክ ወጋገን ባንክን ካየን እንዲሁም እነ ሳትኮን ኮንስትራክሽን እነ ተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ከቻይና ድርጂቶች በመቀጠል የመንገድ የኮዶምንየም እና የዩንቨርሲቲዎች ግንባታ የሚገነቡት ድርጅቶች በሙሉ የትግሬ ናቸው:: ይህን ብየ ወደ ዋናው የህውሃት ሸር እና ተንኮል ልውሰዳችሁ:: የሚገርመው ህውሃቶች ይህን ሁሉ ሃብት ይዘው አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ነውና ትንንሽ ሌሎች ባለሃብቶችን በተለይም ነጥለው አማራ ባለሃብቶችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ድርጅታቸውን እያከሰሩ ይገኛሉ ለምሳሌ የአያት ሪል ስቴት ባለቤት የአቶ አያሌው መታሰር : እነ ማሩ በመስፍን ኢንጂነሪንግ ተጽእኖ ከጫዎታ ሜዳው መገለል : እነ የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ባለቤቶችን በማበሳጨት ካገር ማስዎጣት: በቅርቡ የአባይ መኪና መገጣጠሚያን አክስሮ ማዘጋት: ቀደም ብሎም አሁንም ኤርሚያስ አመልጋን ማመናጨቅ እና ማሰር እንዲሁም ሌሎች አማራ ነጋዴዎችን እያደኑ ከቻሉ ሃብታቸውን መቀማቱን ካልቻሉ አክስሮ ከሃገር ማስዎጣቱን ገፍተውበታል:: ይህ ሁሉ ሃብት የማጋበስ ስትራቴጅ ከምርጫ 97 በኋላ በህውሃት የተቀየሰ እና የተቀናበረ ነው::
ጥቂት የነበሩትን አማራ ነጋዴዎች ጨርሰዋቸዋል:: ዋናው ሴራ ግን ተፎካካሪያቸው አላሙዲንን በሪፖርተር ጋዜጣ አማካኝነት በማመናጨቅ ከጫወታ ሜዳው በሂደት እንዲለቁ ዎይምእንዳይፎ ካከሯቸው ማድረግ ነው ይህ ሂደት ሆን ተብሎ በተወሰኑ ህውሃቶች የሚካሄድ እንደሆነ እኔ እራሴ በደንብ አውቀዋለሁ:: ስለዚህ አውራምባ ታይምሱ የዩኒቲ ምሩቅ ዳዊት ከበደን ልለው የምፈልገው ነገር ቢኖር አንዳንዶች ትግሬ በመሆንህ ቢያገሉህ አይግረምህ እነሱንም አሁን አንተ እየደገፍካቸው ያለከው ህውሃቶች አግልለዋቸው ነው::
ይልቁንስ ዳዊት ሃቀኛ መሆን ከፈለክ ቀልዱን ትተህ ስለ ፍትሃዊ የሃብትና የስልጣን ክፍፍል ጻፍልን : መንግስትን ሞግትልን : እኛ እሱ ነው የናፈቀን:: የህውሃትን የንግድ ድርጅቶች ሙሉ ዝርር ማግኘት የፈለገ የሚከተለውን ሊንክ መጫን ይችላል::
http://www.ethiopianreview.com/research/wp-content/uploads/2011/11/Full-List-of-TPLF-Parasitic-Companies-Under-EFFORT4.pdf
ቸር ይግጠመን
ከአዘጋጁ፡ በዚህ አስተያየት ዙሪያ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን።